መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

1ኛ ዬሐንስ 3

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ፣አብ የሰጠን ፍቅር ፣ምን ዓይነት እንደሆነ አስተውሉ ፤ እኛም ልክ እንደዛው ነን! በዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን እንደማያውቀው እኛንም አያውቀንም።
2የተወደዳችሁ፣አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፤ ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ እርሱን እንደምንመስል እናውቃለን፤ምክንያቱም ትክክለኛ ማንንነቱን እናየዋለን።
3በእርሱም ላይ ይህ ጽኑ እምነት ያለው ሁሉ፣ እርሱ ንፁህ እንደሆነ ራሱን ያነፃል፡፡
4ኃጢያትን የሚሠራ ሁሉ ዐመጽን ያደርጋል፣ ኃጢአትም ዐመጽ ነው፡፡
5ኃጢያትን ለማስወገድ ክርስቶስ እንደተገለፀ ታውቃላችሁ፣ በእርሱም ኃጢያት የለም፡፡
6በእርሱ የሚኖር ኃጢያት አያደርግም፡፡ ኃጢያት የሚያደርግ እርሱን አላየውም ወይም አላወቀውም፡፡
7የተወደዳችሁ ልጆች፣ ማንም አያስታችሁ፡፡ ክርስቶስ ፃድቅ እንደሆነ ሁሉ፣ ፅድቅን የሚያደርግ ፃድቅ ነው።
8ኃጢያት የሚያደርግ ከዲያብሎስ ነው፤ምክንያቱም ዲያብሎስ ከመጀመሪያው ኃጢያት አድርጓል፡፡ በዚህም ምንክያት የዲያብሎስን ሥራ ለማፍረስ ፣የእግዚአብሔር ልጅ ተገልጧል፡፡
9የእግዚአብሔር ዘር በርሱ ስለሚኖር ፣ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢያትን አያደርግም፤ ከእግዚአብሔር ተወልዷልና ኃጢያትን ሊያደርግም አይችልም።
10በዚህም የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች ይታወቃሉ፡፡ ፅድቅን የማያደርግ ወይም ወንድሙን የማይወድ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፡፡
11ከመጀመሪያው የሰማችኋት መልእክት፣ይህ እርስ በርሳችን እንድንዋደድ የሚለው ነው።
12ክፉ እንደሆነውና ወንድሙን እንደ ገደለው እንደ ቃየል አይደለም። የገደለው ለምንድን ነው? ምክንያቱ የራሱ ሥራ ክፉ፣ የወንድሙ ጽድቅ ስለነበረ ነው፡፡
13ወንድሞች፣ ዓለም ቢጠላችሁ፣አትደነቁ።
14ወንድሞችን ስለምንወድ ፣ከሞት ወደ ህይወት እንደተሻገርን እናውቃለን። ፍቅር የሌለው በሞት ውስጥ ይኖራል፡፡
15ወንድሙን የሚጠላ ነፍሰ ገዳይ ነው፡፡ ነፍሰ ገዳይ የሆነ ሁሉ፣ በውስጡ የዘላለም ህይወት እንደሌለው ታውቃላችሁ፡፡
16ክርስቶስ ለእኛ ህይወቱን ሰጥቷልና፣በዚህ ፍቅርን እናውቃለን።እኛም ለወንድሞቻችን ህይወታችንን አሳልፈን መስጠት ይገባናል።
17ነገር ግን ማንም የዚህ ዓለም ንብረት ያለውና፣ወንድሙም የሚያስፈልገውን አውቆ፣ባይራራለት፣ እንዴት የእግዚአብሔር ፍቅር በርሱ ይኖራል?
18የተወደዳችሁ ልጆቼ ፣በሥራና በእውነት እንጂ ፣በቃል ወይም በአንደበት አንዋደድ።
19በዚህም ከእውነት እንደሆንንና፣ልባችንም በፊቱ ትክክል እንደሆነ እናረጋግጣለን።
20ልባችን ግን የሚፈርድብን ከሆነ፣ እግዚአብሔር ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነው፣ሁሉንም ያውቃል፡፡
21ወዳጆች ሆይ! ልባችን የማይፈርድብን ከሆነ፣በእግዚአብሔር ፊት ድፍረት አለን።
22ትዕዛዙን የምንጠብቅና፣በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን የምናደርግ ስለሆነ፣ የምንለምነውንና ሁሉ እንቀበላለን፡፡
23የርሱም ትዕዛዙ፣በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንድናምንና፣ ትእዛዙን እንደሰጠን እንደዚያው እርስ በርስ እንድንዋደድ ነው፡፡
24የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ የሚጠብቅ ፣በርሱ ይኖራል እግዚአብሔርም በርሱ ይኖራል፡፡በዚህም በሰጠን በመንፈሱ፣ በእኛ ውስጥ እንደሚኖር እናውቃለን።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።