1ሰሎሞን ብዙ የባዕዳን አገሮችን ሴቶች አፈቀረ፤ እነዚህም፡- የግብጽ ንጉሥ የፈረዖን ልጅ፣ የሒታውያን፣ የሞአባውያን፣ የአሞራውያን፣ የኤዶማውያንና የሲዶናውያን ሴቶች ልጆችን አፈቀረ፡፡
2እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን፣ አሕዛብ ሴቶችን ያገባችሁ እንደ ሆነ በእርግጥ ወደ አማልክቶቻቸው ስለሚስቡአችሁ እነርሱን አታግቡ ብሎ አስጠንቅቆአቸው ነበር፡፡ እነዚህ ሰሎሞን የወደዳቸው ሴቶች እግዚአብሔር እንዳያጋቡ ከከለከላቸው ሕዝቦች መካከል ናቸው፡፡ ይህ ትእዛዝ ቢኖርም ሰሎሞን ግን በእነርሱ ፍቅር ተነደፈ፡፡
3ሰሎሞን የነገሥታት ልጆች የሆኑ ሰባት መቶ ሚስቶችና ሦስት መቶ ቁባቶች ነበሩት፡፡ ሚስቶቹም ሰሎሞንን ከእግዚአብሔር እንዲርቅ አደረጉት፡፡
4በተለይም በዕድሜ እየሸመገለ በሄደ መጠን ለባዕዳን አማልእክት እንዲሰግድ አደረጉት፡፡ ሰሎሞንም እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሙሉ ልቡን ለእግዘአብሔር አላስገዛም፡፡
5የሲዶናውያን ሴት አምላክ የነበረችውን ለአስታሮትንና ሞሎክ ተብሎ የሚጠራውን ተለይቶ የሚታወቀውን የአሞናውያንን አምላክ ተከተለ፡፡
6ሰሎሞንም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ነገር በማድረጉ አባቱ ዳዊት እንዳደረገው እግዚአብሔርን በቅንነት አልተከተለም፡፡
7ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ በሚገኘው ተራራ ላይ ከሞሽ ተብሎ ለሚጠራው ለሞአባውያን አምላክና ሞሎክ ተብሎ ለሚጠራው ለአሞናውያን አምላክ የመስገጃ ስፍራዎችን ሠራ፡፡
8እንዲሁም የባዕዳን አገር ሚስቶቹ ሁሉ ለየአማልክቶቻቸው ዕጣን የሚያጥኑባቸውንና መሥዋዕት የሚያቀርቡባቸውን ስፍራዎች ሠራ፡፡
9የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሁለት ጊዜ የተገለጠለት ቢሆንም፣ ከእርሱ እየራቀ በመምጣቱ እግዚአብሔር ሰሎሞንን ተቆጣው፡፡
10ባዕዳን አማልክትን እንዳያመልክ አዘዘው፡፡ ነገር ግን ሰሎሞን ለእግዚአብሔር አልታዘዘም፡፡
11ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ አለው፡- ከእኔ ጋር የገባኸውን ቃል ኪዳን ስላፈረሰክና ሕጌንም ስላልፈጸምክ መንግሥትህን ከአንተ ወስጄ ከአገልጋዮችህ ለአንዱ እሰጣለሁ፡፡
12ይሁን እንጂ ለአባትህ ለዳዊት ስል ይህን የማደርገው አንተ ባለህበት ዘመን ሳይሆን በልጅህ መንግሥት ጊዜ ይሆናል፡፡
13ሆኖም ሁሉንም መንግሥት አልወስድም፤ ለአገልጋዬ ለዳዊትና ለመረጥኩት ከተማ ለኢየሩሳሌም ስል ለልጅህ አንዱን ነገድ እሰጠዋለሁ፡፡
14ስለዚህም እግዚአብሔር የኤዶማውያኑን ነገሥታት ዘር ሀዳድን በሰሎሞን ላይ ጠላት አድርጎ አስነሣበት፡፡ እርሱም ከኤዶም ንጉሣዊ ቤተ ሰብ ነበር፡፡
15ዳዊት ከኤዶማውያን ጋር ይዋጋ በነበረ ጊዜ፣ የጦር አዛዡ ኢዮአብ ለመቅበር ወጥቶ በነበረበት ጊዜ፣ በኤዶም ወንዶች ሁሉ ተገድለው ነበር፡፡
16ኢዮአብና የእስራኤል ሠራዊት የኤዶምን ወንዶች ልጆች ገድለው እስኪጨርሱ ድረስ ስድስት ወራት በዚያ ቆይተዋል፡፡
17ነገር ግን ከሞት የተረፉትና ሀዳድ በአባቱ አገልጋዮች ወደ ግብጽ ተወሰዱ፡፡ በዚያን ጊዜ ሀዳድ ገና ሕፃን ነበር፡፡
18እነርሱም ከምድያም ተነሥተው ሰዎችን ወደ ግብፅ ወደወሰዱበት ወደ ፋራን ሄዱ፤ በዚያም የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን ለሀዳድ ቤት፣ መሬትና ምግብ ሰጠው፡፡
19ሀዳድም በንጉሡ ፈርዖን ፊት ታላቅ ሞገስ አገኘ፡፡ ስለዚህ ንጉሡም የሚስቱን የጣፍኔስን እኅት ለሀዳድ ሚስት እንድትሆነው ሰጠው፡፡
20የጣፍኔስንም እኅት ጌንባት ተብሎ የሚጠራውን ወንድ ልጅ ለሀዳድ ወለደችለት፤ እርሱንም ንግሥቲቱ ወስዳ በቤተ መንግሥት አሳደገችው፤ ከፈረዖንም ወንዶች ልጆች ጋር ኖረ፡፡
21ሀዳድ በግብጽ ሳለ የንጉሥ ዳዊትንና የሠራዊቱን አዛዥ የኢዮአብን መሞት በሰማ ጊዜ፣ ወደ አገሬ ተመልሼ እንድሄድ አሰናብተኝ ሲል ፈረዖንን ጠየቀ፡፡
22ከዚያም ፈረዖን ስለምን ትሄዳለህ? ወደ አገርህ ለመሄድ የፈለግከው ከቶ ምን ተጓድሎብህ ነው? አለው፡፡ ሀዳድም ምንም የተጓደለብኝ ነገር የለም፤ ብቻ ወደ ትውልድ አገሬ እንድመለስ ፍቀድልኝ ሲል ለንጉሡ መለሰ፡፡
23እንደገናም እግዚአብሔር ረዞን ተብሎ የሚጠራውን የኤሊዓዳ ልጅ በሰሎሞን ላይ ሌላ ጠላት አድርጎ አስነሣበት፡፡ ረዞን የጾባ ንጉሥ ከነበረው ከጌታው ከዞአብ ንጉሥ ከሀዲድዔዚር ኮብልሎ ነበር፡፡
24ዳዊት ሀዲድዔዚርን ድል ባደረገበት ጊዜ፣ ረዞን ለራሱ ጦር ሰብስቦ የጥቂት ኃይል አለቃ ሆኖ ነበር፡፡ የረዞን ጦር ወደ ደማስቆ ሄደው እዚያ መኖር ጀመሩ፤ በኋላም ደማስቆን ተቆጣጠረ፡፡
25በሰሎለሞን ዘመነ መንግሥት ሁሉ ሀዳድ ካደረሰበት ችግር በተጨማሪ ረዞን የእስራኤል ጠላት ነበር፡፡ ስለዚህ ረዞን በሶርያ ላይ ገዢ ሆኖ በእስራኤል ላይ ጠላትነቱን ቀጠለ፡፡
26የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም፣ ኤፍሬማዊው የሰሎሞን ባለሥልጣናት አንዱ የሆነው፣ ጸሬዳ ተብሎ የምትጠራው ክፍል ተወላጅ የሆነ፣ የእናቱም ስም ጽሩዓ፣ ባልዋ የሞተባት ሴት ነበረች፤ እርሱም በሰሎሞን ላይ እጁን አነሣ፡፡
27ኢዮርብዓም በሰሎሞን ላይ እጁን ያነሣበት ምክንያት፤ በዚያን ጊዜ ሰሎሞን ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ሚሎ ተብሎ የሚጠራውን ጎድጓዳ ስፍራ በመሙላት እየደለደለና የአባቱን የዳዊትን ከተማ ቅጥሮች እየጠገነ ነበር፡፡
28ኢዮርብዓም ጽኑዕ ኃያል ሰው ነበር፡፡ ሰሎሞንም ይህን ተመልክቶ ወጣቱ ትጉህና ብርቱ ሠራተኛ በመሆኑ በዮሴፍ ነገድ ግዛት ላይ ሁሉ ኃላፊ አድርጎ ሾመው፡፡
29በዚያን ጊዜ ኢዮርብዓም ከኢየሩሳሌም ወጥቶ በጉዞ ላይ ሳለ፣ ሴሎናዊው ነቢዩ አኪያ በመንገድ ላይ አገኘው፡፡ አኪያም አዲስ መጎናጸፊያ ለብሶ ሁለት ሰዎች ለብቻ በሜዳ ላይ ነበሩ፡፡
30አኪያም የለበሰውን አዲስ መጎናጸፊያ አውልቆ ከዐሥራ ሁለት ቆራረጠው፡፡
31ኢዮርብዓምንም እንዲህ አለው፤ የእስራኤል አምላክ እግዚያብሔር እንዲህ ይላል፡- «ዐሥሩን ቁራጭ ለራስህ ውሰድ፤ ‹መንግሥትን ከሰለሞን ወስጄ ዐሥሩን ነገድ ለአንተ እሰጥሃለሁ፣
32ለአገልጋዬ ለዳዊትና ከሁሉም የእስራኤል ነገዶች ለመረጥኳት ለኢየሩሳሌም ከተማ ስል ለሰለሞን አንድ ነገድ አስቀርቼለታለሁ፡፡
33ይህንንም የማደርገው ሰሎሞን እኔን ትቶ ባዕዳን አማልክትን፡- አስታሮት ተብላ የምትጠራውን የሲዶና አምላክ፣ ካሞሽ ተብሎ የሚጠራውን የሞአብ አምላክና ሞሎክ ተብሎ የሚጠራውን የአሞናውያን አምላክ ስላመለከ ነው፡፡ አባቱ ዳዊት እንዳደረገ በፊቴ ትክክል የሆነውን፣ ሕጎቼንና ትእዛዞቼንም አልጠበቀም፡፡
34ይሁን እንጂ ከሰለሞን እጅ መንግሥትን በሙሉ አልወስድበትም፤ በዚህ ፈንታ በሕይወት እስካለም ድረስ በሥልጣን ላይ እንዲቆይ አደርገዋለሁ፤ ይህንንም የማደርገው ለመረጥኩትና ሕጎቼንና ትእዛዞቼን ለፈፀመው ለአገልጋዬ ለዳዊት ስል ነው፡፡
35ነገር ግን መንግሥትን ከሰለሞን ልጅ ወስጄ ለአንተ ዐሥሩን ነገዶች እሰጥሃለው፡፡
36ስሜ እንዲጠራባት በመረጥኳት በኢየሩሳሌም አገልጋዬ ዳዊት በፊቴ አንድ ዘር ይኖረው ዘንድ ለልጁ አንድ ነገድ እሰጠዋለው፡፡
37ኢዮርብዓም ሆይ! እኔ አንተን የእስራኤል ንጉሥ አድርጌሃለሁ፤ አንተ በወደድከው ግዛት ሁሉ ላይ መሪ ትሆናለህ፡፡
38አገልጋዬ ዳዊት እንዳደረገው በፍፁም ልብህ ብትታዘዘኝ፣ በሕጎቼና በትእዛዞቼ ጸንተህ ብትኖር፣ በእኔ ፊት ሞገስ ብታገኝ፣ እኔ ዘወትር ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ በእስራኤል ላይ እንድትነግሥም አደርግሃለሁ፤ ለዳዊት ባደረግሁት ዓይነት ዘሮችህ ከአንተ በኋላ እንደሚነግሡ አረጋግጥልሃለሁ፡፡
39በሰለሞን ኃጢአት ምክንያት የዳዊትን ትውልዶች እቀጣለሁ፤ ነገር ግን የምቀጣቸው ለዘላለም አይደለም፡፡
40ከዚህም የተነሣ ሰለሞን ኢዮርብዓምን ለመግደል ሞከረ፡፡ ነገር ግን ኢዮርብዓም ወደ ግብፅ ንጉሥ ሺሻቅ በመኮበለል አመለጠ፤ ሰለሞን እስከ ሞተበት ጊዜ ድረስ እዚያው ቆየ፡፡
41ሰለሞን ያደረገው ሌላው ነገር፣ ያከናወነው ተግባርና ጥበቡ ሁሉ በሰለሞን የታሪክ መጽሐፍ የተመዘገበ አይደለምን?
42ሰለሞንም በኢየሩሳሌም በመላው እስራኤል ላይ የነገሠበት ዘመን አርባ ዓመት ነበር፡፡
43ከዚህ በኋላ ሰለሞን ሞተ፣ በአባቱ በዳዊት ከተማም ተቀበረ፤ ልጁም ሮብዓም በአባቱ በሰለሞን ተተክቶ ነገሠ፡፡