መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

1ኛ ጴጥሮስ 3

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ሚስቶች ሆይ፤ እናንተም እንደዚሁ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤ አንዳንድ ለቃሉ የማይታዘዙ ቢኖሩ እንኳ፣ ሚስቶቻቸው ቃል ሳይናገሩ በመልካም አኗኗራቸው ሊማርኳቸው ይችላሉ፤
2ይህም የሚሆነው ለእነርሱ ያላችሁን አክብሮት በንጹሕ አኗኗራችሁ ሲመለከቱ ነው።
3ውበታችሁ በውጫዊ ነገሮች በመሽሞንሞን ይኸውም ሹሩባ በመሠራት፣ በወርቅ በመንቆጥቆጥ ወይም ጌጠኛ ልብስ በመልበስ አይሁን፤
4ነገር ግን ውበታችሁ በእግዚአብሔር ፊት የከበረ፣ ገርና ጭምት መንፈስ ያለበት፣ ምንጊዜም የማይጠፋ የውስጥ ሰውነት ውበት ይሁን።
5የቀድሞ ቅዱሳት ሴቶች የተዋቡት በዚህ ዐይነት ነበር፤ እነርሱ በእግዚአብሔር የሚደገፉና ለባሎቻቸ የሚታዘዙ ነበሩ።
6ሣራም እንደዚሁ አብርሃምን «ጌታዬ» እያለች ትታዘዘው ነበር፣ እናንተም መከራን ሳትፈሩ መልካም ብታደርጉ፣ አሁን የእርሷ ልጆች ናችሁ።
7እንዲሁም ባሎች ሆይ፤ ሚስቶቻችሁ ደካማ አጋር መሆናቸውን ዐውቃችሁ፣ የሕይወትን ጸጋ ከእናንተ ጋር አብረው የሚካፈሉ መሆናቸውንም ተገንዝባችሁ አብራችኋቸው ኑሩ። ጸሎታችሁ እንዳይከለከል ይህን አድርጉ።
8በመጨረሻም፣ ሁላችሁ በአንድ ሐሳብ ተስማሙ፤ ተዛዘኑ፤ እንደ ወንድማማቾች ተዋደዱ፤ ርኅሩኆችና ትሑታን ሁኑ።
9ክፉን በክፉ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ፤ በዚህ ፈንታ ባርኩ፤ ምክንያቱም እናንተ የተጠራችሁት በረከትን ለመውረስ ነው።
10ስለዚህ «ሕይወትን የሚወድና መልካም ቀኖችን ሊያይ የሚፈልግ ምላሱን ከክፉ፣ ከንፈሮቹንም ተንኰል ከመናገር ይከልክል።
11ከክፉ ይራቅ፤ መልካምንም ያድርግ፤ ሰላምን ይፈልግ፤ ይከተላትም።
12የጌታ ዐይኖች ጻድቃንን ይመለከታሉና፤ ጆሮቹም ጸሎታቸውን ለመስማት የተከፈቱ ናቸው፤ የጌታ ፊት ግን በክፉ አድራጊዎች ላይ ነው።»
13መልካም ነገር ለማድረግ ብትቀኑ የሚጐዳችሁ ማን ነው?
14ነገር ግን በጽድቅ ምክንያት መከራ ቢደርስባችሁ ቡሩካን ናችሁ፤ ዛቻቸውን አትፍሩ፤ አትታወኩም።
15ይልቁንም፣ ክርስቶስ የከበረ መሆኑን ተረድታችሁ በልባችሁ ቀድሱት። እናንተ በእግዚአብሔር ላይ ስላላችሁ መታመን ምክንያቱን ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ሁል ጊዜ የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤ ነገር ግን ይህን ሁሉ በትሕትናና በአክብሮት አድርጉት፤
16በክርስቶስ ያላችሁን መልካም አናናራችሁን የሚያክፋፉ ሰዎች በሐሜታቸው እንዲያፍሩ በጎ ኅሊና ይኑራችሁ።
17እግዚአብሔር የሚፈልገው ይህን ከሆነ፣ ክፉ ሠርቶ መከራ ከመቀበል ይልቅ መልካም አድርጎ መከራ መቀበል ይሻላል፤
18እንዲሁም ክርስቶስ አንድ ጊዜ ስለ ኀጢአታችን ሞቷል። ወደ እግዚአብሔር ያቀርበን ዘንድ፣ ጻድቅ የሆነው እርሱ ስለ እኛ ስለ ዐመፀኞች ሞተ፤ እርሱ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፤
19በመንፈስም ሄዶ በወህኒ ቤት ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው፤
20በወህኒ የነበሩት እነዚህ ነፍሳት ቀድሞ በኖኅ ዘመን መርከብ ሲሠራ እግዚአብሔር በትዕግሥት ይጠብቃቸው የነበሩ እምቢተኞች ናቸው፤ እግዚአብሔር ከውሃ ያዳናቸው ጥቂት ሰዎችን፣ ይኸውም ስምንት ሰዎችን ብቻ ነበር።
21ይህም ውሃ አሁን እናንተን የሚያድነው የጥምቀት ምሳሌ ነው፤ ይህ ጥምቀት የሰውነትን ዕድፍ ማስወገድ ሳይሆን ንጹሕ ኅሊናን ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ልመና ነው፤ የሚያድናችሁም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ አማካይነት ነው፤
22እርሱ ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር አብ ቀኝ አለ፤ መላእክት፣ ሥልጣናትና ኀይላትም ተገዝተውለታል።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።