1የተወደዳችሁ ልጆቼ ፣ሃጢያት እንዳታደርጉ ይህን እፅፍላችኋላሁ። ግን ማንም ሃጢያት ቢያደርግ ፣ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን ፤እርሱም ፃድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፡፡
2እርሱ የእኛ ብቻ ሳይሆን፣ የዓለሙም ሁሉ ሃጢዓት ማስተስረያ ነው፣፡፡
3ትዕእዛዙን የምንጠብቅ ከሆነ ፣በዚህ እርሱን እንዳወቅነው እናውቃለን።
4"እግዚአብሔርን አውቀዋለሁ" የሚል ፣ግን ትዕዛዛቱን የማይጠብቅ፣ ውሸታም ነው ፣እውነትም በውስጡ የለም፡፡
5ሆኖም ማንም ቃሉን ቢጠብቅ፣ በርግርጥ በዚያ ሰው ለእግዚአብሔር ያለው ፍቅር ተገልጧል፤ በዚህም በእርሱ እንደሆንን እናውቃለን።
6በእግዚአብሔር እኖራለሁ የሚል ፣ኢየሱስ ክርስቶስ እንደኖረ መኖር አለበት።
7የተወደዳችሁ፣የምጽፍላችሁ በመጀመሪያ የነበረውን አሮጌ ትዕዛዝ እንጂ አዲስ ትዕዛዝ አይደለም።አሮጌውም ትእዛዝ የሰማችሁት ቃል ነው፡፡
8ሆኖ በክርስቶስና በናንተ እውነት የሆነውን አዲሱን ትእዛዝ እጽፍላችኋለሁ።ምክንያቱም ጨለማው አልፎ እውነተኛው ብርሃን እያበራ ነው።
9በብርሃን አለሁ እያለ ፣ወንድሙን ግን የሚጠላ ፣አሁንም እንኳ በጨለማ ውስጥ ነው፡፡
10ወንድሙን የሚወድ በብርሃን ይኖራል። የሚያሰናክል ሁኔታም የለም፡፡
11ወንድሙን የሚጠላ በጨለማ ውስጥ ነው፣ በጨለማም ይኖራል፤ ወዴት እንደሚሄድም አያውቅም ፣ምክንያቱም ጨለማው ዓይኖች አሳውሮታል፡፡
12ልጆች ሆይ! ኃጢያታችሁ በክርስቶስ ስም ይቅር ስለተባለ እፅፍላችኋለሁ፡፡
13አባቶች ሆይ! ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃኋልና እጽፍላችኋለሁ። ወጣቶች ሆይ! ክፉውን ስላሸነፋችሁ እጽፍላችኋለሁ፡፡ ታናናሽ ልጆች ሆይ! አብን ስላወቃችሁ እጽፍላችኋለሁ፡፡
14አባቶችሆይ! ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ። ወጣቶች ሆይ! ብርቱዎች ስለሆናቹ ፣የእግዚአብሔርም ቃል በእናንተ ስለሚኖር፣ ክፉውንም አሸንፋችኋልና እጽፍላችኋለሁ፡፡
15ዓለምን ወይም በዓለም ያሉት ነገሮች አትውደዱ። ማንም ዓለምን ቢወድ የአብ ፍቅር በርሱ ውስጥ የለም፡፡
16በዓለም ያለው ሁሉ፣ የሥጋ ምኞት፣ የዓይን አምሮትና ትምክህት ከዓለም እንጂ ከአብ አይደሉም፡፡
17ዓለሙና ምኞቱም ያልፋሉ፣የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል፡፡
18ታናናሾች ልጆች ሆይ! የክርስቶስ ተቀዋሚ ስለመምጣቱ እንደሰማችሁት ፣ይህ የመጨረሻው ሰዓት ነው፡፡ አሁንም እንኳ፣ ብዙ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች መጥተዋል፡፡
19ከእኛው መካከል ወጥተዋል ፣ከእኛ ወገን ግን አልነበሩም። ከእኛ ወገን ቢሆኑ ኖሮ፣ ከእኛ ጋር ፀንተው ይኖሩ ነበር። ሆኖም ከእኛ ወገን እንዳልነበሩ እንዲገለጥ ወጡ።
20እናንት ግን፣ከቅዱሱ የተቀበላችሁት ቅባት ስላላችሁ፣ሁላችሁም እውነትን ታውቃላችሁ።
21የምጽፍላችሁ እውነትን ስለማታውቁ አይደለም፤ነገር ግን ስለምታውቁትና፣ በእውነትም ምንም ሃሰት ስለሌለ ነው።
22ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን ከሚክድ በስተቀር ሃሰተኛ ማነው ነው? አብና ወልድን ስለሚክድ፣እንዲህ ዓይነት ሰው የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው።
23ወልድን የሚክድ ሁሉ አብ የለውም፤ ወልድንን የሚያውቅ አብም ደግሞ አለው።
24እናንተ ግን ፣ከመጀመሪያው የሰማችሁት በውስጣችሁ ይኑር። ከመጀመሪያ የሰማችሁት፣በእናንተ ቢኖር፣እናንተም በወልድና በአብ ትኖራላችሁ።
25እርሱ የሰጠን ተስፋ ይህ ነው፤ እርሱም የዘላለም ሕይወት ነው።
26የሚያስቷችሁን በተመለከተ ፣ ይህን ፅፌላችኋለሁ፡፡
27እናንተ ግን የተቀበለች ቅባት በእናንተ ስለሚኖር ፣ማንም እንዲያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም። የርሱም ቅባት ስለ ሁሉም ነገሮች እውነት እንጂ ሃሰት ስለማያስተምራችሁ ፣ እንደተማራችሁት በርሱ ኑሩ፡፡
28አሁንም የተወዳዳችሁ ልጆች፣ በሚገለጥበለት ጊዜ ድፍረት እንዲኖረንና ፣በመምጣቱም እንዳናፍር በእርሱ ኑሩ፡፡
29እርሱ ፃድቅ እንደሆነ ካወቃችሁ ፣ፅድቅን የሚያደርግ ሁሉ ከርሱ እንደተወለደ ታውቃላችሁ፡፡