መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

1ኛ ነገስት 4

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ንጉሡ ሰሎሞን በመላው አስራኤል ላይ ነግሦ ነበር።
2ንጉሡም የሾማቸው ባለሥልጣኖች እነዚህ ናቸው። እነርሱም፡- ዓዛርያስ የተባለው የሳዶቅ ልጅ፡- ካህን ነበር።
3ኤልያፍና አኪያ የተባሉ የሴባ ልጆች የቤተ መንግሥት ጻሐፊዎች ነበሩ። ኢዮሣፍጥ የተባለው የአሒሉድ ልጅ ታሪክ ጻሐፊና የመዛግብት ኃላፊ ነበር።
4በናያስ የተባለው የዮዳሄ ልጅ የጦር ሠራዊት አዘዥ ነበር። ሳዶቅና አብያታር ካህናት ነበሩ።
5ዓዛርያስ የተባለው የናታን ልጅ፡- የክፍለተ አገራት ገዢዎች የበላይ ኃላፊ ነበር። የናታን ልጅ ዛቡድ፡- ካህንና የንጉሡ አማካሪ ነበር።
6አሒሳር የተባለው፡- የቤተ መንግሥት አገልጋዮች ኃላፊ፤ አዶኒራም የተባለው የዓብዳ ልጅ፡- የግዳጅ ሥራ ተቆጣጣሪና ኃላፊ ነበር።
7ንጉሡ ሰሎሞንም በመላው እስራኤል ለንጉሡና ለንጉሡ ቤተ ሰብ ቀለብ የሚያዘጋጁ ዐሥራ ሁለት ባለሥልጣኖች ነበሩት፡፡ እያንዳንዳቸውም በዓመት ውስጥ ለአንድ ወር ቀለብ የማቅረብ ግዴታ ነበረባቸው፡፡
8የእነዚህም ዐሥራ ሁለት ገዢዎችና የሚያስተዳድሩአቸው ግዛቶች ስም ዝርዝር ከዚህ የሚከተለው ነው፡- ቤንሑር፡- ኮረብታማ የሆነችው የኤፍሬም አገር ገዢ፤
9ቤንዴር፡- የማቃጽ የሻዓልቢም፤ የቤትሻሜሽ፡- የኤሎንና የቤት ሐናን ከተሞች ገዢ፤
10ቤንሔሴድ፡- የአሩቦትና የሶኮ ከተሞችና የመላው የሐፌር ግዛት አስተዳዳሪ፤
11ጣፋት የተባለችውን የሰሎሞንን ሴት ልጅ አግብቶ የነበረው ቤን አሚናዳብ የመላው የዶር ግዛት አስተዳዳሪ፤
12በዓና የተባለው የአሒሉድ ልጅ፡-የታዕናክና የመጊዶ ከተሞች፤ እንዲሁም በቤትሳን አጠገብ ያለው ግዛት በሙሉ በጸርታን ከተማ አጠገብ ያለው ግዛትና በኢይዝራኤል ከተማ በስተደቡብ ያለው ግዛት፤ እንዲሁም አቤልመሖላና ዮቅምዓም ተብለው እስከሚጠሩት ከተሞች ድረስ ያለው ግዛት ሁሉ አስተዳዳሪ፤
13በገለዓድ ራሞት ቤን ጌቤር ተብላ የምትጠራው ከተማ በገለዓድ የምናሴ ዘር የሆነው የኢያዕር ጎሣ ይዞታዎች የሆኑት መንደሮች፤ በባሳን አርጎብ ተብላ የምትጠራው ግዛት እንዲሁም በሮቻቸው የነሐስ መወርወሪያ ባሉአቸው የቅጥር ግንቦች የተመሸጉ በድምሩ የስልሳ ታላላቅ መንደሮች አስተዳዳሪ፤
14አሒናዳብ የተባለው የዔዶ ልጅ፡- የመሃናይም ክፍለ አገር ገዢ፤
15መካከል ባስማት ተብላ የምትጠራውን የሰሎሞንን ሴት ልጅ አግብቶ የነበረው አኪማአስ፡- የንፍታሌም ግዛት አስተዳዳሪ፤
16በዓና የተባለው የሔሻይ ልጅ፡- የአሴር ግዛትና የበዓሎት ከተማ ገዢ፤
17ኢዮሣፍጥ የተባለው የፋሩሕ ልጅ፡- የይሳኮር ግዛት አስተዳዳሪ፤
18ሳሚ የተባለው የኤላ ልጅ፡- የብንያም ግዛት አስተዳዳሪ፤
19ጊቤር የተባለው የኡሪ ልጅ፡- በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎንና በባሳን ንጉሥ በዐግ ትገዛ የነበረችው የገለዓድ ግዛት አስተዳዳሪ፤ እነዚህን ዐሥራ ሁለቱን አስተዳዳሪዎች የሚቆጣጠር በመላ አገራቱ ሌላ አንድ የበላይ ኃላፊ ነበር፡፡
20የይሁዳና የእስራኤል ሕዝብ ብዛት እንደ ባሕር ዳር አሸዋ ነበር፤ እነዚህ ሁሉ እየበሉና እየጠጡ ዘወትር ደስ እየተሰኙ ነበር፡፡
21የሰሎሞንም ግዛት ከኤፍራጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ፍልስጥኤም ግዛት፣ ከዚያም አልፎ እስከ ግብፅ ወሰን ያለውን አገር ሁሉ ያጠቃልል ነበር፤ የእነዚህም አገሮች ሕዝቦች በጠቅላላ ሰሎሞን በነበረበት ዘመን ሁሉ ለእርሱ ተገዢዎች ሆነው ይገብሩለት ነበር፡፡
22ሰሎሞንም በየቀኑ ለቀለብ የሚሆን አምስት ሺህ ኪሎ ግራም ያህል ምርጥ ዱቄት፤ ዐሥር ሺህ ኪሎ ግራም ያህል ነበር፡፡
23በበረት ውስጥ እየተመገቡ የደለቡ ዐሥር ሰንጋዎችና በግጦሽ መስክ ተሰማርተው የተመገቡ ሃያ ፍሪዳዎች፣ አንድ መቶ በጎች፤ ከዚህም ሌላ አጋዘኖች፣ የሜዳ ፍየሎች፤ ሚዳቆዎችና ምርጥ ወፎች ያስፈልጉት ነበር፡፡
24ሰሎሞን ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ምዕራብ ያለው ምድር ሁሉ ከቲፍሳ ከተማ ጀምሮ እስከ ጋዛ ከተማ ድረስ ይገዛ ነበር፤ ይህም ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተምዕራብ የሚገኙትን ነገሥታት ሁሉ ያጠቃልላል፤ ጎረቤቱ ከሆኑት አገሮችም ሁሉ ጋር በሰላም ይኖር ነበር፡፡
25በኖረበትም ዘመን ሁሉ ከዳር እስከ ቤርሳቤህ ድረስ መላው የይሁዳና የእስራኤል ሕዝብ ያለ ስጋት በሰላም ይኖር ነበር፤ እያንዳንዱ ቤተ ሰብ ለራሱ የሆነ የወይን ተክልና የበለስ ዛፍ ስለ ነበረው በእነዚህ ተክሎች ጥላ ሥር ያርፍ ነበር፡፡
26ሰሎሞን ሠረገላ የሚስቡ አርባ ሺህ ፈረሶች፣ ለጦርነት የሚያገለግሉ ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረሶች ነበሩት፡፡
27ለሰሎሞንና በቤተ መንግሥቱ ለሚቀለቡት ሁሉ የሚያስፈልገውን ምግብ የሚያቀርቡ ዐሥራ ሁለቱ ገዢዎች እያንዳንዳቸው በተመደበላቸው ወር ምንም ነገር ሳያጓድሉ በወቅቱ ያመጡ ነበር፡፡
28ከዚህም በቀር እያንዳንዱ ገዢ እንደሚችለው ሌላም አገልግሎት ለሚያበረክቱ የጋማ ከብቶች ገብስና ገለባ ያቀርብ ነበር፡፡
29እግዚአብሔር ለሰሎሞን አጅግ አስደናቂ የሆነ ጥበብንና አስተተዋይነትን እንዲሁም እንደ ባሕር ዳር አሸዋ ወሰን የማይገኝለትን ዕውቀት ሰጠው፡፡
30የሰሎሞንም ጥበብ ከምሥራቅ አገርና ከግብፅም ጥበበኞች እጅግ የላቀ ነበረ፡፡
31እርሱ ከሰዎች ሁሉ የሚበልጥ ታላቅ ጥበበኛ ነበረ፤ ከኢይዝራኤላዊው ኤታን፣ የማሖል ልጆች ከሆኑት ከሮማን ከካልኮልና ከዳርዓዕ የሚበልጥ ጥበበኛ ነበረ፤ ዝናውም ከፍ ብሎ በጎረቤት ሕዘቦች ሁሉ ዘንድ አስተጋባ፡፡
32ሦስት ሺህ ምሳሌዎችንና አንድ ሺህ አምስት የመዝሙር ድርስቶች ነበሩት፡፡
33ሰሎሞን ከሊባኖስ ዛፍ ጀምሮ በቤት ግንብ ላይ እስከሚበቅለው ሂሶጵ ድረስ ስለ ዛፎችና ስለ ተክሎች ምሳሌዎችን ተናግሮአል፤ እንዲሁም ስለ ልዩ ልዩ እንስሶች፣ ወፎች፣ በሆዳቸው እየተሳቡ ስለሚሄዱ ፍጥረቶችና ስለዓሣዎች አስተምሮአል፡፡
34በመላው ዓለም የሚገኙ ነገሥታት ስለ ሰሎሞን ጥበብ ለመስማት ይመጡ ነበር፡፡ ስለ ጥበቡም የሰሙት ከምድር ነገሥታት ሁሉ ወደ እርሱ መጥተዋል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።