መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

1ኛ ሳሙኤል 12

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ሳሙኤል እስራኤላውያንን በሙሉ እንዲህ አላቸው፥”የነገራችሁኝን በሙሉ ሰምቻችኋለሁ፥ ንጉሥንም በላያችሁ ላይ አንግሼላችኋለሁ።
2አሁንም፥ በፊታችሁ የሚሄድላችሁ ንጉሥ ይኸውላችሁ፤ እኔ አርጅቻለሁ፥ ጸጉሬም ሸብቷል፤ ልጆቼም ከእናንተ ጋር ናቸው። ከልጅነቴ ጀምሮ እስካሁን ድረስ በፊታችሁ ኖሬአለሁ።
3ይኸው በፊታችሁ ነኝ፤ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ። የማንን በሬ ወስጃለሁ? የማንንስ አህያ ወስጃለሁ? ማንን አታለልሁ? በማንስ ላይ ግፍ ሠራሁ? ዓይኖቼን ለማሳወር ከማን እጅ ጉቦ ተቀበልሁ? መስክሩብኝና እመልስላችኋለሁ።“
4እነርሱም፥”አላታለልከንም፥ ግፍም አልሠራህብንም ወይም ከማንም እጅ ምንም ነገር አልሰረቅህም“ አሉ።
5እርሱም፥”በእጄ ላይ ምንም እንዳላገኛችሁ ዛሬ እግዚአብሔር በእናንተ ላይ ምስክር ነው፥ እርሱ የቀባውም ምስክር ነው“ አላቸው። እነርሱም፥”እግዚአብሔር ምስክር ነው“ ብለው መለሱ።
6ሳሙኤልም ሕዝቡን፥”ሙሴንና አሮንን የመረጣቸው፥ አባቶቻችሁንም ከግብፅ ምድር ያወጣቸው እግዚአብሔር ነው።
7አሁን እንግዲህ፥ እግዚአብሔር ለእናንተና ለአባቶቻችሁ ስለ ሠራላችሁ የጽድቅ ሥራ ሁሉ እንድሟገታችሁ በእግዚአብሔር ፊት ራሳችሁን አቅርቡ።
8ያዕቆብ ወደ ግብፅ በመጣ ጊዜ አባቶቻችሁ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ። እግዚአብሔር፥ ከግብፅ ምድር እየመሩ አውጥተው በዚህ ስፍራ እንዲቀመጡ ያደረጓቸውን ሙሴንና አሮንን ላከ።
9እነርሱ ግን አምላካቸውን እግዚአብሔርን ረሱ፤ እርሱም የሐጾር ሠራዊት አዛዥ በሆነው በሲሣራ እጅ፥ በፍልስጥኤማውያን እጅና በሞአብ ንጉሥ እጅ ሸጣቸው፤ እነዚህ ሁሉ አባቶቻችሁን ተዋጓቸው።
10እነርሱም ወደ እግዚአብሔር በመጮህ፥ "እግዚአብሔርን ትተን በኣልንና አስታሮትን በማገልገላችን ኃጢአት አድርገናል። አሁን ግን ከጠላቶቻችን እጅ አድነን፥ እኛም እናገለግልሃለን' አሉት።
11ስለዚህ እግዚአብሔር ይሩበኣልን፥ ባርቅን፥ ዮፍታሔንና ሳሙኤልን ልኮ በሰላም እንድትኖሩ በዙሪያችሁ ባሉ ጠላቶቻችሁ ሁሉ ላይ ድልን ሰጣችሁ።
12እናንተም የአሞን ሕዝብ ንጉሥ ናዖስ እንደመጣባችሁ ባያችሁ ጊዜ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ንጉሣችሁ ሆኖ እያለ፥ 'አይሆንም፥ ይልቁን በላያችን ላይ ንጉሥ መንገሥ አለበት' አላችሁኝ።
13አሁንም እናንተ የመረጣችሁት፥ እንዲሆንላችሁ የጠየቃችሁትና እግዚአብሔርም በእናንተ ላይ ንጉሥ እንዲሆን የመረጠው ንጉሥ ይኸውላችሁ።
14እናንተም እግዚአብሔርን ብትፈሩት፥ ብታገለግሉት፥ ድምፁንም ብትታዘዙና በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ላይ ባታምጹ ያን ጊዜ እናንተና በላያችሁ የሚገዛው ንጉሣችሁ የአምላካችሁ የእግዚአብሔር ተከታዮች ትሆናላችሁ።
15የእግዚአብሔርን ድምፅ ባትታዘዙ፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ላይ ብታምጹ፥ ያን ጊዜ በአባቶቻችሁ ላይ እንደነበረ የእግዚአብሔር እጅ በእናንተ ላይ ይሆናል።
16አሁንም፥ ራሳችሁን አቅርቡና እግዚአብሔር በዓይናችሁ ፊት የሚያደርገውን ይህንን ታላቅ ነገር ተመልከቱ።
17ዛሬ የስንዴ መከር ነው አይደል? ነጎድጓድና ዝናብን እንዲልክ እግዚአብሔርን እጠራለሁ። ከዚያም ለራሳችሁ ንጉሥ በመጠየቃችሁ በእግዚአብሔር ፊት ያደረጋችሁት ክፋት ታላቅ እንደሆነ ታውቃላችሁ፥ ታያላችሁም“።
18ስለዚህ ሳሙኤል እግዚአብሔርን ጠራ፤ በዚያው ቀን እግዚአብሔር ነጎድጓድንና ዝናብን ላከ። ሕዝቡም ሁሉ እግዚአብሔርንና ሳሙኤልን በጣም ፈሩ።
19ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ ሳሙኤልን፥ "እንዳንሞት፥ ስለ አገልጋዮችህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ። ለራሳችን ንጉሥ በመጠየቃችን በኃጢአታችን ሁሉ ላይ ይህንን ክፋት ጨምረናልና” አሉት።
20ሳሙኤል እንዲህ ሲል መለሰላቸው፥ “አትፍሩ። ይህንን ሁሉ ክፋት አድርጋችኋል፥ ነገር ግን እግዚአብሔርን በሙሉ ልባችሁ አገልግሉት እንጂ ከእግዚአብሔር ፊታችሁን አትመልሱ።
21የማይጠቅሙ ናቸውና ሊረዷችሁ ወይም ሊረቧችሁ የማይችሉትን ከንቱ ነገሮች አትከተሉ።
22እግዚአብሔር የራሱ ሕዝብ ሊያደርጋችሁ ስለ ወደደ፥ ስለ ታላቅ ስሙ ሲል ሕዝቡን አይጥላቸውም።
23ስለ እናንተ መጸለይን በመተው በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአትን ማድረግ ከእኔ ይራቅ። ይልቁንም፥ መልካሙንና ትክክለኛውን መንገድ አስተምራችኋለሁ።
24ብቻ እግዚአብሔርን ፍሩት፥ በሙሉ ልባችሁም በእውነት አገልግሉት። ያደረገላችሁን ታላላቅ ነገሮች አስቡ።
25ክፉ በማድረግ ብትጸኑ ግን እናንተና ንጉሣችሁ ትጠፋላችሁ”።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።