መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

1ኛ ቆሮንቶስ 11

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እኔ ክርስቶስን እንደምመስል፣እናንተም እኔን ምሰሉ።
2አሁን የማመሰግናችሁ በሁሉ ነገር ስለምታስቡኝ ነው። ለእናንተ ያስተላለፍኳቸውን ልምዶች ልክ እንደዚያው እንዳሉ አጥብቃችሁ በመያዛችሁ አመሰግናችኋለሁ።
3ክርስቶስ የወንድ ሁሉ ራስ ፣ወንድ ደግሞ የሴት ራስ ፣ እግዚአብሔር የክርስቶስ ራስ እንደሆነ እንድትረዱ እፈልጋለሁ።
4ራሱን ሸፍኖ የሚጸልይ ወይም ትንቢት የሚናገር ወንድ የእርሱ ራስ የሆነውን ክብር ያሳጣል።
5ነገር ግን ራሷን ሳትሸፍን የምትጸልይ ወይም ትንቢት የምትናገር ሴት ራሷን ክብር ታሳጣለች። ይህን ማድረግ ልክ ጠጉሯን እንደመላጨት ነው።
6ሴት ራሷን ካልሸፈነች፣ጠጕሯን አሳጥራ መቆረጥ ይኖርባታል። ሴት ጠጕሯን አሳጥራ መቆረጧ ወይም መላጭቷ አሳፋሪ ከሆነ፣ ራሷን ትሸፍን።
7ወንድ ራሱን መሸፈን የለበትም፣ ምክንያቱም እርሱ የእግዚአብሔር መልክ እና ክብር ነውና።
8ሴት ግን የወንድ ክብር ነች። ወንድ ከሴት አልተገኘምና። ይልቁንስ፣ሴት ከወንድ ተገኝታለች።
9ወንድ ለሴት አልተፈጠረም፣ሴት ግን ለወንድ ተፈጥራለች።
10ለዚህ ነው፣ ከመላእክቱ የተነሳ፣ ሴት በራሷ ላይ የሥልጣን ምልክት ሊኖራት የሚገባው።
11የሆነ ሆኖ፣በጌታ ሴት ከወንድ፣ ወንድም ከሴት የተነጣጠሉ አይደሉም።
12ሴት የተገኘችው ከወንድ እንደሆነ ሁሉ፣ወንድም የተገኘው ከሴት ነው። ሁሉም ነገር ደግሞ የተነኘው ከእግዚአብሔር ነው።
13ራሳችሁ ፍረዱ፦ሴት ራሷን ሳትሸፈን ወደ እግዚአብሔር ብትጸልይ ተገቢ ነው?
14ወንድስ ረጅም ጠጕር ቢኖረው አሳፋሪ እንደሆነ ተፈጥሮ ራሱ አያስተምራችሁም?
15ሴት ግን ረጅም ጠጕር ቢኖራት ክብሯ እንደሆነ ተፈጥሮ ራሱ አያስተምራችሁም? ለእርሷ ጠጕር የተሰጣት እንደ መሸፈኛ ነውና።
16ነገር ግን በዚህ ማንም ክርክር ሊያስነሳ ቢፈልግ፣እኛም ሆንን የእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት ከዚህ የተለየ ልምምድ የላቸውም።
17በሚከተሉት መመሪያዎቼ ግን፣አላመሰግናችሁም። ምክንያቱም በምትሰበሰቡበት ጊዜ፣ ለተሻለ ነገር ሳይሆን እጅግ ለከፋ ነገር ትሰበሰባላችሁ።
18በመጀመሪያ፣ በቤተክርስቲያን ስትሰበሰቡ በመካከላችሁ መከፋፈል እንዳለ ሰምቼአለሁ፣ ደግሞም ይህ እንደሚሆን በመጠኑም ቢሆን አምኜበታልሁ።
19ምክንያቱም በእናንተ መካከል ተቀባይነትያላቸው እንዲለዩ የተለያዩ ቡድኖች መኖራቸው ግድ ነው።
20በአንድነት በምትሰብሰቡበት ጊዜ፣የምትበሉት የጌታን ማዕድ አይደለምና።
21በምትበሉበት ጊዜ፣ሌሎች ምግብ ከማግኘታቸው በፊት እያንዳንዱ ቀድሞ የየራሱን ምግብ ይበላል። አንዱ ተርቦ ሳለ ሌላው ይሰክራል።
22የምትበሉበትና የምትጠጡበት ቤት የላችሁም? የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን በመናቅ ምንም የሌላቸውን ታዋርዳላችሁ? ምን ልበላችሁ? ታዲያ ላመስግናችሁ? ለዚህ አላምሰግናችሁም!
23ከጌታ የተቀበልሁትን ለእናንተ አሳልፌ ሰጥቼአለሁ፣ ጌታ ኢየሱስ ታልፎ በተሰጠበት ምሽት፣እንጀራ አንሳ።
24ካመሰገነ በኋላ ቆረሰውና፣"ለእናንተ የሆነ ሥጋዬ ይህ ነው፣ይህን እኔን ለማስታወስ አድርጉት፣" አለ።
25እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋን አንስቶ፣"ይህ በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው።ይህን በጠጣችሁ ጊዜ ሁሉ እኔን ለማስታወስ አድርጉት።"
26ይህን እንጀራ በበላችሁ እና ይህን ጽዋ በጠጣችሁ ጊዜ ሁሉ፣ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ታውጃላችሁ።
27ስለዚህ ማንም፣ተገቢ ባልሆነ ሁኔታ የጌታን እንጀራ ቢበላ ወይም የጌታን ጽዋ ቢጠጣ፣ለጌታ ሥጋ እና ለጌታ ደም ተጠያቂ ይሆናል።
28አንድ ሰው ራሱን ከመረመረ በኋላ እንጀራውን ይብላ ጽዋዉንም ይጠጣ።
29የጌታ ሥጋ መሆኑን ሳይረዳ የሚበላ እና የሚጠጣ፣በራሱ ላይ ፍርድን ይበላል ይጠጣልም።
30በመካከላችሁ ብዙዎች የታመሙ እና በሽተኞች የሆኑት ስለዚህ ነው፣ አንዳንዶችም ደግሞ ሞተዋል።
31ነገር ግን ራሳችንን ብንመረምር አይፈረድብንም።
32በጌታ ስንፈረድ ግን፣ከዓለም ጋር እንዳንኮነን እንገሠጻለን።
33ስለዚህ፣ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ለመብላት ስትሰበሰቡ፣እርስ በርሳችሁ ተጠባበቁ።
34ማንም የተራበ ቢኖር፣እቤቱ ይብላ፣እንዲያ ሲሆን ስትሰበሰቡ ለፍርድ አይሆንባችሁም። ስለ ጻፋችሁልኝ ሌሎች ነገሮች፣ስመጣ መመሪያዎችን እሰጣለሁ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።