መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

1ኛ ቆሮንቶስ 12

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ወንድሞች እና እህቶች መንፈሳዊ ስጦታዎችን በተመለከተ፣የማታውቁት ነገር እንዲኖር አልፈልግም።
2አረማውያን በነበራችሁበት ወቅት፣መናገር እንኳ በማይችሉ ጣዖታት ወደማታውቁት መንገድ ተመርታችሁ እንደነበር ታውቃላችሁ።
3ስለዚህ ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ፣"ኢየሱስ የተረገመ ነው፣" የሚል እንደሌለ ሁሉ፤ እንዲሁም በእግዚአብሔር መንፈስ ካልሆነ በቀር፣"ኢየሱስ ጌታ ነው፣" ሊል የሚችል እንደሌለ እወቁ።
4ልዩ ልዩ ስጦታዎች አሉ፣መንፈስ ቅዱስ ግን አንድ ነው።
5አገልግሎቶች ልዩ ልዩ ናቸው፣ጌታ ግን አንድ ነው።
6ልዩ ልዩ ሥራዎች አሉ፣ነገር ግን ለእያንዳንዱ ሰው ችሎታን የሚሰጥ አንዱ እግዚአብሔር ነው።
7ደግሞም ለእያንዳንዱ መንፍስ ቅዱስን መግለጥ የተሰጠው ለሁሉም ጥቅም ሲባል ነው።
8ለአንዱ የጥበብ ቃል በመንፈስ ቅዱስ ይሰጣል፣ለሌላው ደግሞ የእውቀት ቃል በዚያው መንፈስ ይሰጣል።
9ለሌላው በዚያው መንፈስ እምነት ይሰጠዋል፣ለሌላው ደግሞ በዚያው መንፈስ የፈውስ ስጦታ ይሰጠዋል።
10ለሌላው ደግሞ የኃይል ሥራዎች፣ለሌላው ትንቢት መናገር። ለሌላው ደግሞ መናፍስትን መለየት፣ለሌላው በልዩ ልዩ ልሳኖች መናገር፣እና ለሌላው ልሳኖችን የመተርጎም ስጦታ ይሰጠዋል።
11ነገር ግን፣ለእያንዳንዳቸው እንደወደደ ልዩ ልዩ ስጦታዎችን በመስጠት በእነዚህ ሁሉ የሚሠራው ያው አንዱ መንፈስ ቅዱስ ነው።
12አካል አንድ ሆኖ ሳለ ብዙ ብልቶች እንዳሉት ሁሉ፣ ሁሉም ብልቶች የእንዱ አካል ክፍል እንደሆኑ፣በክርስቶስም እንዲሁ ነው።
13በአንድ መንፈስ በአንድ አካል እንደተጠመቅን፣አይሁድ ይሁኑ ግሪኮች፣ባሪያ ይሁን ነጻ፣ሁሉ ከአንዱ መንፈስ ጠጥተዋል።
14አካል አንድ ብልት ብቻ ሳይሆን ብዙ ብልቶች አሉት።
15እግር፣"እኔ እጅ አይደለሁም፣ስለዚህ የአካሉ ክፍል አይደለሁም፣" ቢል የአካሉ ክፍል መሆኑ አይቀርም።
16ጆሮም ተነስቶ፣"ዓይን ስላይደለሁ፣የአካሉ ክፍል አይደለሁም፣" ቢል የአካሉ ክፍል ከመሆን አይቀነስም። አካል ሁሉ ዓይን ቢሆን፣ መስማት ወዴት ይሆናል?
17አካል ሁሉ ጆሮ ቢሆን፣ማሽተት ወዴት ይሆናል?
18እግዚአብሔር ግን እያንዳንዱን የአካል ክፍል እንደወደደ ሠርቶታል።
19ሁሉም አንድ ብልት ቢሆኑ ኑሮ፣አካል ወዴት በሆነ ነበር?
20አሁን ግን ብዙ ብልቶች ያሉት፣ አንድ አካል ነው።
21ዓይን እጅን፣"አንተ አታስፈልገኝም፣" ሊል አይችልም። ራስም እግርን፣"አታስፈልገኝም፣" ሊል አይችልም።
22ነገር ግን ዝቅተኛ ግምት የሚሰጣቸው ብልቶች አስፈላጊ ናቸው፣
23ዝቅተኛ ግምት የምንሰጣቸውን የሰውነት ክፍሎች ትልቅ ክብር እንሰጣቸዋለን፣እምናፍርባቸውን ብልቶች ደግሞ በአክብሮት እንይዛለን።
24የማናፍርባቸውን ብልቶች ደግሞ በአክብሮት መያዝ አያስፈልገንም ምክንያቱም ቀድሞዉኑ ክብር አግኝተዋል። እግዚአብሔር ግን ብልቶችን ሁሉ በአንድነት በማያያዝ ክብር ላልተሰጣቸው የበለጠ ክብርን ሰጥቷል።
25እግዚአብሔር እንዲህ ያደረገው በአካል ውስጥ መከፋፈል እንዳይኖርና ይልቁን ብልቶች በበለጠ ፍቅር እርስ በርሳቸው አንዳቸው ሌላቸውን እንዲከባከቡ ነው።
26እናም አንዱ ብልት ሲሰቃይ ሁሉም ብልቶች አብረው ይሰቃያሉ። አንዱ ብልት ሲከብር፣ሁሉም ብልቶች አብረው ሐሴት ያደርጋሉ።
27እንግዲህ እናንተ የክርስቶስ አካል ስትሆኑ እያንዳንዳችሁ የአካሉ ብልቶች ናችሁ።
28እግዚአብሔርም በቤተክርስቲያን በመጀመሪያ ሐዋርያትን፣ሁለተኛ ነቢያትን፣ሦስተኛ አስተማሪዎችን፣ከዚያም ተአምራት ማድረግን፣በመቀጠል የፈውስ ስጦታዎችን፣እርዳታ የሚያደርጉትን፣ የአስተዳደር ሥራ የሚሠሩትን፣ እና ልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖችን የሚናገሩትን ሰጥቷል።
29ታዲያ ሁላችን ሐዋርያት ነን? ሁላችንስ ነቢያት ነን? ወይስ ሁላችን አስተማሪዎች ነን? ሁላችን ተአምራቶችን እናደርጋለን?
30ሁላችን የፈውስ ስጦታዎች አሉን? ሁላችን በልሳኖች እንናገራለን? ሁላችን ልሳኖችን እንተረጉማለን?
31የሚበልጡትን ስጦታዎች በከፍተኛ ጉጉት ፈልጉ። እጅግ የሚበልጠውንም መንገድ አሳያችኋልሁ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።