መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

1ኛ ሳሙኤል 5

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ፍልስጥኤማውያንም የእግዚአብሔርን ታቦት በመማረክ ከአቤንኤዘር ወደ አሽዶድ አመጡት።
2እነርሱም የእግዚአብሔርን ታቦት ማርከው ወደ ዳጎን ቤት ወስደው በዳጎን አጠገብ አቆሙት።
3የአሽዶድ ሰዎች በቀጣዩ ቀን ማልደው በተነሡ ጊዜ፥ ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በምድር ላይ በግምባሩ ተደፍቶ አዩ። ስለዚህ ዳጎንን አንሥተው በስፍራው መልሰው አቆሙት።
4ነገር ግን በማግስቱ ማልደው በተነሡ ጊዜ፥ ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በምድር ላይ በግምባሩ ተደፍቶ አዩ። በደጁ መግቢያ ውስጥ የዳጎን ራሱና እጆቹ ተሰብረው ወድቀው ነበር። የቀረው የዳጎን ሌላው የአካል ክፍሉ ብቻ ነበር።
5ለዚህ ነው እስካሁን እንኳን የዳጎን ካህናትና ሌላ ማንኛውም ሰው በአሽዶድ ወደሚገኘው ወደ ዳጎን ቤት በሚመጣበት ጊዜ የዳጎንን ደጅ መግቢያ ሳይረግጥ የሚያልፈው።
6የእግዚአብሔር እጅ በአሽዶድ ሰዎች ላይ ከብዶ ነበር። በአሽዶድና በዙሪያው ባሉት ላይ ጥፋትን በማምጣት በእባጭ መታቸው።
7የአሽዶድ ሰዎች የሆነባቸውን ባስተዋሉ ጊዜ፥ “እጁ በእኛና በአምላካችን በዳጎን ላይ ከብዳለችና የእስራኤል አምላክ ታቦት ከእኛ ጋር መቆየት የለበትም” አሉ።
8ስለዚህ ወደ ፍልስጥኤማውያን ገዢዎች ልከው በአንድ ላይ ሰበሰቧቸው፤ እነርሱም፥ "በእስራኤል አምላክ ታቦት ላይ ምን እናድርግ?" አሏቸው። እነርሱም፥ “የእስራኤል አምላክ ታቦት ወደ ጌት ይምጣ” ብለው መለሱላቸው። የእስራኤልን አምላክ ታቦት ወደዚያ ወሰዱት።
9ነገር ግን ወደዚያ ካመጡት በኋላ የእግዚአብሔር እጅ በከተማዪቱ ላይ ሆነ፥ ታላቅ መደናገርንም አደረገባቸው። ልጅና ዐዋቂውን፥ የከተማውን ሰዎች አስጨነቀ፤ ሰውነታቸውም በእባጭ ተወረረ።
10ስለዚህ የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ አቃሮን ላኩት። ነገር ግን የእግዚአብሔር ታቦት ወደ አቃሮን እንደ መጣ፥ አቃሮናውያን፥ "እኛንና ሕዝባችንን እንዲገድል የእስራኤልን አምላክ ታቦት ወደ እኛ አምጥተዋል" በማለት ጮኹ።
11ስለዚህ ወደ ፍልስጥኤማውያን ገዢዎች በመላክ ሁሉንም በአንድ ላይ ሰበሰቧቸው፤ እነርሱም፥ “እኛንና ሕዝባችንን እንዳይገድል የእስራኤልን አምላክ ታቦት ላኩት፥ ወደ ስፍራውም ይመለስ" አሏቸው። በዚያ የእግዚአብሔር እጅ እጅግ ስለበረታባቸው በከተማው ሁሉ የሞት ድንጋጤ ነበረ።
12ከሞት የተረፉት ሰዎች በእባጮቹ ይሠቃዩ ስለነበር የከተማዪቱ ጩኸት ወደ ሰማያት ወጣ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።