መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

1ኛ ቆሮንቶስ 3

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ወንድሞችና እህቶች ሆይ፤ እንደ ሥጋውያን፤ በክርስቶስም እንደ ሕፃናት እንጂ መንፈሳውያን እንደ ሆናችሁ ልናገራችሁ አልቻልሁም።
2ገና ጠንካራ ምግብ ለመብላት ስላልቻላችሁ ጠንካራ ምግብ ሳይሆን ወተት ጋትኋችሁ። እስከ አሁን ስንኳ ጠንካራ ምግብ ለመብላት ገና አልበቃችሁም።
3ምክንያቱም ገና ሥጋውያን ናችሁና። ቅናትና ክርክር ስለ ሚገኝባችሁ በሥጋ ፈቃድ እየኖራችሁ አይደላችሁምን? እንደ ሰውስ ልማድ እየተመላለሳችሁ አይደለምን?
4አንዱ፦ "እኔ ጳውሎስን እከተላለሁ" እንዲሁም ሌላውም፦ "እኔ የአጵሎስ ተከታይ ነኝ" ሲል እንደ ሰዎች ልማድ መመላለሳችሁ አይደለምን?
5ታዲያ አጵሎስ ማን ነው? ጳውሎስስ ማን ነው? በእነርሱ እጅ ያመናችሁ እንደ ተሰጣቸው አገልጋዮች ናቸው።
6እኔ ተክልሁ አጽሎስም አጠጣ፤ ግን ያሳደገው እግዚአብሔር ነው።
7እንግዲህ የሚተክል ወይም የሚያጠጣ ምንም አይደለም። ነገር ግን የሚያሳድግ እግዚአብሔር ነው።
8የሚተክልና የሚያጠጣ አንድ ናቸው። እንዲሁም እያንዳንዱ እንደ ራሱ ድካም መሠረት የራሱን ደመወዝ ይቀበላል።
9ምክንያቱም ከእግዚአብሔር ጋር አብረን የምንሠራ ነን። የእግዚአብሔር እርሻ፤ የእግዚአብሔርም ሕንፃ ናችሁ። ።
10ከእግዚአብሔር በተሰጠኝ ጸጋ እንደ ዋና ሙያተኛ መሐንድስ መሠረትን ጠልሁ፤ ሌላውም ሰው በላዩ ያንጻል። እያንዳንዱ ሰው ግን በእርሱ ላይ እንዴት እንደሚያንጽ ይጠንቀቅ።
11ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልም፤ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
12ማንም ግን በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ ቢሆን፤ በብር፤ በከበረ ድንጋይ፤ በእንጨት፤ በሣር ወይም በአገዳ ቢያንጽ፤
13የእያንዳንዱ ሥራ ይገለጣል፤ የቀን ብርሃንም ይገልጠዋልና። የእያንዳንዱም ሥራ ጥራት እንዴት መሆኑን እሳቱ ይፈትነዋል።
14አንድ ሰው ማንኛውንም ነገር ያነጸው ሥራ ቢጸናለት ሽልማቱን ይቀበላል። ነገር ግን የማንም ሥራ የተቃጠለበት ከሆነ ይከስራል።
15ነገር ግን እርሱ ራሱ ከእሳት እንደሚያመልጥ ሆኖ ይድናል ።
16እናንተ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደሆናችሁ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደሚኖርባችሁ አታውቁምን?
17ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል። የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ እንደሆነ እናንተም እናንተም ቅዱሳን ናችሁ።
18ማንም ራሱን አያታልል። ከእናንተ መካከል ማንም በዚህ ዘመን ጥበበኛ እንደሆነው ቢያስብ፤ ጥበበኛ ይሆን ዘንድ እንደ ሞኝ ራሱን ይቁጠር።
19የዚህ ዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ፊት ሞኝነት ነውና። ምክንያቱም "እርሱ ጥበበኞችን በተንኮላቸው ይይዛል" ተብሎ ተጽፎአል።
20ደግሞም፦ "ጌታ የጥበበኞችን አሳብ ከንቱ እንደ ሆን ያውቃል" ተብሎ ተጽፎአል።
21ስለዚህ ማንም በሰው አይመካ። ነገር ሁሉ የእናንተ ነውና፤
22ጳውሎስ ቢሆን፥ ወይም አጵሎስ ቢሆን፥ ወይም ኬፋ ቢሆን፥ ወይም ዓለምም ቢሆን፥ወይም ሕይወት ቢሆን፥ ወይም ሞት ቢሆን፥ ወይም ያለውም ቢሆን፥ ወይም የሚመጣውም ቢሆን
23ሁሉ የእናንተ ነው፤ እናንተም የክርስቶስ ናችሁ፤ ክርስቶስም የእግዚአብሔር ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።