መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

1ኛ ሳሙኤል 21

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከዚያም ዳዊት ካህኑን አቢሜሌክን ለማግኘት ወደ ኖብ መጣ። አቢሜሌክም ዳዊትን ለመገናኘት እየተንቀጠቀጠ መጣና፥ “አንድም ሰው አብሮህ ያልሆነውና ብቻህን የሆንከው ለምንደነው?” አለው።
2ዳዊትም ካህኑን አቢሜሌክን፥ “ንጉሡ ለአንድ ጉዳይ ልኮኛል። እርሱም፥ 'ስለምልክህ ጉዳይና ያዘዝኩህን ነገር ማንም እንዳያውቅ'ብሎኛል። ወጣቶቹንም የሆነ ቦታ ላይ እንዲጠብቁኝ ነግሬአቸዋለሁ።
3ታዲያ አሁን እጅህ ላይ ምን አለ? አምስት እንጀራ ወይም ያለውን ነገር ስጠኝ” አለው።
4ካህኑም ለዳዊት መልሶ፥ “ማንኛውም ሰው የሚበላው እንጀራ የለኝም፥ ነገር ግን ታዳጊ ወጣቶቹ ራሳቸውን ከሴቶች ጠብቀው ከሆነ የተቀደሰ እንጀራ አለ” አለው።
5ዳዊትም ለካህኑ እንዲህ ሲል መለሰለት፥ “በእርግጥ በእነዚህ ሦስት ቀናት ከሴቶች ተጠብቀናል። ለተራ ተልዕኮ በሚወጡበት ጊዜ ራሳቸውን ካነጹ ለዚህ ተልዕኮማ ከእኔ ጋር ያሉት ወጣቶች ሰውነት ለእግዚአብሔር እንዴት የበለጠ የተቀደሰ አይሆንም?”
6ስለዚህ ከተነሣ በኋላ በስፍራው ትኩስ እንጀራ ይደረግ ዘንድ፥ ከእግዚአብሔር ፊት ከተነሣው፥ ከገጸ ሕብስቱ በስተቀር ሌላ እንጀራ በዚያ አልነበረምና፥ ካህኑ ለእግዚአብሔር የተቀደሰውን እንጀራ ሰጠው።
7በዚያም ቀን ከሳኦል አገልጋዮች አንዱ በእግዚአብሔር ፊት በእዚያ ቆይቶ ነበር፤ ስሙ ዶይቅ የሚባል ኤዶማዊ፥ የሳኦል የእረኞቹ አለቃ ነበር።
8ዳዊት አቢሜሌክን፥ "እዚህ ጦር ወይም ሰይፍ ይኖርሃል? የንጉሡ ጉዳይ አስቸኳይ ስለነበረ ሰይፌንም ሆነ መሣሪያዬን ይዤ አልመጣሁም“ አለው።
9ካህኑም፥”በዔላ ሸለቆ የገደልከው የፍልስጥኤማዊው የጎልያድ ሰይፍ በጨርቅ ተጠቅልሎ እዚህ ከኤፉዱ ኋላ አለ። ሌላ የጦር መሣሪያ በዚህ የለምና እርሱን ልትወስደው ብትፈልግ ውሰደው።" ዳዊትም፥ "እንደ እርሱ ያለ ሌላ ሰይፍ የለም፤ እርሱን ስጠኝ" አለው።
10በዚያን ቀን ዳዊት ተነሥቶ ከሳኦል ፊት ሸሸ፥ ወደ ጌት ንጉሥ ወደ አንኩስም ሄደ።
11የአንኩስ አገልጋዮችም ንጉሡን፥ "ይህ የምድሪቱ ንጉሥ የሆነው ዳዊት አይደለም? 'ሳኦል ሺዎችን ገደለ፥ ዳዊት ዐሥር ሺዎችን ገደለ' እያሉ ስለ እርሱ በዘፈን እየተቀባበሉ ዘምረውለት አልነበረም? አሉት።
12ዳዊት ይህንን ቃል በልቡ አኖረው፥ የጌትን ንጉሥ አንኩስንም እጅግ ፈራው።
13በፊታቸውም አዕምሮውን ለወጠ፥ በያዙት ጊዜም እንደ ዕብድ ሆነ፤ የቅጥሩን በር እየቧጨረም ለሃጩን በጺሙ ላይ አዝረከረከ።
14አንኩስም አገልጋዮቹን፥ “ተመልከቱ፥ ሰውዬው ዕብድ እንደሆነ ታያላችሁ።
15ወደ እኔ ለምን አመጣችሁት? ይህንን ሰው በፊቴ እንዲያብድ ወደ እኔ ያመጣችሁት ያበዱ ሰዎችን ስላጣሁኝ ነው? በእርግጥ እንዲህ ያለው ሰው ወደ ቤቴ ይገባል?” አላቸው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።