1ለጣዖት ስለተሰዋ ሥጋ፦ "ሁላችንም ዕውቀት እንዳለን" እናውቃለን።ዕውቀት ያስታብያል፤ ፍቅር ግን ያንጻል።
2አንድ ሰው አንድ ነገር እንደሚያውቅ ቢያስብ፥ ያ ሰው ፥እንደሚገባ እንደሚያውቅ ገና አለወቀም።
3ነገር ግን ማንም ሰው እግዚአብሔርን ቢወድ እርሱም በእግዚአብሔር ዘንድ ይታወቃል።
4እንግዲህ ለጣዖት የተሠዋውን ሥጋ ስለ መብላት በተመለከተ፦ "የዚህ ዓለም ጣዖት ከንቱ ነው፤" እና "ከአንዱም ከእግዚአብሔር በቀር ሌላ አምላክ የለም" ይህንን እናውቃለን።
5ብዙ "አማልክትና ጌቶች" እንዳሉ ሁሉ፥ ምንም እንኳ በሰማይና በምድር አማልክት የተባሉ ቢኖሩ ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ
6እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ ብቻ አለን፤ እንዲሁም ነገር ሁሉም በእርሱ በኩል የሆነ እኛም በእርሱ በኩል የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ አለን።
7ይሁን እንጂ ይህ ዕውቀት በሁሉም አይገኝም። በዚህ ፈንታ፥ አንዳንዶች ግን እስካሁን ድረስ ጣዖትን ማምለክ ስለ ለመዱ፦ ለጣዖት እንደ ተሠዋ አድርገው ይበላሉ። ሕሊናቸው ደካማ ስለ ሆነ ይረክሳሉ።
8መብል ግን ወደ እግዚአብሔር አያደርሰንም። ስላልበላምንም አንረክስም፤ ወይም ስለበላንም የተሻለን አንሆንም።
9ነገር ግን ይህ ነጻነታችሁ በእምነት ደካማ ለሆኑት ምክንያት ሆኖ መሰናከያ እንዳይሆን ተጠንቃቁ።
10አንተ ዕውቀት ያለህ በጣዖት ቤት በማዕድ ተቀምጠህ ስትበላ አንድ ሰው ቢያይህ፤ በእምነቱ ያልጠነከረ ሰው ለጣዖት የተሠዋውን ለመብላት አይደፋፈርምን?
11ስለ ጣዖት ባሕርይ በአንተ ዕውቀት የተነሣ ክርስቶስ የሞተላቸው ደካማ ወንድም ወይም እህት ይጠፋሉ።
12ስለዚህም ወንድሞችንና እህቶችን ስትበድሉና ደካማ ሕሊናቸውንም ስታቆሽሹ ክርስቶስን ትበድላላችሁ።
13ስለዚህም መብል ወንድሜንና እህቴን የሚያሰናክል ከሆን ወንድሜንና እህት እንዳላሰናክል ለዘላለ ከቶ ሥጋን አልበለም።