መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

1 ጢሞቴዎስ 2

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ስለዚህ ከሁሉ በፊት፣ ጸሎት፣ ምልጃና ምሥጋና ስለ ሰዎቸ ሁሉ እንዲደረግ እመክራለሁ፤ እግዚአብሔርን በመፍራትና በማክበር፣
2በጸጥታ ሕይወት ሰላማዊ ኑሮ እንድንኖር፣ ለነገሥታትና በሥልጣን ላይ ላሉ ሁሉ ጸልዩ፡፡
3ይህም በአዳኛችን በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ተቀባይነት ያለው ነገር ነው፡፡
4እርሱ ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና እውነትን ሁሉ ወደ ማውቅ እንዲደርሱ ይፈልጋልና፡፡
5አንድ እግዚአብሔር አለና፣ እንዲሁም በሰዎችና በእግዚአብሔር መካከል፣ ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ አንድ መካከለኛ አለ፤
6እርሱም ለሁሉ ራሱን ቤዛ አድርጎ የሰጠ፣ በትክክለኛው ጊዜ የተገለጠ ምስክር ነው፡፡
7ለዚህም ዓላማ እኔ ራሴ፣ አወጅ ነጋሪና ሐዋርያ ሆኜአለሁ፡፡ እውነትን እናገራለሁ አልዋሽም፤ እኔ ለአሕዛብ የእምነትና የእውነት አስተማሪ ነኝ፡፡
8ስለዚህ፣ ወንዶች ሁሉ በየሥፍራው ያለ ጥርጥርና ያለ ቁጣ የተቀደሱ እጆቻቸውን እያነሱ እንዲጸልዩ እፈልጋለሁ፡፡
9እንደዚሁም፣ ሴቶች አግባብ ያለው አለባበስ ይኑራቸው፣ ራሳቸውን በመግዛት ረጋ እንዲሉ እንጂ ጸጉራቸውን በወርቅ ወይም በዕንቁ በመሥራት ወይም ውድ የሆኑ ልብሶችን በመልበስ ሊያጌጡ አይገባም፡፡
10ነገር ግን እግዚአብሔርን ለሚፈሩ ሴቶች አግባብ እንደሆነው፣ በመልካም ሥራ ተውበው ይታዩ፡፡
11ሴት በጸጥታና በመታዘዝ ትማር፡፡
12ሴት በጸጥታ እንድትኖር እንጂ፣ እንድታስተምርና በወንድ ላይ ሥልጣን እንዲኖራት አልፈቅድም፡፡
13አስቀድሞ አዳም ተፈጥሮአልና፣ ከዚያም ሔዋን፡፡
14አዳም አልተታለለም፣ ነገር ግን ሴቲቱ ሙሉ ለሙሉ በመተላለፍ ተታልላለች፡፡
15ሆኖም፣ በእምነትና በፍቅር፣ በቅድስናም በመልካም አዕምሮ ጸንታ ብትኖር፣ ልጆችን በመውለድ ትድናለች፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።