መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

1ኛ ዬሐንስ 5

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ሆነ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዷል።አባት የሆነውን የሚወድ ሁሉ፣ከርሱ የተወለደውን ደግሞ ይወዳል።
2እግዚአብሔርን ስንወድና ትዕዛዙን ስንፈጽም፣ የእግዚአብሔርን ልጆች እንደምንወድ በዚህ እናውቃለን።
3እግዚአብሔርን የምንወደው የርሱን ትእዛዙን በመጠበቃችን ነው። የርሱም ትእዛዛት ከባዶች አይደሉም።
4ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋል። ዓለምን የሚያሽንፈው እምነታችን ነው።
5ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ከሚያምን በቀር፣ ዓለምን የሚየሸንፍ ማነው?
6በውሃና በደም የመጣው እርሱም ነው፣እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ፣ በውሃ ብቻ ሳይሆን፣ነገር ግን በውሃና በደም የመጣ ነው።
7-8የጥንቶችቹ የተሻሉት ቅጅዎች ይተውታል። ሦሶት ምስክሮች አሉ፤እነርሱም መንፈሱ ፣ውሃውና ደሙ ናቸው፤ሦስቱም በአንድ ይስማማሉ።
9የሰዎችን ምስክርነት የምንቀበል ከሆነ፣ የእግዚአብሔር ምስክርነት ደግሞ የበለጠ ነው። እግዚአብሔር ስለ ጁል የሰጠው ምስክር ይህ ነው።
10በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በውስጡ ምስክር አለው። በእግዚአብሔር የማያምን ፣እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረውን ምስክር ስለማያምን ሐሰተኛ አድርጎታል።
11ምስክሩም ይህ ነው ፣እግዚአብሔር የዘላለምን ህይወት እንደሰጥንና፣ይህም ህይወት በልጁ መሆኑ ነው።
12ልጁ ያለው ሕይወት አለው፥ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።
13በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ፣የዘላለም ህይወት እንዳላችሁ እንድታውቁ ፣እነዚህን ነገሮች እጽፍላችኋለሁ።
14በእርሱ ፊት ያለን ድፍረት ይህ ነው፣እንደ ፈቃዱ ማንኛውንም ነገር ብንጠይቀው፣ይሰማናል።
15የምንጠይቀውን ሁሉ እንደሚሰማን ካወቅን፣ከርሱ የጠየቅነውን ሁሉ እንደተቀበልን እናውቃለን።
16ማንም ወንድሙ ለሞት የማያበቃ ሃጢዓት ሲያደርግ ቢያይ፣ መጸለይ ይገባዋል፣ሞት የማይገባውን ሃጢዓት ለሚያደርጉት እግዚአብሔር ህይወትን ይሰጣል። ለሞት የሚያበቃ ኃጢዓት አለ። ያንን የተመለከተ ልመና እንዲያደርግ አላልኩም።
17ዓመጽ ሁሉ ኃጢዓት ነው፣ ነገር ግን ለሞት የማያበቃ ኃጢዓት አለ።
18ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢዓት እንደማያደርግ እናውቃለን፣ከእግዚአብሔር የተወለደውን፣እግዚአብሔር ከክፉ ይጠብቀዋል ፣ክፉውም አይነካውም።
19እኛ ከእግዚአብሔር እንደሆንን፣ዓለም ሁሉ በክፉው ቁጥጥር ሥር እንደሆነ እናውቃለን።
20እኛ ግን የእግዚአብሔር ልጅ እንደመጣና እውነት የሆነውን እንድናውቅ ማስተዋል እንደሰጠን እናውቃለን፤ እኛም እውነት በሆነው በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ እንዳለን እናውቃለን። እርሱም እውነተኛ አምላክና የዘላለም ህይወት ነው።
21ልጆች ሆይ! ከጣዖታት ዓምልኮ ራሳችሁን ጠብቁ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።