1የሌዊ ወንዶች ልጆች፤ ጌድሶን፣ቀዓት፣ሜራሪ፣
2የቀዓት ወንዶች ልጆች፤እንበረም፣ ይሰዓር፣ኬብሮን፣ዑዝኤል።
3የእምበረም ልጆች፤ አሮን፣ሙሴ፣ማርያም። የአሮን ወንዶች ልጆች፤ናዳብ፣አብዮድ፣አልዓዛር፣ኢታምር።
4አልዓዘር ፊንሐስን ወለደ፤ ፊንሐስ አቡሲን ወለደ፤
5አቢሲ ኦዚን ወለደ፤
6ኦዚ ዘራእያን ወለደ፤ዘራእያ መራዮትን ወለደ፤
7መራዮት አማርያን ወለደ፤አማርያ አኪጦብን ወለደ፤
8አኪጦብ ሳዶቅን ወለደ፤
9ሳዶቅ አኪማአስን ወለደ፤አኪማአስ ዓዛርያስን ወለደ፤ዓዛርያስ ዮሐናን ወለደ፤
10ዮሐናን ዓዛርያስ ወለደ፤እርሱም ሰለሞን በኢየሩሳሌም ባሠራው ቤተ መቅደስ በክህነት ያገለግል ነበር፤
11ዓዛርያስ አማርን ወለደ፤አማርያም አኪጦብን ወለደ፤
12አኪጦብ ስሳዶቅን ወለደ፤ሳዶቅ ሰሎምን ወለደ፤
13ሰሎም ኬሌቅያስን ወለደ፤ኬሌቅያስ ዓዛርያስ ሠራያን ወለደ፤
14ዓዛርያስ ሠራያን ወለደ፤ሠራያ ኢዮሴዴቅን ወለደ፤
15እግዚአብሔር የይሁዳና የእየሩሳሌም ሕዝብ በናቡከደነፆር እጅ ተማርከው እንዲወሰዱ ባደረገ ጊዜ ኢዮሴዴቅም አብሮ ተማርኮ ሄደ።
16የሌዊ ወንዶች ልጆች፤ ጌድሶን፣ቀዓት፣ሜራሪ።
17የጌድሶን ወንዶች ልጆች፤ሎቢኒ፣ሰሜኢ።
18የቀሃት ወንዶች ልጆች፤እምበረም፣ይስዓር፣ኬቤሮን፣ዑዝኤል።
19የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤ሞሖሊ፣ሙሲ። በየአባቶቻቸው ቤተሰብ የተቁጠሩ የሌዊ ጎሣዎች የሚከተሉት ናቸው፤
20ከጌርሶን፤ ልጁ ሎቢኒ፣ልጅ ኢኤት፣ልጁ ዛማት፣
21ልጁ ዮአክ፣ልጁ አዶ፣ልጁ ዛራ፣ልጁ ያትራይ።
22የቀዓት ዘሮች፤ ልጁ አሚናዳብ፣ልጁ ቆሬ፣ልጁ አሴር፣
23ልጁ ህልቃና፣ልጁ አቢሳፍ፣ልጁ አሴር፣
24ልጁ ኢኢት፣ልጁ ኡርኤል፣ልጁ ዖዝያ፣ልጁ ሳውል።
25የሕልቃና ዘሮች፤ አማሢ፣አኪሞት።
26ልጁ ሕልቃና፣ልጁ ሱፊ፣ልጁ ናሐት፣
27ልጁ ኤልያብ፣ልጁ ይሮሐም፣ልጁ ሕልቃና፣ልጁ ሳሙኤል።
28የሳሙኤል ወንዶች ልጆች፤የበኩር ልጁ ኢዮኤል፣ሁለተኛው ልጁ አብያ።
29የሜራሪ ዘሮች፤ ሞሖሊ፣ልጁ ሎቤኒ፣ልጁ ሰሜኢ፣ልጁ ዖዛ፣
30ልጁ ሳምን፣ልጁ ሐግያ፣ልጁ ዓሣያ።
31ታቦቱ ከገባ በኋላ፣ዳዊት የመዘምራን አለቃ አድርጎ በእግዚአብሄር ቤት የሾማቸው ሰዎች እነዚህ ናቸው፤
32እርሱም ሰሎሞን የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ፣በማደሪያው ይኸውም በመገናኛ ድንኳን ፊት ሆነው እየዘመሩ ያገለግሉ ነበር፣አገልግሎታቸውንም የሚያከናውኑት በወጣላቸው ደንብ መሠረት ነው።
33ከወንዶች ልጆቻቸው ጋር ሆነው ያገለገሉ ሰዎች እነዚህ ናቸው፤ከቀዓታዊያን ልጆች፤ሙዚቃ ተጫዋቹ ኤማን፣የኢዮኤል ልጅ፣የሳሙኤል ልጅ፤
34ሳሙኤል የሕልቃና ልጅ ነበረ፤ ሕልቃና ፣የይሮሐም ልጅ፣ይብኤሊኤል ልጅ፣የቶዋ ልጅ፣
35የሱፍ ልጅ፣የሥልቃና ልጅ፣የመሐት ልጅ፣የአማሢ ልጅ፣
36የሕልቃና ልጅ፣የኢዮኤል ልጅ፣የዓዛርይስስ ልጅ፣የሶፎንያስ ልጅ፣
37የታሐት ልጅ፣የአሴር ልጅ፣የአብያሳፍ ልጅ፣የቆሬ ልጅ፣
38የይስዓር ልጅ፣የቃዓት ልጅ፣የሌዊ ልጅ፣የእስራኤል ልጅ።
39እንዲሁም የሔማን ወንድም አሳፍ በስተቀኙ ሆኖ ያገለግል ነበር፤ አሳፍ የበራክያ ልጅ፤የሳምዓ ልጅ፤
40የሚካኤል ልጅ፣
41የኤትኒ ልጅ፣የዛራ ልጅ፣የዓዳያ ልጅ፣
42የኤታን ልጅ፣የዛማት ልጅ፣የሰሜኢ ልጅ፣
43የኢኤት ልጅ፣የጌድሶን ልጅ፣የሌዊ ልጅ፣
44በስተግራቸው በኩል አብረዋቸው ያሉት የሜራሪ ልጂች፣የቂሳ ልጅ ኤታን፣የአብዲ ልጅ፣የማሎክ ልጅ፣
45የሐሸብያ ልጅ፣የአሰያሰ ልጅ፣የኬልቅያስ ልጅ፣
46የአማሲ ልጅ፣የባኒ ልጅ፣የሰሜር ልጅ፣
47የሞሖሊ ልጅ፣የሙሲ ልጅ፣የሜራሪ ልጅ፣የሌዊ ልጅ፣
48ሌዋውያን ወንድሞቻቸው ግን የእግዚአብሔር ቤት የማደሪያ ድንኳን ተግባር እንዲያከናውኑ ተመድበው ነበር።
49አሮንና ልጆቹ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ባዘዝው ምሠረት ስለእስራኤል ማስተሰሪያ በቅድስት ቅዱሳኑ ውስጥ የሚያከናውነውን ተግባር ሁሉ፣በመሠዊያ ላይ የሚቃጠል መሥቃዕትና በዕጣኑ መሠዊያ ላይ የሚቀርበውም መሥዋዕት የሚቀርቡት ግን አሮንና ዘሮቹ ብቻ ነበሩ።
50የአሮን ዝርያዎች እነዚህ ነበሩ፤ ልጁ አልዓዛር፣ልጅ ፊንሐስ፣ልጁ አቢሹ፣
51ልጁ ቡቂ፣ልጁኦዚ፣ልጁ ዘራአያ፣
52ልጁ መራዮት፣ልጁ አማርያ፣ልጁ አኪጦብ፣
53ልጁ ሳዶቅ፣ልጁ አኪማአስ።
54መኖሪያዎቻቸው እንዲሆኑ የተመደቡላቸው ቦታቸው እነዚህ ናቸው፤የመጀመሪያ ዕጣ የእነርሱ ስለ ሆነ፣ከቀዓት ጎሣ ለሆኑት ለአሮን ዘሮች የተመደቡላቸው መኖሪያቸው እነዚህ ነበሩ።
55ለእነርሱም በይሁዳ ምድር የሚገኘው ኬብሮንና በዙሪያዋ ያለው የግጦሽ ቦታ ተሰጠ፣
56በኬብሮን ዙሪያ የሚገኙት የዕርሻ ቦታዎችና መንደሮች ግን ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ተሰጡ።
57ለአሮን ዘሮች የመማፀኛ ከተሞች የሆኑትን ኬብሮንን፣ልብናን፣የቲርን፣ኤሽትሞዓን፣
58ሖሎንን፣ዳቤርን፣ከነመሰማሪዎቻቸው።
59ዓሳንን፣ዮታን፣ቤትሳኒስን ከነመሰማሪዎቻቸው ሰጡ።
60ከብንያም ነገድ ድርሻ ላይ ገባዖንን፣ጌባን፣ጋሌማን፣ዓናቶትን ከነመሰማሪያዋቻቸው ሰጡ። ለቀዓት ዘሮች የተከፋፈሉ እነዚህ ከተሞች ባጠቃላይ ዐሥራ ሦስት ናቸው።
61ለቀሩት የቀዓት ዘሮች ደግሞ ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ድርሻ በዕጣ ዐሥር ከተሞች ተሰጧቸው።
62ለጌድሶን ነገድ በየጎሣቸው ከይሳኮር፣ከአሴር፣ከንፍታሌምና በባሳን ከሚገኘው ከምናሴ ነገድ ድርሻ ላይ ዐሥራ ሦስት ከተሞች ተመደቡላቸው።
63ለሜራሪ ዘሮች በየጎሣቸው ከሮቤል፣ከጋድና ከዛብሎን ድርሻ ላይ ዐሥራ ሁለት ከተሞች በዕጣ ተመደቡላቸው።
64እስራኤላዊያን ከተሞቹን በዚሁ ሁኔታ መድበው ከነመሰማሪያዎቻቸው ለሌዋውያኑ ሰጧቸው።
65ቀደም ብለው የተጠቀሱትንም ከተሞች ከይሁዳ ከስምዖንና ከብንያም ነገድ ላይ ወስደው በዕጣ መደቡላቸው።
66ለአንዳንድ የቀዓት ጎሣዎችም ከኤፍሬም ነገድ ድርሻ ላይ ከተሞች ተሰጣቸው።
67በኮረብታማው በኤፍሬም ምድር የሚገኙትን ሴኬምን(የማማፀኛ ከተማ) ፣ኔዝርን፣
68ዮቅምዓምን፣ቤትሖሮን፣
69ኤሎንንና ጋትሪሞን ከነመሰማሪዎቻቸው ሰጧቸው።
70እንዲሁም እስራኤላውያን ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ድርሻ ላይ ዓኔርና ቢልዓም የተባሉትን ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው ወስደው ለሩት የቀዓት ጎሣዎች ሰጧቸው።
71ለጌድሶናውያን ከምናሴ ነገድ እኩሌታ፣ በባሳን የሚገኘውን ጎላንና አስታሮትን ከነመሰማሪያዎቻቸው ተሰጠ፤
72ከይሳኮር ነገድ፤ ቃዴስን፣ዳብራትን
73ራሞትንና ዓኔምናን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ፤
74ከአሴር ነገድ መዓሳልን፣ዓብዶን፣
75ሑቆቅንና፣ረአብን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ፤
76ከንፍታሌም ነገድ በገሊላ የሚገኘውን ቃዴስን፣ሐሞንንና፣ቂርያታይምን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ።
77ከሌዋውያን የቀሩት የሜራሪ ጎሣዎች ደግሞ ከዚህ የሚከተለው ወሰዱ፤ከዛቢሎን ነገድ ዮቅኒዓምን፣ቀርታህን፣ሬሞንና፣ታቦርን፣ከነመሰማሪዮቻቸው ወሰዱ።
78ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ ኪኢያሪኮ በስተምስራቅ ከሚገኘውን ቦሶርን፣ያሳን፣
79ቅዴሞትንና ሜፍዓትን ከነመሰማሮያዎቻችው ወሰዱ፤
80ከጋድ ነገድ በገለዓድ የምትገኘውን ሬማትን፣መሃናይምን፣
81ሐሴቦንና ኢያዜርን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ።