1መታመኛችን በሆነው በክርስቶስ ኢየሱስ እና በአዳኛችን በእግዚአብሔር ትእዛዝ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ጳውሎስ፣
2በእምነት እውነታኛ ልጄ ለሆነው፣ ለጢሞቴዎስ፡፡ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ ምሕረትና ሰላም ለአንተ ይሁን፡፡
3ወደ መቄዶንያን በሄደኩ ጊዜ አንዳንድ ሰዎች ልዩ ትምህርትን እናዳያስተምሩ፣
4በእምነት የሆነውን የእግዚአብሔርን እቅድ ለማያግዙ ለታሪኮችና መጨረሻ የሌላቸውን የትውልዶችን ሐረግ ለመቁጠር ትኩረት ወደ መስጠት እንዳያዘነብሉ ታስጠነቅቃቸው ዘንድ በኤፌሶን እንድትቀመጥ አዘዝኩህ፡፡
5ነገር ግን የትእዛዙ ግብ ከንጹህ ልብ፣ ከመልካም ኅሊና እና ከእውነተኛ እምነት የሚወጣ ፍቅር ነ|ው፡፡
6አንዳንድ ሰዎች ከእነዚህ ነገሮች ርቀው ወደ ባዶ ወሬ ዞረዋል፡፡
7የሕግ አስተማሪዎች ለመሆን ተመኝተዋል፤ ነገር ግን የሚናገሩትንና መሆን አለበት የሚሉትን ነገር አያውቁትም፡፡
8ሆኖም ሕግ በትክክል ቢጠቀምበት መልካም እንደሆነ እናወቃለን፡፡
9እንዲሁም ሕግ ለጻድቅ ሰው እንዳልተሠራ እናውቃለን፤ ነገር ግን ሕግ የተሰጠው፣ ሕገወጥ ለሆኑና ለአመጸኞች ሰዎች ፣ እግዚአብሔርን ለማይፈሩና ለኃጢአተኞች ፣
10ለአመንዝሮችና ለግብረ ሰዶማውያን፣ ሰዎችን ባርያ አድርገው ለሚሸጡ፣ ለውሸተኞች፣ ለሐሰት ምስክሮች፣ ከእውነተኛው ትምህርት ርቀው ለሚገኙ ሰዎች ነው፡፡
11ይህ እውነተኛ ትምህርት በተባረከው አምላካችን ለእኔ በአደራ የተሰጠው ወንጌል ነው፡፡
12ለዚህ አገልገሎት ታማኝ እንድሆን ያበቃኝንና የሾመኝን፣ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን አመሰግናለሁ፡፡
13ምንም እንኳ አስቀድሞ ተሳዳቢና አሳዳጅ ብሆንም፣ ባለማወቅና ባለማመን ስላደረግሁት ከጌታ ዘንድ ምሕረትን አግኝቼአለሁ፡፡
14ነገር ግን የጌታችንም ጸጋ በክርስቶስ ኢየሱስ ከእምነትና ከፍቅር ጋር ይበልጥ በዛ፡፡
15‹‹ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም መጣ›› የሚለው መልዕክት ሁሉም ሊቀበሉት የተገባና አስተማማኝ ነው፡፡ እኔም ከእነዚህ ሁሉ የባስኩ ኃጢአተኛ ነኝ፡፡
16በዚህም ምክንያት ከኃጢአተኞች ዋነኛ በምሆን በእኔ ክርስቶስ ኢየሱስ ትእግስቱን ሁሉ ሊያሳይ ምሕረትን አገኘሁ፤ ይህም የሆነው በእርሱ ለሚያምኑና የዘላለም ሕይወት ለሚያገኙ ምሳሌ እሆን ዘንድ ነው፡፡
17ስለዚህ ለዘላለም ንጉሥ ፣ ለማይሞተው እና ለማይታየው፣ ብቻውን አምላክ ለሆነው፣ ክብርና ግርማ ለዘላለም ይሁን፡፡ አሜን፡፡
18ልጄ ጢሞቴዎስ ሆይ፣ ስለ አንተ አስቀድሞ በተነገረው ትንቢት ተስማምቼ ይህን አዝሃለሁ፤ መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፤
19ስለዚህም እምነትና መልካም ኅሊና ይኑርህ፡፡ አንዳንድ ሰዎች እነዚህን ክደው መርከብ አለመሪ እንደሚጠፋ በእምነት ነገር ጠፍተዋል፡፡
20ከእነዚህም መካከል በእግዚአብሔር ላይ የስድብን ቃል እንዳይናገሩ፣ ለሰይጣን አሳልፌ የሰጠኋቸው፣ ሄሜኔዎስ እና እስክንድሮስ ይገኙባቸዋል፡፡