መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

1ኛ ጴጥሮስ 4

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ክርስቶስ በሥጋው መከራን ስለ ተቀበለ፣ እናንተም በዚሁ ዐላማ ታጥቃችሁ ተነሡ፤ በሥጋው መከራን የሚቀበል ሰው ኀጢአትን ትቶአል።
2እንዲህ ያለው ሰው ከእንግዲህ በሚቀረው ዕድሜ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ እንደ ሥጋ ምኞት አይኖርም።
3አሕዛብ ፈልገው እንደሚያደርጉት በመዳራት፣ በሥጋ ምኞት፣ በስካር፣ ቅጥ ያጣ ፈንጠዝያ፣ በጭፈራና ርኵስ ከሆነ የጣዖት አምልኮ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።
4እነዚህን ነገሮች ለማድረግ ከአነርሱ ጋር አለመተባበራችሁ እንግዳ ሆኖባቸው ስለ እናንተ ክፉ ያወራሉ።
5ነገር ግን እነርሱ በሕያዋንና በሙታን ላይ ሊፈርድ ለተዘጋጀው መልስ ይሰጣሉ።
6ወንጌል ለሙታን የተሰበከው በዚህ ምክንያት ነው፤ በሥጋቸው እንደ ሰው ሁሉ ይፈረድባቸዋል፤ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በመንፈስ ይኖራሉ።
7የሁሉም ነገር መጨረሻ ተቃርቦአል፤ ስለዚህ መጸለይ እንድትችሉ ንቁ አእምሮ ይኑራችሁ፤ በአስተሳሰባችሁም ጠንቃቆች ሁኑ።
8ፍቅር ብዙ ኀጢአትን ይሸፍናልና ከሁሉ አስቀድሞ እርስ በርሳችሁ ከልብ ተዋደዱ፤
9ያለ ማጒረምረም እርስ በርሳችሁ በእንግድነት ተቀባበሉ።
10እንደ ታማኝ የእግዚአብሔር ልዩ ልዩ ጸጋ መጋቢ እያንዳንዱ ሰው በተቀበለው የጸጋ ስጦታ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤
11የሚናገር ቢኖር እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢኖር እግዚአብሔር በሚሰጠው ብርታት ያገልግል፤ ይኸውም እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት በሁሉም ነገር እንዲከብር ነው፤ ክብርና ኀይል ከዘላለም እስከ ዘላለም ለእርሱ ይሁን፤ አሜን።
12ወዳጆች ሆይ፤ እንደ እሳት የሚፈትን ብርቱ መከራ ስትቀበሉ፣ እንግዳ ነገር እንደ ደረሰባችሁ በመቍጠር አትደነቁ፤
13ነገር ግን ክብሩ በሚገለጥበት ጊዜ ደስታችሁ ታላቅ እንዲሆን የክርስቶስ መከራ ተካፋዮች በመሆናችሁ ሐሴት አድርጉ።
14ስለ ክርስቶስ ስም ብትሰደቡ፣ የክብር መንፈስ የሆነው የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ላይ ስለሚያርፍ ቡሩካን ናችሁ።
15ከእናንተ ማንም እንደ ነፍሰ ገዳይ፣ እንደ ሌባ፣ እንደ ክፉ አድራጊ ወይም በሰው ነገር ጣልቃ እንደሚገባ ሰው ሆኖ መከራን አይቀበል፤
16ማንም ክርስቲያን በመሆኑ መከራ ቢደርስበት፣ በዚህ ስም እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር፤
17ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት የሚጀምርበት ጊዜ ቀርቦአል። እንግዲህ ፍርድ የሚጀምረው በእኛ ከሆነ፣ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ ሰዎች መጨረሻቸው ምን ይሆን?
18እንግዲህ፣ ጻድቅ ሰው የሚድነው በጭንቅ ከሆነ፣ ዐመፀኛውና ኀጢአተኛው እንዴት ይሆን ይሆን?”
19ስለዚህ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መከራ የሚቀበሉ መልካም እያደረጉ ነፍሳቸውን ለታመነው ፈጣሪ ዐደራ ይስጡ። ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።