መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

1ኛ ዬሐንስ 1

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከመጀመሪያው ስለ ነበረው፣ ስለ ሰማነው፣ በዓይኖቻች ስላየነው፣ ስለ ተመለከትነው ፣በእጆቻችንም ስለ ዳሰስነው ስለ ህይወት ቃል
2ህይወትም ተገልጦ ነበር ፤እኛም አይተናል፣ምስክሮችም ነን፤ በአብ ዘንድ ስለ ነበረው ለእኛም ስለ ተገለጠው፣ የዘላለም ሕይወት እንናገራለን፤
3ከእኛም ጋር ህብረት እንዲኖራቸሁ፣ ያየነውንና የሰማነውን እንነግራችኋለን፤ ህብረታችንም ከአብና፣ ከልጁ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው፡፡
4ደስታችሁም ሙሉ እንዲሆን ፣እነዚህን ነገሮች እንጽፍላችኋለን።
5ከእርሱ የሰማነው፣ለናንተም የምንነግራችሁ መልዕክት፣ እግዚአብሔር ብርሃን ነው፤ በእርሱም ምንም ጨለማ የለም፤ የሚል ነው፡፡
6ከእርሱ ጋር ህብረት አለን እያልን፣ ነገር ግን በጨለማ ውስጥ ብንመላለስ፣እንዋሻለን ፣እውነትንም አናደርግም፡፡
7እርሱ ብርሃን እንደሆነ ፣ በብርሃን ብንመለላለስ እርስ በርሳችን ህብረት ይኖረናል፡፡የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስም ደም ከሃጢአት ሁሉ ያነጻናል።
8ሃጢያት የለብንም ብንል፣ ራሳችንን እናስታለን፣ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።
9ነገር ግን ሃጢያታችንን ብንናዘዝ፣ሃጢያታችንን ይቅር ሊለንና ከዓመጽ ሁሉ ሊያነጻን፣ የታመነና ፃድቅ ነው፡፡
10ሃጢአት አላደረግንም ብንል፣ ሃሰተኛ እናደርገዋለን፣ ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።