መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

1ኛ ቆሮንቶስ 14

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ፍቅርን ተከታተሉ ለመንፈሳዊ ስጦታዎችም ከፍተኛ ጉጉት ይኑራችሁ፣
2በተለይም ደግሞ ትንቢት የመናገር ስጦታን በብርቱ ፈልጉ። በልሳን የሚናገር ለሰው ሳይሆን ለእግዚአብሔር ይናገራል፣በመንፈስ የተሰወሩ ነገሮችን ይናገራልና ማንም አይረዳውም።
3ትንቢት የሚናገር ግን ሰዎችን ለማነጽ፣ለማበረታታትና፣ ለማጽናናት፣ ይናገራል።
4በልሳን የሚናገር ራሱን ያንጻል፣ትንቢት የሚናገር ግን ቤተክርስቲያንን ያንጻል።
5እንግዲህ ሁላችሁም በልሳኖች ብትናገሩ ምኞቴ ነበር። ከዚያ ይበልጥ ትንቢት ብትናገሩ እወዳለሁ። በልሳን የተነገረውን የሚተረጉም ከሌለ፣ ቤተክርስቲያን እንድትታነጽ ልሳን ከሚናገር ይልቅ ትንቢት የሚናገር ይበልጣል።
6ወንድሞች እና እህቶች፣ልሳን እየተናገርሁ ወደ እናንተ ብመጣ ምን እጠቅማችኋለሁ? በመገለጥ፣ወይም በእውቀት፣ወይም በትንቢት፣ወይም በማስተማር ካልሆነ ልጠቅማችሁ አልችልም።
7ሕይወት የሌላቸው እንደ ዋሽንት ወይም ክራር ያሉ የሙዚቃ መሣሪያዎች መለየት የሚቻሉ ድምፆችን ካላወጡ፣አንድ ሰው የትኛው የሙዚቃ መሣሪያ እንደተጫወተ እንዴት ማወቅ ይችላል?
8መለከት ሊለይ በማይቻል ድምፅ ቢነፋ፣አንድ ሰው ለጦርነት ለመዘጋጀት ጊዜው እንደሆነ እንዴት ሊያውቅ ይችላል?
9እናንተንም በተመለከተ እንዲሁ ነው። ሊታወቅ የማይችል ንግግር ብትናገሩ አንድ ሰው ምን እንደተናገራችሁ እንዴት ሊያውቅ ይችላል? እናንተ ትናገራላችሁ ነገር ግን ማንም አይረዳችሁም።
10በዓለም ውስጥ ብዙ ልዩ ልዩ ቋንቋዎች እንዳሉ ጥርጥር የለውም፣
11አንዳቸውም ግን ትርጉም የሌላቸው አይደሉም። የአንድን ቋንቋ ትርጉም የማላውቅ ከሆን ለሚናገረው ሰው እንግዳ እሆንበታለሁ፣ተናጋሪውም እንግዳ ይሆንብኛል።
12ለእናንተም እንዲሁ ነው። ለመንፈስ ቅዱስ መገለጦች ከፍተኛ ፍላጎት ስላላችሁ፣ቤተክርስቲያንን ለማነጽ ጉጉት ይኑራችሁ።
13ስለዚህ በልሳን የሚናገር መተርጎም እንዲችል ይጸልይ።
14በልሳን በምጸልይበት ጊዜ መንፈሴ ይጸልያል፣አእምሮዬ ግን ያለ ፍሬ ነው።
15ታዲያ ምን ላድርግ? በመንፈሴም እጸልያልሁ፣በአእምሮዬም እጸልያለሁ። በመንፈሴ እዘምራለሁ፣በአእምሮዬም እዘምራለሁ።
16እንደዚያ ካልሆነ ግን እግዚአብሔርን በመንፈሳችሁ ብታመሰግኑና ሌላው ሰው በምታመሰግኑበት ሰዓት ምን እያላችሁ እንደሆነ ካላወቀ እንዴት "አሜን" ይላል?
17በእርግጠኝነት በሚገባ እያመሰገናችሁ ነው፣ሌላው ሰው ግን እየታነጸበት አይደለም።
18ከሁላችሁም የበለጠ በልሳን ስለምናገር እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።
19በቤተክርስቲያን ውስጥ ግን ሰዎችን ማስተማር እንድችል፥ በልሳን አሥር ሺ ቃላትን ከምናገር፣ በአእምሮዬ አምስት ቃላትን መናገር እመርጣለሁ።
20ወንድሞች እና እህቶች፣በአስተሳሰባችሁ ልጆች አትሁኑ። ይልቁን ክፋትን በተመለከተ እንደ ሕፃናት ሁኑ። ነገር ግን በአስተሳሰባችሁ ይበልጥ የበሰላችሁ ሁኑ።
21በሕጉ እንደተጻፈው፣"የማያውቁት ቋንቋ ባላቸው ሰዎችና እንግዳ በሆነ ንግግር ለዚህ ሕዝብ እናገራለሁ። እንደዚያም ሆኖ አይሰሙኝም፣" ይላል እግዚአብሔር።
22ስለዚህ ልሳኖች ለአማኞች ሳይሆን አማኝ ላልሆኑ ሰዎች ምልክት ናቸው። ትንቢት መናገር ግን ለማያምኑ ሰዎች ሳይሆን ለአማኞች ምልክት ነው።
23ስለዚህ፣ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለ ሰው ሁሉ ቢሰበሰብ እና በልሳኖች በመናገር ላይ እያሉ ከውጭ ያሉና የማያምኑ ሰዎች ቢገቡ አብደዋል አይሉምን?
24ነገር ግን ሁላችሁም ትንቢት እየተናገራችሁ ባለበት ሰዓት አማኝ ያልሆነ ወይም የውጭ ሰው ቢገባ በሚሰማው ነገር ሁሉ ኃጢአተኝነቱ ይሰማዋል። በሚነገረው ነገር ሁሉ ይፈረድበታል።
25የልቡም ምስጢር ሁሉ ይገልጣል። ከዚህም የተነሳ፣ በግንባሩ ተደፍቶ እግዚአብሔርን ያመልካል። እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው! ብሎ ያውጃል።
26ታዲያ ምን ይሁን፣ወንድሞች እና እህቶች? በአንድነት በምትሰበሰቡበት ጊዜ፣እያንዳንዳችሁ መዝሙር፣ትምህርት፣መገለጥ፣ልሳን፣ወይም ልሳን መተርጎም አላችሁ። የምታደርጉትን ሁሉ ቤተክርስቲያንን ለማንጽ አድርጉት።
27ማንም በልሳን ቢናገር ሁለትም ሦስትም ብትሆኑ ተራ በተራ አድርጉት። ሌላው ሰው ደግሞ በልሳን የተነገረውን ይተርጉም።
28የሚተረጉም ከሌለ ግን፣ሁሉም ሰው ድምፁን ሳያሰማ ለራሱ እና ለእግዚአብሔር ብቻ ይናገር።
29ሁለት ወይም ሦስት ነቢያቶች በሚናገሩበት ጊዜ ሌሎች የሚነገረውን በመመርመር ያዳምጡ።
30ነገር ግን በስብሰባው ውስጥ አንድ ሰው መረዳት ከመጣለት በመናገር ላይ ያለው ዝም ይበል።
31ትንቢት ስትናገሩ ሁሉም ሰው እንዲበረታታ እያንዳንዳችሁ ተራ በተራ መናገር ትችላላችሁ።
32የነቢያቶች መንፈስ ለነቢያት ይገዛል።
33እግዚአብሔር የሰላም አምላክ እንጂ ግራ የመጋባት አምላክ አይደለም። በሁሉም የአማኞች አብያተክርስቲያናት ውስጥ፦
34ሴቶች በቤተክርስቲያን ውስጥ ዝም ይበሉ። እንዲናገሩ አይፈቀድላቸውም። ሕጉ ይህን ይላልና ይልቁንስ ይገዙ ።
35ሊያውቁ የሚፈልጉት ነገር ቢኖር፣ባሎቻቸውን በቤት ውስጥ ይጠይቁ። ሴት በቤተክርስቲያን ውስጥ መናገሯ አሳፋሪ ነውና።
36የእግዚአብሔር ቃል የመጣው ከእናንተ ነውን? ወይስ ወደ እናንተ ብቻ ደርሷልን?
37ማንም ሰው ራሱን ነቢይ እንደሆነ ወይም መንፈሳዊ እንደሆነ ቢያስብ፣የጻፍሁላችሁ ነገሮች የጌታ ትዕዛዛት እንደሆኑ ሊያውቅ ይገባዋል።
38ነገር ግን ማንም ይህን ባያውቅ እርሱም ዕውቅና አያግኝ።
39እንግዲህ ወንድሞች እና እህቶች፣ትንቢትን መናገር በቅንነት ፈልጉ፣ ማንንም ልሳኖችን እንዳይናገር አትከልክሉ።
40ነገር ግን ማንኛውም ነገር በመልካም ምግባር እና በሥርዓት ይደረግ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።