መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

1ኛ ቆሮንቶስ 13

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በሰዎች እና በመላእክት ልሳኖች ብናገር፣ግን ፍቅር ከሌለኝ፣የሚንጫጫ ቃጭል ወይም የሚጮህ ታንቡር ነኝ።
2የትንቢት ስጦታ ቢኖረኝ፣ የተሰወሩ እውነቶችን እና እውቀት ሁሉ ቢኖረኝ፣ተራሮችን ከስፍራቸው የሚያስወግድ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ፣ ፍቅር ከሌለኝ ግን ምንም የማይጠቅም ነኝ።
3ድሆችን ለመመገብ ያለኝን ሁሉ ብሰጥ፣ ሰውነቴንም እንዲቃጠል ብሰጥ፣ፍቅር ከሌለኝ ግን ምንም አይጠቅመኝም።
4ፍቅር ታጋሽና ደግ ነው። ፍቅር አይመቀኝም ደግሞም አይመካም። አይታበይም
5ወይም ትህትና የጎደለው አይደለም። ራስ ወዳድ አይደለም። በቀላሉ አይበሳጭም፤ወይም በደልን አይቆጥርም።
6ፍቅር በአመጽ ደስ አይሰኝም፣በእውነት ግን ደስ ይለዋል።
7ፍቅር ሁሉን ይታገሳል፤ሁሉን ያምናል፤በሁሉም ድፍረት አለው በሁሉ ይጸናል።
8ፍቅር ፍጻሜ የለውም። ትንቢቶች ያልፋሉ፤ልሳኖችም ቢሆኑ ያበቃሉ፤ዕውቀትም ቢሆን ጊዜ ያልፍበታል።
9ከዕውቀት የተወሰነውን እናውቃልን፣ትንቢትም በከፊል እንተነቢያለን።
10ነገር ግን ፍጹም የሆነው ሲመጣ፣ፍጹም ያልሆነው ወደ ፍጻሜ ይደርሳል።
11ልጅ በነበርሁበት ጊዜ፣እንደ ልጅ እናገር ነበር፣እንደ ልጅም አስብ ነበር፣የመረዳት ችሎታዬም እንደ ልጅ ነበር። ጎልማሳ ስሆን ግን የልጅነት ነገሮችን አስወገድሁ።
12አሁን በጨለማ ውስጥ ያለን ምስል በመስታዋት እንደሚያይ እንመለከታለን፣የዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን። አሁን ዕውቀትን በከፊል አውቃለሁ፣የዚያን ጊዜ ግን ልክ እኔ ሙሉ በሙሉ እንደምታወቀው ሙሉ በሙሉ አውቃለሁ።
13ነገር ግን እምነት፣ ተስፋ፣ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ግን ጸንተው ይኖራሉ። ከእነዚህ የሚበልጠው ፍቅር ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።