መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

1ኛ ቆሮንቶስ 7

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እንግዲህ ስለጻፋችሁኝ ነገር ሰው ከሴት ጋር አለመገናኘት መልካም ነው።
2ነገር ግን ስለ ዝሙት ፈተና ምክንያት እንዳይሆን እያንዳንዱ ሰው የራሱ ሚስት ይኑረው፤ እንዲሁም ለእያንዳንዱ ሴት የራስዋ ባል ይኑራት።
3ባል ለሚስቱ የሚገባትን ያድርግላት፤ እንደዚሁም ደግሞ ሚስቲቱ ለባልዋ የሚገባትን ታድርግ።
4ሚስት በገዛ ሰውነትዋ ላይ ሥልጣን ያላትም፤ ሥልጣን ለባልዋ ነው እንጂ፤ እንዲሁም ባል በገዛ ሰውነቱ ላይ ሥልጣን የላውም ሥልጣን ለሚስቱ ነው እንጂ።
5በጸሎት ለመትጋት ተስማምታችሁ ለጊዜው ካልሆነ በቀር እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ። ራሳችሁን ስለ አለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ ደግሞ አብራችሁ መሆን ትችላላችሁ።
6ዳሩ ግን ይህን እንደ ፈቃድ እላለሁ እንጂ እንደ ትእዛዝ አይደለም።
7ሰው ሁሉ እንደ እኔ ቢሆን እወዳለሁ። ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው ለራሱ ከእግዚአብሔር የተቀበለ አንዱ አንድ ዓይነት ሌላው ሌላ ዓይነት ስጦታ አለው።
8ላላገቡትና ባሎቻቸው ለሞተባቸው ሴቶች ግን እላለሁ፦ እንደ እኔ ሳያገቡ ቢኖሩ ለእነርሱ መልካም ነው።
9ነገር ግን ራሳቸውን መግዛት የማይችሉ ከሆነ መጋባት ይሻላል። በምኞት ከመቃጠል ይልቅ መጋባት ይሻላቸዋልና።
10ደግሞ የተጋቡትን እንዲ ብዬ አዛቸዋለሁ ይህንም እኔ ሳልሆን ጌታ ነው፦ "ሚስት ከባልዋ አትለይ፥
11ብትለይ ግን ሳታገባ ትኑር" ወይም "ከባልዋ ጋር ትታረቅ፥እንዲሁም" ባልም ሚስቱን አይፍታት።"
12ነገር ግን ሌሎችንም ጌታ ሳይሆን እኔ እላለሁ፦ ማንም ያላመነች ሚስት ያለው ወንድም፥ ከእርሱ ጋር ለመኖር ብትስማማ አይፍታት፤
13እንዲሁም ያላመነ ባል ያላት ሚስትም ብትኖር፥ ከእርስዋ ጋር ለመኖር ቢስማማ አትፍታው። ያላመነች ሚስት በአማኙ ባልዋ ተቀድሳለችል፤
14እንዲሁም ያላመነ ባል በአማኝ ሚስቱ ተቀድሶአል። አለዚያ ልጆቻቸውሁ ርኩሳን ይሆኑ ነበር፤ አሁን ግን የተቀደሱ ናቸው።
15የማያምን የትዳር ጓደኛ ግን የሚለይ ከሆነ ይለይ። እንዲህ በሚመስል ነገር ወንድም ወይም እህት በቃል ኪዳን መታሰር የለባቸውም። እግዚአብሔር ግን በሰላም እንድንኖር ጠርቶናል።
16አንቺ ሴት ባልሽን ታድኚ እንደ ሆንሽ ምን ታውቂአሽ? ወይስ አንተ ሰው ሚስትህን ታድናት እንደ ሆንህ ምን ታውቃለህ?
17እያንዳንዱ ሰው እንደተጠራው ዓለማና ጌታ በሰጠው ሕይወት ብቻ ይመላለስ። ይህ ለአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የእኔ ድንጋጌ ነው።
18ማንም ተገርዞ ወደ እምነት ተጠርቶአልን? ወደ አለመገረዝ መመለስ የለበትም። እንዲሁም ማንም ሳይገርዝ ወደ እምነት ተጠርቶአልን? መገረዝ የለበትም።
19የእግአብሔርን ትእዛዛት መጠበቅ ነው እንጂ መገረዝ ወይም አለመገረዝ የሚያመጠው ችግር የለም።
20እያንዳንዱ ሰው እግዚአብሔር ለእምነት በጠራበት ጊዜ እንደነበረ ይመላለስ።
21እግዚአብሔር ሲጠራህ ባሪያ ነበርን? ይህ ሊገድህ አይገባም። ነፃ የምትወጣ ከሆንህ ተቀበለው።
22አንድ ሰው በጌታ ባሪያ ሆኖ የተጠራ የጌታ ነፃ ሰው ነው፤ እንደዚሁም ነፃ ሆኖ ለእምነት የተጠራ የክርስቶስ ባሪያ ነው።
23በዋጋ ተገዝታችልኋልና የሰው ባሪያ አትሁኑ።
24ወድሞችና እህቶች ሆይ፤ እያንዳንዳችን በተጠራንበት እንደዚሁ ሆነን በእግዚአብሔር ዘንድ እንኑር።
25ላላገቡት የጌታ ትእዛዝ የለኝም። ነገር ግን በጌታ ምሕረት እንደ ታመነ ሰው ሆኜ የራሴን ምክር እሰጣለሁ።
26ስለዚህ ለችግር ጊዜ መፍትሔ እንዲሆን ሰው ሳያገባ መኖር ከቻለ መልካም ይመስለኛል።
27በጋብቻ ቃል ኪዳን በሚስት ታስረሃልን? እንዲህ ከሆነ ከዚህ ነፃ ለመሆን አትሻ። በበጋብቻ በሚስት አልታሰርህ ወይም ያላገባህ ነህ? ሚስትን አትሻ።
28ነገር ግን ካገባህ ኃጢአት አይሆንብህም። እንዲሁም ያላገባች ሴት ብታገባ ኃጢአት አይሆንባትም። ሆኖም ግን የሚያገቡ በኑሮአቸው ብዙ ችግር ይሆንባቸዋል፤ ከእንዲ ዓይነት ሕይወት እንድትርቁ እመኛለሁ።
29ዳሩ ግን ወንድሞ ሆይ፤ ይህን እላለሁ፤ ዘመኑ አጭር ነው። ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸ እንደሌላቸው ይኑሩ።
30የሚያላቅሱም እንደማያለቅሱ ይሁኑ፤ እንዲሁም የሚደሰቱ ደስታ እንደሌላቸው ይሁኑ፤
31ደግሞ ማንኛውንም ነገር የሚገዙ ምንም እንደሌላቸ ይሁኑ፤ በዚህች ዓለም የሚጠቀሙ በሙሉ እንደ ማይጠቀሙ ይሁኑ ምክንያቱም የዚች ዓለም አሠራር ሁሉ አላፊ ነውና።
32ነገር ግን ያለ ጭንቀት እንድትኖሩ እወዳለሁ። ያላገባው ጌታን እንዴት ደስ እንደሚያሰኘው የጌታን ነገር ያስባል።
33ያገባው ግን ሚስቱን እንዴት ደስ እንዲያሰኛት የዓለምን ነገር ያስባል፥ ልቡም ተከፍሎአልና።
34ያላገባች ሴት ወይም ድንግል በሥጋና በመንፈስ እንዴትምትቀደስ የጌታን ነገር ታስባለች። ያገባች ሴት ግን ባልዋን እንዴት ደስ እንደምታሰኘው የዓለምን ነገር ታስባለች።
35ሌላ ሸክም ሊጭንባችሁ ሳይሆን ለራሳችሁ ጥቅም ይህን እላለሁ። ያለ ምንም ጉዳት በጌታ እንድትጸኑ ስለእውነት ይህን እላለሁ።
36ዳሩ ግን ማንም ሰው ያጫትን ድንግል በአግባቡ ካልያዘ የእርስዋም ዕድሜ እየገፋ ከሄደ ሊያገባት ካሰበ ያግባት። ይህ ኃጢአት የለበትም።
37ነገር ግን አንድ ሰው ላለማግባት ቢወስንና ስሜቱንም ለመቆጣጠር ከቻለ እርስዋን ባለማግባቱ መልካም ያደርጋል።
38የእርሱንም እጮኛ የሚያገባት መልካም ያደርጋል፤እርስዋንም ለማግባት የማይመርጥ የበለጠ መልካም ያድርጋል።
39አንዲት ሴት ባልዋ በሕይወት እስካለ ድረስ ከባልዋ ጋር የታሰረች ናት። ነገር ግን ባልዋ ቢሞት በጌታ የሆነውን ብቻ ለማግባት ነጻነት አላት።
40እንደ እኔ ውሳኔ ግን ሳታገባ ብትኖር ደስተኛ ትሆናለች። እኔም የእግዚአብሔር መንፈስ ያለኝ ይመስለኛል።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።