መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

1ኛ ቆሮንቶስ 9

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እኔ ነፃ አይደለሁም? እኔ ሐዋርያስ አይደለሁም? ጌታችን ኢየሱስን አላየሁትም? እናንተስ በጌታ የሥዬ ፍሬዎች አይደላችሁም?
2ለሌሎች ሐዋርያ ባልሆን እንኳ ቢያንስ ለእናንተ ሐዋርያ ነኝ። በጌታ ሐዋርያ ለመሆኔ እናንተ ማረጋገጫ ናችሁና።
3ለሚጠይቁኝ መልሴ ይህ ነው።
4እኛስ ለመብላትና ለመጠጣት መብት የለንም?
5እንደ ሌሎቹ ሐዋርያት፣ እንደ ጌታ ወንድሞች፣ እና እንደ ኬፋ፣ አማኝ የሆነች ሚስት ይዞ ለመሄድ መብት የለንም?
6ወይስ የመሥራት ግዴታ ያለብን እኔና በርናባስ ብቻ ነን?
7በራሱ ወጪ በውትድርና የሚያገለግል ማን ነው? የወይን ተክል ተክሎ ከፍሬው የማይበላ ማን ነው? ወይስ ከሚጠብቀው መንጋ ወተት የማይጠጣ ማን ነው?
8እነዚህን ነገሮች የምናገረው በሰው ሥልጣን መሠረት ነው? ሕጉስ ይህን አይልም?
9በሙሴ ሕግ፦ "የሚያበራየውን በሬ፣አፉን አትሰር" ተብሎ ተጽፎአል። በእርግጥ እግዚአብሔር ስለ በሬዎች አስቦ ነው?
10እየተናገረ ያለው ስለ እኛ አይደለም? የተጸፈው ስለ እኛ ነው፣ምክንያቱም የሚያርስ በተስፋ ሊያርስ፣የሚያበራይም ከመከሩ ለመካፈል ተስፋ በማድረግ ሊያበራይ ይገባዋል።
11በመካከላችሁ መንፈሳዊ ነገር ዘርተን ከሆነ፣ከእናንተ ቁሳዊ ነገሮችን ብናጭድ ይበዛብናል?
12ሌሎች ይህን መብት ከእናንተ የሚያገኙ ከሆነ፣እኛስ የበለጠ መብት የለንም? ሆኖም ግን ይህን መብት ይገባናል አላልንም፣ይልቁንም ለክርስቶስ ወንጌል እንቅፋት እንዳንሆን ሁሉን ታገስን።
13በመቅደስ የሚያገለግሉ ምግባቸውን ከመቅደስ እንደሚያገኙ አታውቁም፣በመሠዊያው ላይ የሚያገልግሉስ መሠዊያው ላይ ከሚሠዋው እንደሚካፈሉ አታውቁም?
14እንዲሁም ደግሞ ወንጌልን የሚያውጁ ከወንጌል በሚገኝ እንዲኖሩ ጌታ አዟል።
15እኔ ግን ከእነዚህ መብቶች አንዱንም ይገባኛል አላልሁም። ይህንንም የጻፍሁት አንዳች እንዲደረግልኝ አይደለም። ይህን ትምክህቴን ማንም ከሚወስድብኝ ሞትን እመርጣለሁ።
16ይህ ግዴታዬ ስለሆነ ወንጌል ብሰብክ የምታበይበት ምክንያት የለኝም፣ ወንጌልን ባልሰብክ ግን ወዮልኝ!
17ይህን በፈቃደኝነት ባደርገው ግን ሽልማት አለኝ። በፈቃደኝነት ባላደርገው ግን በአደራ የተሰጠኝ ኃላፊነት አለብኝ።
18ታዲያ ሽልማቴ ምንድነው? በወንጌል ውስጥ ያለ ሙሉ መብቴን ትቼ ያለምንም ክፍያ ወንጌልን ስሰብክ ነው።
19ምንም እንኳ ከሁሉም ነፃ ብሆንም፣ ብዙዎችን ለመማረክ እንድችል፣የሁሉ አገልጋይ ሆንሁ።
20አይሁድን ለመማረክ እንድችል፣ እንደ አይሁዳዊ ሆንሁ። ምንም እንኳ በሕግ ስር ባልሆንም፣ በሕግ ስር ያሉትን መማረክ እንድችል፣ ከሕግ ስር እንዳለ ሰው ሆንሁ።
21ከሕግ ውጭ ያሉትን መማረክ እንድችል፣እኔ ራሴ ከእግዚአብሔር ሕግ ውጭ ሳልሆን፣ ነገር ግን ከክርስቶስ ሕግ ስር እያለሁ፣ ከሕግ ውጭ እንዳለ ሰው ሆንሁ።
22ደካማውን መማረክ እንድችል፣እንደ ደካማ ሆንሁ። አንዳንዶችን ማዳን እንድችል፣ ለሰዎች ሁሉ ብዬ ሁሉን ሆንሁ።
23ይህን ሁሉ ያደረግሁት ከወንጌል በረከት መካፈል እንድችል፣ ስለ ወንጌል ብዬ ነው።
24በሩጫ ውድድር የሚሳተፉ ሯጮች ሁሉ እንደሚሮጡ፣ ነገር ግን ሽልማት የሚቀበል አንዱ ብቻ እንደሆነ አታውቁም? ስለዚህ ሽልማት ለማግኘት ሩጡ።
25ለውድድር የሚዘጋጅ ሰው ሥልጠና ጊዜ ሁሉ ራሱን መቆጣጠር ይለማመዳል። እነርሱ የሚጠፋውን ሽልማት ለማግኘት ይሮጣሉ፣ እኛ ግን የማይጠፋውን ሽልማት ለማግኘት እንሮጣለን።
26ስለዚህም ያለ ዓላማ አልሮጥም፣ወይም ንፋስ በቦክስ አልመታም።
27ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ከውድድሩ ውጭ እንዳልሆን ሥጋዬን በመቆጣጠር አስገዛዋለሁ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።