1ወንድሞች እና እህቶች፣ይህን እንድታውቁ እወዳለሁ፣አባቶቻችን ከዳመና በታች እና በባሕር ውስጥ አለፉ።
2ሁሉም በዳመና እና በባሕር ውስጥ በሙሴ ተጠመቁ፣
3መንፈሳዊ ምግብ ተመገቡ፣
4ሁሉም አንድ ዓይነት መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ። እነርሱም ይከተላቸው ከነበረው መንፈሳዊ ዓለት ጠጡ፣ያም ዓለት ክርስቶስ ነበር።
5ነገር ግን እግዚአብሔር በብዙዎች አልተደሰተምና ሬሳቸው ምድረ በዳ ውስጥ ወድቆ ቀረ።
6እኛም እነርሱ እንዳደረጉት ክፉ ነገር እንዳንመኝ እነዚህ ነገሮች ምሳሌ እንዲሆኑልን ተጽፈውልናል።
7"ሕዝቡ ሊበሉና ሊጠጡ ተቀመጡ፣በዝሙት ፍላጎት በመነሳሳት ሊጨፍሩ ተነሡ።" ተብሎ እንደተጻፈ፣ከእነርሱ አንዳንዶች እንዳደረጉት ጣዖት አምላኪዎች አትሁኑ።
8ከእነርሱ ብዙዎች ዝሙት በመፈጸማቸው ምክንያት ሃያ ሦስት ሺ ሰዎች በአንድ ቀን እንደሞቱ፣እኛም ዝሙት አንፈጽም።
9ከእነርሱም ብዙዎች ክርስቶስን እንደፈተኑት እና በእባብ እንደጠፉ፣እኛም ጌታን እንፈታተን።
10በማጉረምረማቸው ምክንያት የሞት መልአክ እንዳጠፋቸው፣እኛም አናጉረምርም።
11በእነርሱ ላይ የሆኑት እነኚህ ነገሮች ምሳሌ እንዲሆኑልን የተጻፈው፣ የዘመን ፍጻሜ ለደረሰብን ለእኛ ትምህርት እንዲሆንልን ነው።
12ስለዚህ ማንም ቆሜአለሁ ብሎ የሚያስብ፣ እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ።
13በሰው ሁሉ ላይ ከሚደርሰው በላይ የሆነ ፈተና አልደረሰባችሁም። ነገር ግን እግዚአብሔር ታማኝ ነውና ከምትችሉት በላይ እንድትፈተኑ አያደርግም። ይልቁን ፈተናውን መወጣት እንድትችሉ ከፈተናው ጋር ማምለጫ መንገዱንም ያዘጋጅላችኋል።
14ስለዚህ ወዳጆቼ ሆይ፣ከጣዖት አምልኮ ሽሹ።
15ይህን የምናገራችሁ አስተዋዮች በመሆናችሁ ነው፤የምለውን አመዛዝኑ።
16የምንባርከው የበረከት ጽዋ፣የክርስቶስን ደም መካፈል አይደለም? የምንቆርሰው እንጀራ የክርስቶስን ሥጋ መካፈል አይደለም?
17እንጀራው አንድ እንደሆነ፣ብዙዎች ሆነን ሳለ አንዱን እንጀራ በመካፈል አንድ አካል ነን።
18የእስራኤልን ሕዝብ ተመልከቱ፦ ከመሥዋዕቱ የሚበሉ ከመሠዊያው ተካፋዮች አይደሉም?
19ስለዚህ ምን እያልሁ ነው? ጣዖት ምንም አይደለም እያልሁ ነው? ወይስ ለጣዖት የተሠዋ ምግብ ምንም አይደለም ማለቴ ነው?
20እያልሁ ያለሁት፣አሕዛብ የሚሠዋቸው ነገሮች፣ለአጋንንት እንጂ ለእግዚአብሔር አይደለም። ከአጋንንት ጋር ተካፋዮች እንድትሆኑ አልፈልግም! የጌታንም ጽዋ፣ የአጋንንትንም ጽዋ ልትጠጡ አትችሉም።
21በጌታም ማዕድ፣ በአጋንንትም ማዕድ ኅብረት ልታደርጉ አትችሉም።
22ይህን ብማድረግ ጌታን ለቅናት እናነሳሳዋለን? ከእርሱ የምንበረታ ነን?
23"ሁሉም ነገር ተፈቅዷል፣" ነገር ግን ሁሉም ነገር የሚጠቅም አይደልም። "ሁሉም ነገር ተፈቅዷል፣" ነገር ግን ሁሉም ነገር ሰዎችን የሚያንጽ አይደለም።
24ማንም ለራሱ መልካም የሆንውን ብቻ አያስብ። ይልቁን፣እያንዳንዱ ለሌሎች ሰዎች ሁሉ መልካም የሆነውን ይፈልግ።
25በገበያ ቦታ የሚሸጥ ማንኛውንም ነገር፣የኅሊና ጥያቄ ሳታነሱ መብላት ትችላላችሁ።
26"ምድርና በውስጧ ያለው ሁሉ የጌታ ነውና።"
27አንድ አማኝ ያልሆነ ሰው ምግብ ቢጋብዛችሁና ግብዣውን ተቀብላችሁ መሄድ ብትፈልጉ፣ በፊታችሁ የቀረበላችሁን ማንኛውንም ነገር የኅሊና ጥያቄ ሳታነሱ ብሉ።
28ነገር ግን እንድ ሰው፣"ይህ ምግብ ለጣዖት የተሠዋ ነው።" ብሎ ቢነግራችሁ አትብሉ። ይህን ማድረግ የሚገባችሁ፣ ለነገራችሁ ሰው እና ለኅሊና ስትሉ ነው።
29ይህን ስል ስለ እናንተ ኅሊና ሳይሆን ስለ ሌላው ሰው ኅሊና ነው። ስለ ሌላው ኅሊና ሲባል ለምን በነፃነቴ ላይ ይፈረዳል?
30ምግቡን በአክብሮት ከተቀበልሁ፣አመስግኜ ለበላሁት ነገር ለምን እሰደባልሁ?
31ስለዚህ፣ስትበሉ እና ስትጠጡ፣ወይም በምታደርጉት ሁሉ፣ሁሉን ለጌታ ክብር አድርጉት።
32ለአይሁዶች ወይም ለግሪኮች፣ እንዲሁም ለእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን መሰናከያ አታድርጉ።
33እኔ ሰዎችን ሁሉ በሁሉ ነገር ደስ ለማሰኘት እንደምፈልግ ሁሉ እናንተም እንዲሁ አድርጉ። የራሴን ጥቅም ሳይሆን፣ለብዙዎች ጥቅም የሚሆነውን እፈልጋለሁ። ይህን የማደርገው ወደ ድነት እንዲመጡ ብዬ ነው።