1የእስራኤሌ በኩር ልጅ የሮቤል ልጆች፤ ሮቤል የበኩር ልጅ ቢሆንም፤ የአባቱን መኝታ ስላረከሰ፤ የበኩርናው መብቱ ለእስራኤል ልጅ ለዮሴፍ ልጆች ተሰጥቶአል። ከዚህም የተነሣ ትውልዱ የበኩርነቱን ተራ ይዞ ሊቁጥል አልቻለም።
2ይሁዳ ከወንድሞቹ ይልቅ ብርቱ ነበረ፤ ገዥ የወጣው ከእርሱ ቢሆንም፣ የበኩርነት መብቱ የተላለፈው ለዮሴፍ ነበረ።
3የእስራኤል የበኩር ልጅ የሮቤል ወንዶች ልጆች፤ ሄኖኅ፣ ፋሉሶ፣ አስሮን፣ ከርሚ ነበሩ።
4የኢዮኤል ዘሮች ልጁ ሽማያ፣ ልጁ ጎግ፣ ልጁ ስሜኢ፣
5ልጁ ሚካ፣ ልጁ ራያ፣ ልጁ ቢኤል፣
6የአጆር ንጉስ ቴልጌል ቴልፌልሶር ማኮር የወሰደው ልጅ ብኤራ ነበሩ።
7የቤተሰቡ የዘር ትውልድ በየጎሣ በየጎሣው ሲቁጠር እንደሚከተለው ነው፤ የጎሣ አለቃ የሆነው ኢዮኤል፣ ዘካርያስ፣
8የኢዮኤል ልጅ፣ እነዚህ ከአሮዔር እስከ ናባውና እስከ በኣልሜዎን ድረስ በሚገኘው ምድር ላይ ሰፈሩ።
9ከብቶቻቸው በገለዓድ ምድር በዝተው ስለነበር በምስራቅ በኩል ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ እስከ ምድረ በዳው ዳርቻ ድረስ የሚገኘውን ምድር ያዙ።
10በሳኦልም ዘመነ መንግሥት በእጃቸው ተመትተው ድል ከተደረጉት አጋራውያን ጋር ተዋጉ፤ በመላው የገለዓድ ምሥራቃዊ ክፍል የሚገኙትን መኖሪያዎቻቸውን ያዙ።
11የጋድ ነገድ ደግሞ ከእነርሱ ቀጥሎ እስከ ሰልካ ድረስ በሚገኘው በባሳን ምድር ኖሩ፤
12አለቃው ኢዮኤል፣ ሁለተኛው ሳፋም ከዚህም ያናይና ሰፋጥ ሆነው በባሳን ተቀመጡ።
13ቤተ ዘመዶቻቸውም በየቤተሰቡ እነዚህ ነበሩ፤ ሚካኤል፣ ሜሱላም፣ ሳባ፣ ዮራይ፣ ያካን፣ ዙኤ፣ ኦቤድ፣ ባጠቃላይ ስባት ነበሩ።
14እነዚህ ደግሞ የቢዝ ልጅ፣ የዬዳይ ልጆች፣ ኦቤድ፣ የኢዬሳይ ልጅ፣ የሚካኤል ልጅ፣ የገለዓድ ልጅ፣ የኢዳይ ልጅ፣ የዑሪ ልጅ፣ የሑሪ ልጅ፣ የአቢካኢል ልጆች ናቸው።
15የቤተሰባቸው አለቃ የኑጊ ልጅ፣ የአብዲኤል ልጅ አሒ ነበረ።
16እነዚህም በገለኣድ፣ በባሳንና እስከ ዳርቻዋ በሚገኙት መንደሮች እንዲሁም በሳሮን በሚገኙ የግጦሽ ስፍራዎች ሁሉና ከዚያም ወዲያ አልፈው ተቀመጡ።
17እነዚህ ሁሉ ትውልድ በመዝገብ የሰፈሩት በይሁዳ ንጉሥ በኢዮአታምና በእስራኤል ንጉሥ በኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት ነው።
18የሮቤል፣ የጋድና፣ የምናሴ ነገድ እኩሌታ አርባ አራት ሺህ ብቁ የጦር ሰዎች ነበሩአቸው። እነርሱም ጋሻ መያዝ፣ ሰልፍ መምዘዝና ቀስት መሳብ የሚችሉ ጠንካራና በውጊያ የሠለጠኑ ናቸው።
19እነዚህም በአጋራውያን፣ በኢጡር፣ በናፌስ፣ በናዳብ ላይ ዘመቱ።
20በጦርነቱም ላይ ወደ እግዚአብሔር ጮኸው ስለ ነበር፣ በውጊያው ረዳቸው፣ አጋራው ያንንና የጦር አጋሮቻቸውን ሁሉ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ስለ ታመኑበትም ፀሎታቸውን ሰማ።
21የአጋራውያንንም እንስሶች ማረኩ፤ እነዚህም አምሳ ሺህ ግመሎች፣ 250 000 በጎችና ሁለት ሺህ አህዮች ነበሩ። እንዲሁም 100 000 ሰው ማረኩ።
22ውጊያው የእግዚአብሔር ስለነበር ሌሎችም ብዙ ሰዎች ተገደሉ። እስከ ምርኮ ጊዜ ምድሪቱ በእጃቸው ነበረች።
23የምናሴ ነገድ እኩሌታ ህዝብ ቁጥር ብዙ ነበረ፣ እነርሱም ከባሳን ጀምሮ እስከ በኣልአርሞንዔም ድረስ ባለው ምድር ሰፈሩ፤ ይህም እስከ ሳኔር አርሞንዔም ተራራ ድረስ ማለት ነው።
24የየቤተሰቡ አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ ዔፌር፤ ይሽዒ፣ ኤሊኤል፣ ዓዝርኤል፣ ኤርምያ፣ ሆዳይዋ፣ ኢየድኤ፤ እነዚህ ጀግና ተዋጊዎች የታወቁ ሰዎችና የየቤተሰባቸው አለቆች ነበሩ።
25ይሁን እንጂ ለአባቶቻቸው አምላክ ታማኞች አልሆኑም፤ እግዚአብሔር ከፊታቸው ያጠፋቸው የምድሪቱን ከሕዝብ አማልክት በማምለክ አመነዘሩ
26ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የአሦርን ንጉሥ የፎሐት መንፈስ ይኸውም የቴልጌል ቴፌልሶርን መንፈስ አነሣሥቶ የሮቤልን፣ የጋድንና፣ የምናሴን ነገድ እኩሌታ ማርኮ እንዲወሰድ አደረገ። እነዚህንም ወደ ጎዛን ወንዝ ዳርቻ አፈለሳቸው፤ እነርሱም እስከ ዛሬ ድረስ በዚያ ይገኛሉ።