1ዳዊትም፥”አሁንም አንድ ቀን በሳኦል እጅ እሞታለሁ፤ ወደ ፍልስጥኤማውያን ምድር ከመሸሽ የሚሻል አማራጭ የለኝም፤ ያን ጊዜ ሳኦል በእስራኤል ወሰኖች ሁሉ ውስጥ እኔን መፈለጉን ያቆማል፤ በዚህ መንገድ ከእጁ አመልጣለሁ" ብሎ በልቡ አሰበ።
2ዳዊትም ተነሣ፥ እርሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ስድስት መቶ ሰዎች ወደ ጌት ንጉሥ ወደ አሜህ ልጅ ወደ አንኩስ ተሻገሩ።
3ዳዊትና ሰዎቹ እያንዳንዱ ከቤተሰቡ ጋር፥ እርሱም ከሁለቱ ሚስቶቹ፥ ከኢይዝራኤላዊቱ ከአኪናሆምና የናባል ሚስት ከነበረችው ከቀርሜሎሳዊቷ ከአቢግያ ጋር በጌት ከአንኩስ ጋር ኖሩ።
4ዳዊት ወደ ጌት መሸሹን ሳኦል ሰማ፥ ስለዚህ ከዚህ በኋላ አልፈለገውም።
5ዳዊትም አንኩስን፥ "በዐይንህ ፊት ሞገስ አግኝቼ ከሆነ፥ በዚያ እኖር ዘንድ በአገሪቱ ካሉት ከተሞች በአንዲቱ ስፍራ ይስጡኝ፤ አገልጋይህ በንጉሣዊ ከተማ ከአንተ ጋር ለምን ይኖራል?" አለው።
6ስለዚህ በዚያን ቀን አንኩስ ጺቅላግን ሰጠው፤ እስከዛሬ ድረስ ጺቅላግ የይሁዳ ነገሥታት የሆነችው ለዚህ ነው።
7ዳዊት በፍልስጥኤም ምድር የኖረበት ቀን ሲቆጠር አንድ ዓመት ከአራት ወር ሆነው።
8ዳዊትና ሰዎቹ ጌሹራውያንን፥ ጌርዛውያንን እና አማሌቃውያንን በመውረር የተለያዩ ቦታዎችን አጠቁ፤ እነዚህ ሕዝቦች እስከ ሱርና እስከ ግብፅ ምድር ድረስ ባለው አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ናቸው። እነርሱም ከጥንት ጀምሮ በዚያ ምድር ይኖሩ ነበር።
9ዳዊትም ምድሪቱን መታ፥ ወንዱንም ሆነ ሴቱን በሕይወት አልተወም፤ በጎችን፥ በሬዎችን፥ አህዮችን፥ ግመሎችን እና ልብሶችን ወሰደ፤ ተመልሶም እንደገና ወደ አንኩስ መጣ።
10አንኩስ፥ "ዛሬ በማን ላይ ወረራ ፈጸማችሁ?" ብሎ ይጠይቅ ነበር፥ ዳዊትም፥ "በይሁዳ ደቡብ ላይ" ወይም "በደቡብ ይረሕምኤላውያን ላይ" ወይም "በደቡብ ቄናውያን ላይ" ብሎ ይመልስለት ነበር።
11"ስለዚህ ስለ እኛ፥ 'ዳዊት እንዲህና እንዲህ አደረገ' ለማለት እንዳይችሉ" ብሎ ነበርና ዳዊት ወደ ጌት ይዞ ለመምጣት በማሰብ ወንድ ወይም ሴት በሕይወት አያስቀርም ነበር። በፍልስጥኤም አገር በኖረበት ጊዜ ሁሉ ያደረገው እንደዚህ ነበር።
12አንኩስም፥ "የራሱ የሆነው የእስራኤል ሕዝብ አምርሮ እንዲጠላው አድርጓል፤ ስለዚህ ለዘላለም አገልጋዬ ይሆናል“ ብሎ ስላሰበ ዳዊትን አመነው።