መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

1ኛ ቆሮንቶስ 5

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በእናንተ መካከል ዝሙት እንዳለ ሰምተናል፤የዚያም ዓይነት ዝሙት በአሕዛብ መካከል እንኳ ተሰምቶ የማይታወቅ ነው። እንደሰማነው ከእናንተ አንዱ ከእንጀራ እናቱ ጋር የሚተኛ አለ።
2ስለዚህ በትዕቢት የምትመላለሱ አይደላችሁምን? በዚህም ልታዝኑ አይገባችሁምን? ይህን ያደረገ ሰው ከመካከላችሁ ሊወገድ ይገባል።
3እኔ በአካል ከእናንተ ጋር ባልሆንም በመንፈስ ከእናንተ ጋር አለሁ፤ከእናንተም ጋር እንዳለሁ ሆኜ ይህን ባደረገው ሰው ላይ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሁን ፈርጄበታለሁ።
4እናንተ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በምትሰበሰቡበት ጊዜ መንፈሴም ከጌታችን ኢየሱስ ኃይል ጋር እዚያው በመካከላችሁ አለ።
5ይህ ሰው በጌታ በኢየሱስ ቀን ይድን ዘንድ፤ ለሥጋው ጥፋት ለሰይጣን እንዲሰጥ ፍርዴ ነው።
6መመካታችሁ መልካም አይደለም። ጥቂት እርሾ ሊጡን ሁሉ እንደሚያቦካ አታውቁምን?
7እንግዲህ እርሾ የሌለ እንጀራ ሆናችሁ አዲሱን ሊጥ ትሆኑ ዘንድ ከአሮጌው እርሾ ራሳችሁን አንጹ። ምክንያቱም የፋሲካችን በግ የሆነው ክርስቶስ ታርዶአል።
8ስለዚህ በአሮጌ እርሾ በመጥፎ አስተሳሰብና በክፋት ሳይሆን በቅንነትና በእውነት በዓልን እርሾ በሌለ ቂጣ እናድርግ።
9ዝሙትን ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር ኅብረት እንዳታደርጉ በመልእክቴ ጽፌላችሁ ነበር።
10በምንም ነገር የዚህን ዓለም ዝሙት ከሚያደርጉትን ወይም ገንዘብን ከሚመኙትን፥ ከነጣቂዎችንም፤ወይም ጣዖትን ከሚያመልኩትን ከማያምኑት አትተባበሩ። እንዲህ ቢሆን ኖሮ ከዓለም መውጣት በተገባችሁ ነበር።
11አሁን ግን በክርስቶስ ወንድሞች ወይም እህቶች ተብለው ከሚጠሩት ከማናቸውም ዝሙትን ከሚያደርግ ወይም ገንዘብን ከሚመኝ ወይም ጣኦትን ከሚያመልክ ወይም ተሳዳቢ ወይም ሰካራም ወይም ነጣቂ ቢሆኑ ከእነርርሱ ጋር እንዳትተባበሩ እጽፍላችኋለሁ። እንደነዚህ ካሉት ጋር አብራችሁ እንኳን አትብሉ።
12ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ባሉ ሰዎች ላይ ለመፍረድ እንዴት እደፍራለሁ? በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ባሉ ሰዎች ላይ እናንተ አትፈርዱምን?
13ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ባሉቱ ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል። "ክፉውን ከመካከላችሁ አውጡት።"
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።