መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

1 ተሰሎንቄ 3

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ስለዚህ ከዚያ በላይ ልንታገስ ባልተቻለን ጊዜ በአቴና ለብቻችን መቅረታችን መልካም እንደሆነ አሰብን።
2በእምነታችሁ ያጸናችሁና ያበረታችሁ ዘንድ ወንድማችንንና በክርስቶስ ወንጌል የእግዚአብሔር አገልጋይ የሆነውን ጢሞቴዎስን ላክንላችሁ፣
3ይህንን ያደረግነውም በእነዚህ መከራዎቻችሁ ማንም እንዳይናወጥ ነው፣ ለዚህ እንደተመረጥን ራሳችሁ ታውቃላችሁና።
4በእርግጥ ከእናንተ ጋር በነበርንበት ወቅት መከራ ልንቀበል እንዳለን አስቀድመን ነግረናችሁ ነበር፣ እንደምታውቁት የሆነውም ይኸው ነው።
5በዚህ ምክንያት ወደፊት ልታገስ ባቃተኝ ጊዜ ምናልባት ፈታኙ ፈትኗችሁ ልፋታችንም ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር ስለ እምነታችሁ አውቅ ዘንድ ላክሁት።
6ጢሞቴዎስ ከእናንተ ዘንድ ተመልሶ ስለ እምነታችሁና ፍቅራችሁ የምሥራች ባመጣልን ጊዜ ሁልጊዜ በመልካም እንደምታስታውሱንና እኛ ደግሞ ልናያችሁ እንደምንናፍቅ ሁሉ ልታዩን እንደምትናፍቁ ሲነግረን
7በዚህ ምክንያት ወንድሞች ሆይ፣ በችግራችንና በመከራችን ሁሉ በእናንተ እምነት ተጽናንተናል።
8በጌታ ጸንታችሁ ብትቆሙ እኛ ደግሞ አሁን በሕይወት እንኖራለን።
9በእናንተ ምክንያት በአምላካችን ፊት ስላገኘነው ደስታ ሁሉ ስለ እናንተ ለእግዚአብሔር እንዴት ያለ ምስጋና ማቅረብ እንችል ይሆን?
10ፊታችሁን ለማየትና በእምነታችሁ የሚጎድላችሁን ለመሙላት ሌሊትና ቀን እጅግ አጥብቀን እንጸልያለን።
11ራሱ አምላካችንና አባታችን፣ ጌታችንም ኢየሱስ ወደ እናንተ እንድንመጣ መንገዳችንን ያቅና፣
12እኛ ደግሞ እንደምናፈቅራችሁ ጌታ ለእርስ በርሳችሁና ለሰው ሁሉ የሚሆን ፍቅራችሁን ያብዛ ያትረፍርፍም።
13ጌታችን ኢየሱስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ሲመጣ በአምላካችንና በአባታችን ፊት ልባችሁን ነቀፋ በሌለበት ቅድስና ያጸና ዘንድ ይህንን ያድርግላችሁ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።