1የይሁዳ ዘሮች፤ ፋሬስ፣ ኤስሮም፣ ከርሚ፣ ሆር፣ ሦባል።
2የሦባል ልጅ ራያ ኢኤትን ወለደ፤ ኢኤትደግሞ አሑማይንና ላሃድን ወለደ፤ እነዝዝዚህ የጾርዓውያን ጎሣዎች ናቸው።
3የኤጣም ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ኢይዝራኤል፣ ይሽማ፣ ይደባሽ። እኅታቸው ሃጽሌልፎኒ ትባላለች።
4ፋኑኤል ጌዶርን ወለደ፤ ኤጽር ደግሞ ሑሻ ምን ወለደ። እነዚህ የኤፍራታ የበኩር ልጅና የቤተልሔም አባት የሆነው የሆር ዘሮች ናቸው።
5የቴቁሔ አባት አሽሑር፣ ሔላና ነዕራ የተባሉ ሁለቱ ሚስቶች ነበሩት።
6ነዕራም አሑዛምን፣ ኦፌርን፣ ቴምኒን፣ አሐሽታሪን ወለደችለት፤ የነዕራ ዘሮች እነዚህ ነበሩ።
7የሔላ ወንዶች ልጆች፤ ዴሬት፣ ይጽሐር፣ ኤትናን ናቸው።
8የቆጽ ወንዶች ልጆች ደግሞም ዓኑብ፣ ጾቤባና፣ የሃሩም ናቸው።
9ያቤጽ ከወንድሞቹ ይልቅ የተከበረ ሰው ነበረ፤ እናቱም "በጣር የወለድድኩት" ስትል ስሙን ያቤጽ አለችው።
10ያቤጽም፣ "አቤቱ፤ እንድትባርከኝ፣ ግዛቴንም እንድታሰፋልኝ እለምንሃለሁ፣ እጅህ ከእኔ ጋር ትሁን፣ ከሥቃይና ከጉዳትም ጠብቀኝ" በማለት ወደ እስራኤል አምላክ ጮኸ።እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።
11የሹሐ ወንድም ክሉብ ምሒርን ወለደ፤ ምሒርን ወለደ፤ ምሒርም ኤሽቶን ወለደ፤
12ኤሽቶን ቤትራፋንና ፋሴሐን ወለደ፤ የዒርናሐሽን ከተሞች የቁረቁረ እርሱ ነው። እነዚህ የሬካ ሰዎች ናቸው።
13የቄኔዝ ወንዶች ልጆች፤ ሐታት፣ መዖኖታይ።
14መዖታይ ደግሞ ዖፍራን ወለደ። ሠራያ የኢዮአብ አባት ሲሆን፣ ኢዮአብ ጌሐራሺምን ወለደ፤ የእደ ጥበብ ባለ ሙያዎች ስለ ነበሩ ይህ ስም ተሰጣቸው።
15የዮፎኔ ልጅ የካሌብ ወንዶች ልጆች፤ ዒሩ፣ ኤላ፣ ነዓም። የኤላ ልጅ ቄኔዝ።
16የይሃልኤል ወንዶች ልጆች፤ ዚፍ፣ ዚፋ፣ ቲርያ፣አሣርኤል።
17የዕዝራ ሜሬድ፣ዔፌር፣ያሎን። ከሜሬድ ሚስቶች እንዲቱ ማርያምን፣ ሽማይንና የኤሽትምዓን አባት ፅሽባን ወለደች።
18አይሁዳዊት ሚስቱም የጌዶርን አባት ዮሬድን፣ የጆኮን አባት ሔቤርን፣ የዛኖዋን አባት ይቁቲኤልን ወለደች፤ እነዚህም ሜሬድ ያገባት የፈርዖን ልጅ የቢትያ ልጆች ናቸው።
19የሆዲያ ሚስት የነሐም እኅት ወንዶች ልጆች፤ የገርሚው የቅዒላ አባት፣ ማዕካታዊው ኤሽትሞዓ።
20የሺሞን ወንዶች ልጆች፤ አምኖን፣ ሪና፣ ቤንሐናን፣ ቲሎን። የይሺዒ ዘሮች፤ ዞሔትና ቤንዞሔት።
21የይሁዳ ልጅ የሴሎም ወንዶች ልጆች፤ የሌካ አባት ዔር፣ የመሪሳና በቤት አሽቤዓ የበፍታ ጨርቅ ሠሪ የሆኑት ጎሣዎች አባት ለዓዳ፣
22ዮቂም፣ የኮዜባ ሰዎች፣ ኢዮአስ፣ ሞዓብን የገዛ ሣራፍና ያሹቢሌሔም። ታሪካቸውም ጥንታዊነት ያለው ነው።
23ሰዎቹ ነበጣዒምና በጋዴራ የሚቀመጡ ሸክላ ሠሪዎች ነበሩ፤ በዚያም በመቀመጥ ለንጉሡ ሸክላ ይሠሩ ነበር።
24የስምዖን ዘሮች፤ ነሙኤል፣ ያሚን፣ ያሪን፣ ዛራ፣ ሳኡል፣
25ሰሎም የሳኡል ልጅ ነው፤ መብሳም የሰሎም ልጅ ነው፤ ማስማዕ ደግሞ የመብሳም ልጅ ነው።
26የማስማዕ ዘሮች ልጁ ሃሙኤል፣ ልጁ ዘኩር፣ ልጁ ሰሜኢ።
27ሰሚኤ ዐሥራ ስድስት ወንዶችና ስድስት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ ወንድሞቹ ግን ብዙ ልጆች አልነበሯቸው፤ ስለዚህ ጎሣቸው በሙሉ እንደ ይሁዳ ሕዝብ ብዙ አልነበረም።
28የኖረባችውም ቦታዎች እነዚህ ናቸው። ቤርሳቤህ፣ ሞላደ፣ ሐጻርሹዓል፣
29ቢልሃ፣ ዔጼም፣ ቶላድ፣
30ቤቱኤል፣ ሔርማ፣ ፊቅላግ፣
31ቤትማርካቦት፣ ሐጸርሲሲም፣ ቤትቢሪ፣ ሽዓራይም፣ እስከ ዳዊት ዘመነ መንግስት ድረስ የኖሩት በእነዚህ ከተሞች ነው።
32በአካባቢያቸው የሚገኙት ወንደሮች ደግሞ ኤጣም፣ ዓይን፣ ሬሞን፣ ቶኬን፣ ዓሻን የተባሉ አምስት ከተሞች ናቸው፤
33በእነዚህ ከተሞች ዙሪያ በአል የሚዝችልቁ መንደሮች ነበሩ፤ መኖሪያቸው በዚሁ ሲሆን፤ የትውልድ መዝገብም አላቸው።
34ሞሾብብ፣ የምሌክ፣ የአሜስያስ ልጅ ኢዮስያስ፣
35ኢዮኤል፣ የዮሺብያ ልጅ፣ የሠራያ የዓጂኤል ልጅ ኢዩ
36እንዲሁም ኤልዩዔናይ፣ ያዕቆብ፣ ፅሾሐያ፣ ዓሣያ፣ ዓሲዔል፣ ዩሲምኤል፣ በናያስ፣
37የሺፊ ልጅ ዚዛ፣ የአሎን ልጅ፣ የይዳያ ልጅ፣ የሺምሪ ልጅ፤ የሸማያ ልጅ፤
38እነዚህ ስማቸው ከላይ የተዘረዘረው ሰዎች የየጎሣቸው መሪዎች ነበሩ፤ የቤተሰባቸው ብዛት እጅግ በጣም እየጨመረ ሄደ፤
39እነርሱም ለከብቶቻቸው ግጦሽ ፍለጋ ከሸለቆው በስተምስራቅ እስካለው እስከ ጌደር መግቢያ ድረስ ዘልቀው ሄዱ።
40በዚያም ለምለምና ያማረ የግጦሽ ቦታ አገኙ፤ ምድሪቱም ሰፊ፤ ሰላምና ጸጥታ የሰፈነበት ነበረች። በቀድሞ ቀመን በዚህ ምድር ይኖሩ የነበሩት አንዳንድ የካም ዘሮቼ ናቸው።
41እነዚህ ስማቸው ከላይ የተዘረዘሩው ወደዚሁ ቦታ የመቱት በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን ነበረ፤ እነርሱም በድንኳኖቻቸው ውስጥ በነበሩበት በካም ወገኖችና በምዑናውያን ላይ አደጋ በመጣል ፈፅመው አላጠፋአቸው፤ ይህም እስከ ዛሬ ድረስ በግልጽ ይታያል። ለመንጎቻቸው በቂ ግጦሽ ቦታ ስላላገኙ፣ በዚያ መኖር ጀመሩ።
42ከእነዚሁ አምስት መቶ የሚሆኑ የስምዖን ወገኖች በይሽዒ ልጆች በፈላጥያ፣ በነዓርያ፣ በረፋያና በዑዝኤል ተመርተው የሴይርን ኩረብታማ አገር ወረሩ።
43አምልጠው የቀሩትን አማሌቅውያን ፈጅተው እስከ ዛሬ በዚያው ይኖራሉ።