መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

1ኛ ዬሐንስ 4

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ወዳጆች ሆይ! መንፈስን ሁሉ አትመኑ፣ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር መሆናቸውን መርምሩ፣ ምክንያቱም ብዙ ሃሰተኛ ነቢያት ወደ ዓለም ገብተዋል፡፡
2የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ እናውቃለን፣- ጌታ ኢየሱስ በሥጋ እንደመጣ የሚቀበል መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው።
3ኢየሱስን የማይቀበል መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም። ይህ እንደሚመጣ የሰማችሁት የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ ነው፣ አሁን እንኳ በዓለም ውስጥ አለ፡፡
4የተወደዳችሁ ልጆች! እናንተ ከእግዚአብሔር ስለሆናችሁ፣ እነዚህን መናፍስት አሸንፋችኋል፣ ምክንያቱም በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ይበልጣል፡፡
5እነዚህ መናፍስት ከዓለም ናቸው፣ስለሆነም የሚናገሩት ሁሉ የዓለምን ነው፣ዓለምም ይሰማቸዋል፡፡
6እኛ ከእግዚአብሔር ነን። እግዚአብሔርን የሚያውቅ ይሰማናል። ከእግዚአብሔር ያልሆነ ግን አይሰማንም። በዚህም የእውነት መንፈስንና ፣የስህተትን መንፈስን እናውቃለን፡፡
7ወዳጆች ሆይ! እርስ በርስ እንዋደድ፣ምክንያቱም ፍቅር ከእግዚአብሔር ነውና፣ ፍቅር ያለው ከእግዚአብሔር ተወልዷል፣ እግዚአብሔርንም ያውቃል፡፡
8ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፣እግዚአብሔር ፍቅር ነውና፡፡
9በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በመካከላችን ተገልጧል፣ እግዚአብሔር በርሱ እንድንኖር ፣አንድ ልጁን ወደ ዓለም ላከው፡፡
10ፍቅር እንደዚህ ነው፣እግዚአብሔርን ስለወደድነው ሳይሆን፣ እርሱ ስለወደደን ለኃጢያታችን ማስተሰረያ እንዲሆን ልጁን ላከ፡፡
11ወዳጆች ሆይ! እግዚአብሔር ይህን ያህል ከወደደን፣እኛም እርስ በርሳችን መዋደድ ይገባናል።
12ማንም እግዚአብሔርን አላየውም። እርስ በርሳችን ብንዋደድ፣ እግዚአብሔር በኛ ይኖራል፣ ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ይሆናል፡፡
13መንፈሱን ሰጥቶናልና፣ በዚህም እኛ በእርሱ እንደምንኖር፣ እርሱም በኛ እንደሚኖር እናውቃለን።
14እኛም አይተናል፣እግዚአብሔር ልጁን የዓለም አዳኝ አድርጐ እንደላከውም እንመሰክራለን፡፡
15ማንም ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ቢቀበል፣ እግዚአብሔር በርሱ ይኖራል ፤እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል፡፡
16እኛም እግዚአብሔር ለኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል ደግሞም አምነናል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፣ በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል፣እግዚአብሔርም በርሱ ይኖራል፡፡
17በፍርድ ቀን ድፍረት እንዲኖረን፣ይህም ፍቅር በመካከላችን ተፈጸሟል፣ እኛም በዚህ ዓለም እንደ እርሱ ነን ፡፡
18በፍቅር ፍርሃት የለም። ነገር ግን ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል፣ ምክንያቱም ፍርሃት የሚያመለክተው ቅጣት መኖሩን ነው። የሚፈራ ግን ፍቅሩ ፍፁም አይደለም፡፡
19አስቀድሞእግዚአብሔር ወዶናልና፣እኛም እንወደዋለን።
20አንድ ሰው "እግዚአብሔርን እወዳለሁ" እያለ ወንድሙን ግን ቢጠላ ሃሰተኛ ነው፤የሚያየውን ወንድሙን የማይወድ፣ የማያየውን እግዚአብሔርን ሊወድ አይችልም።
21እግዚአብሔርን የሚወድ ወንድሙን መውደድ አለበት፣የሚል ትእዛዝ ከእግዚአብሔር ተቀብለናል።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።