መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

1ኛ ዜና 7

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የይሳኮር ወንዶች ልጆች፤ ቶላ፣ፋዋ፣ያሱብ፣ሺምሮን፣ባጠቃላይ አራት ናቸው።
2የቶላ ወንዶች ልጆች፤ኦዚ፣ርረፋያ፣ይሪኤል፣የሕማይ፣ይብሣም፣ሽሚኤል፣እነዚህ የየቤተሰባቸው አለቆች ናቸው።በዳዊት ዘመነመንግሥት ከቶላ ዘሮች በየትውልድ ሀረጋቸው የተቁጠሩ የቶላ ዘሮች ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ፤ቁጥራቸው ሃያ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ነበረ።
3የኦዚ ወንድ ልጅ፤ይዝረሕያ። የይዝረሐያ ወንዶች ልጆች፤ሚካኤል፣አብድዩ፣ይሺያ፣አምስቱም አለቆች ነበሩ።
4ብዙ ሚስቶችና ልጆች ስለ ነበሩአቸው፣ከነቤተሰባቸው የትውልድ ሐረግ ለውጊያ ብቁ የሆኑ 36000 ሰዎች ነበሩአቸው።
5ከይስኮር ጎሣዎች ሁሉ የተመዘገቡት ተዋጊዎች የቤተሰቦቹ ትውልድ ቁጥር ባጠቃላይ 87000 ነበሩ።
6ሦስቱ የብንያም ወንዶች ልጆች፤ ቤላ፣ቤኬብ፣ይዲኤል።
7የቤላ ወንዶች ልጆች፤ ኤሴቦንም፣ኦዚ፣ዑዝኤል፣ኢያሪሙት፣ዒሪ፣ባጠቃላይ አምስት ሲሆኑ፣ የቤተ ሰብ አለቆች ናቸው፤በትውልድ ሐረግ መዝገባቸው 22034 ተዋጊ ሰዎች ተመዝገበዋል።
8የቤኬር ወንዶች ልጆች፤ዝሚራ፣ኢዮአስ፣አልዓዛር፣ኤልዮዔናይ፣ዖምሪ፣ ኢያሪሙት፣አብያ፣ዓናቶት፣ዔሌሜት፣እነዚህ ሁሉ የቤኬር ልጆች ነበሩ።
9በትውልድ ሐረግ መዝገባቸውም ውስጥ የየቤተ ሰባቸው አለቆችና ሃያ ሺህ ሁለት መቶ ተዋጊዎች ተመዝግበዋል።
10የይዲኤል ልጅ፤ ቢልሐን።የቢልሐን ወንዶች ልጆች፤ የዑስ፣አሲሳኦር፣
11እነዚህ ሁሉ የይዲኤል ልጆች የየቤተሰቡ አለቆች ነበሩ፤እነርሱም ለውጊያ ብቁ የሆኑ 17200 ተዋጊዎች ነበሯቸው።
12(ሳፈንና ሁፊም የዒር ዘሮች ሲሆኑ ሑሺም ደግሞ የአሐር ዘር ነው።)
13የንፍታሌም ወንዶች ልጆች፤ ያህጽሔል፣ጉኒ፣ዬጽር፣ሺሌም፤እነዚህ የባላ የልጅ ልጆች ናቸው።
14የምናሴ ዘሮች፤ ሶርያዊት ቁባቱ የወለደችለት ልጁ አሥርኤል ነው።እርሷም የገለዓድን አባት ማኪርያ የወለደች ናት፤
15ማኪርም ከሑፊምና ከሳፊም ወገኖች ሚስት አገባ።እኅቱም መዓካ ትባል ነበር።ሌላው ዘሩ ሰለጸዓድ ሲሆን፣እርሱም ሴቶች ልጆች ብቻ ነበሩት።
16የሚከር ሚስት መዓካ ወንድ ልጅ ወለደች፣ስሙንም ፋሬስ አለችው።የወንድሙም ስም ሱሮስ ይባላል፤ወንዶች ልጆቹም ኡላምና ራቄም ነበሩ።
17የኡላም ወንድ ልጅ፤ባዳን፣እነዚህ የምናሴ ልጅ፣የማኪር ልጅ፣የገለዓድ ወንዶች ልጆች ናቸው፤፤
18እኅቱ መለኬት ኢሱድን፣አቢዔዝርንና መሐላን ወለድች።
19የሽሚዳ ወንዶች ልጆች ደግሞ እነዚህ ነበሩ፤ አሒያንምምሴኬም፣ሊቅሒ፣አኒዓም።
20የኤፍሬም ዘሮች፤ ሹቱላ፣ልጁ ባሬድምምልጁ ታሐት፣ልጁ ኤልዓዳ፣ልጁ ታሐት፣
21ልጁ ዛባድ፣ልጁ ሹቱላ።ኤድርና ኤልዓድ ከብቶች ለመስረቅ በወረዱ ጊዜ፣የአገሩ ተወለጆች በሆኑት በጌት ሰዎች ተገደሉ።
22አባታቸውም ኤፍሬም ብዙ ቀን አለቀሰላቸው፤ዘመዶቹም መጥተው አፅናኑት።
23ከዚያም ወደ ሚስቱ ገብቶ ተኛ፤እርሷም ፀነሰች፤ወንድ ልጅም ወለደች፤በቤተሰቡ ላይ ከደረሰው መከራ የተነሣ ስሙን በሪያ አለው።
24ሴት ልጁ ስሟ ሲኢራ ይባላል፤እርሷም የታችኛውና የላይኛውን ቤት ሖሮንንና ኡዜን ሼራን የተባሉትን ከተሞች የቁረቁረች ናት።
25ልጁ ፋፌ፣ልጁ ሬሴፍ፣ልጁ ቴላ፣ልጁ ታሐን፣
26ልጁ ለአዳን፣ልጁ ዓሚሁድ ልጁ ኤሊሳማ፣
27ልጁ ነዌ፣ልጁ ኢያሱ።
28በምድራቸውና መኖሪያቸው ቤቴልንና በዙሪያዋ የሚገኙት ከተሞች በስተምሥራቅ ነዓራን፣በስተ ምዕራብ ጌዝርንና መንደሮቿን በሙሉ ታጠቃልል ነበር።
29በምናሴ ወሰን ላይ ቤትሳን፣ታዕናክ፣መጊዶና ዶና ከነመንደሮቻቸው ነበሩ።በእነዚህም መንደሮች የእስራኤል ልጅ የዮሴፍ ዘሮች ነበር።
30የአሴር ወንዶች ልጆች፤ዩምና፣የሱዋ፣የሱዊ፣በሪዓ፣እኅታቸውም ሤራሕ ትባል ነበር።
31የበሪዓ ወንዶች ልጆች፤ሐቤርም የቢርዛዊት አባት መልኪኤል።
32ሔቤርም ያፍሌጥን፣ሳሜርን፣ኮታምንና እኅታቸውን ሶላን ወለደ።
33የያፍሌጥ ወንዶች ልጆች፤ ፋሴክ፣ቢምሃል፣ዓሲት፣የያፍሌጥ ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ ።
34የስሜር ወንዶች ልጆች፤ አ፣፥ሮኦጋ፣ይሑባ፣አራም።
35የወንድሙ የኤላም ወንዶች ልጆች፤ጾፋ ይምና፣ሰሌስ፣ዓማል።
36የጻፋ ወንዶች ልጆች፤ ሱዋ፣ሐርኔፍር፣ሦጋል፣ቤሪ፣ይምራ፣
37ቤጼር፣ሆድ፣ሳማ፣ ሰሊሳ፣ይትራን፣ብኤራ።
38የዬቴር ወንዶች ልጆች፤ዮሮኒ፣ፊስጻ፣አራ።
39የዑላ ወንዶች ልጆች፤ኤራ፣ሐኒኤል፣ሪጽያ።
40እነዚህ ሁሉ የአሴር ዜሮች ናቸው።እነርሱም የቤተ ሰብ አለቆች፣ምርጥ ሰዎች፣ብርቱ ተዋጊዎችና ድንቅ መሪዎች ነበሩ።ለውጊያ ብቁ የሆኑት ወንዶች ቁጥር 26000 ነበር። 39የዑላ ወንዶች ልጆች፤ኤራ፣ሐኒኤል፣ሪጽያ። 40እነዚህ ሁሉ የአሴር ዜሮች ናቸው።እነርሱም የቤተ ሰብ አለቆች፣ምርጥ ሰዎች፣ብርቱ ተዋጊዎችና ድንቅ መሪዎች ነበሩ።ለውጊያ ብቁ የሆኑት ወንዶች ቁጥር 26000 ነበር።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።