መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

1ኛ ቆሮንቶስ 6

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከእናንተ አንድ ሰው ከሌላ ሰው ጋር ክርክር ቢኖረው፤ በቅዱሳን ፊት ስለጉዳዩ ከመነጋገር ይልቅ በማያምን ዳኛ ፊት ለመቆም ወደ ፍርድ ቤት ለመሄድ ይደፍራልን?
2ቅዱሳን በዓለም ላይ እንደሚፈርዱ አታውቁምን? በዓለም ላይ የምትፈርዱ ከሆነ፤ በትናንሽ ጉዳዮችን መፍረድ እንዴት ይሳናችኋል?
3በመላእክት ላይ እንኳ እንደምንፈርድ አታውቁምን? እንግዲህ በዚህ ዓለም ሕይወት ጉዳዮች ላይ የበለጠ ለመፍረድ እንዴት አንችልም?
4ለዕለታዊ ጠቃሚ ጉዳዮች ላይ መፍረድ ካለባችሁ በቤተ ክርስቲያን መካከል ለሚነሱ ክርክሮች የማያምኑ ሰዎችን እንዲፈርዱ ታስቀምጣላችሁን?
5አሳፍራችሁ ዘንድ ይህን እላለሁ። እንደዚህ ነውን? በወንድሞችና እህቶች መካከል ክርክሮችን ሊፈታ የሚችል አንድ አስተዋይ ሰው በእናንተ ዘንድ አይገኝምን?
6ነገር ግን አንዱ አማኝ ሌላውን አማኝ ለመክሰስ በማያምን ዳኛ ፊት ለመቆም ይሄዳልን?
7እንግዲህ በክርስቲያኖች መካከል የእርስ በርስ ማንኛውም ክርክር ቢኖርባችሁ ለእናንተ ሽንፈት ነው። ብትበደሉ አይሻልምን? ብትታለሉስ እይሻልምን?
8ነገር ግን እናንተ ወድሞቻችሁንና እህቶቻችሁን ትበድላላችሁ ታታልሉማላችሁ።
9ዓመጸኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁምን? በሐሰት አታምኑ። ዝሙት አድራጊዎች ቢሆኑ፣ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ፥ ወይም አመዝሮች ወይም ግብረ ሶዶማውዎች ቢሆኑ፤ ወይም ሌቦች፥ ወይም ስግብግቦች፤ ወይም ሰካራሞች፣ ወይም ተዳዳቢዎች፥
10ወይም ነጣቂዎች፥ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።
11ከእናንተም አንዳንዶቻችሁ እንዲሁ ነበራችሁ። ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፥ ተቀድሳችኋል፤ ጸድቃችሁማል።
12ሁሉ ተፈቅዶልኛል፤ነገር ግን ሁሉም የሚጠቅም አይደለም። ሁሉ ተፈቅዶልኛል ነገር ግን በእኔ ላይ ምንም ነገር አይሠለጥንብኝም።
13"መብል ለሆድ ነው፤ ሆድም ለመብል ነው።" እግዚአብሔር ግን ይህንም ያንም ያጠፋቸዋል። ሥጋ ግን ለጌታ ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም። ይልቁን ሥጋችንም ለጌታ ነው፤እንዲሁም ጌታ ለሥጋ ያዘጋጃል።
14እግዚአብሔርም ደግሞ ጌታን አስነሣ እኛንም በኃይሉ ያስነሣናል።ሥጋችሁ የክርስቶስ ብልቶች እንደሆነ አታውቁምን?
15እንግዲህ የክርስቶስን ብልቶች ወስጄ የሴተኛ አዳሪ ሴት ብልቶች ላድርጋቸውን? ሊሆን አይችልም።
16ከሴተኛ አዳሪ ጋር የሚተባበር ከእርስዋ ጋር አንድ ሥጋ እንዲሆን አታውቁምን? "ሁለቱ አንድ ሥጋ ይሆናሉ" በእግዚአብሔር ቃል ተጽፎአል።
17ከጌታ ጋር የሚተባበር ግን ከእርሱ ጋር አንድ መንፈስ ነው።
18ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚያደርገው ሌላ ኃጢአት ሁሉ ከሥጋ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚያደርግ ሰው ግን በገዛ ሥጋው ላይ ኃጢአትን ያድርጋል።
19ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁትና በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን?
20በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም። ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።