1ዳዊት በኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ የነገዱን የጦር አለቆች፣ ንጉሡን የሚያገለግሉትን የክፍለ ጦር አዛዦች፣ የሻለቆቹን፣ የመቶ አለቆቹን፣ የንጉሥና የልጆቹ ንብረትና ከብት ሁሉ ኅላፊ የሆኑትን፣ እንዲሁም የቤተ መንግሥቱን ሹማምት፣ ኅያላንና ጀግና ተዋጊዎቹን፣ በአጠቃላይ የእስራኤልን ሹማምት ሁሉ ጠራ።
2ከዚያም ንጉሥ ዳዊት በእግሩ ቆሞ እንዲህ አላቸው፤ "ወንድሞቼንና ወገኖቼ ሆይ፤ እስቲ አድምጡኝ፤ እግዚአብሔር ለቃል ኪዳኑ ታቦት ማደሪያና ለአምላካችን እግር ማረፊያ የሚሆን ኔት ለመሥራት ዐስቤ ዕቅድ አውጥቼ ነበር።
3እግዚአብሔር ግን እንዲህ አለኝ፤ ጦረኛ ለስሜ ቤት አትሠራም።
4ነገር ግን የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ለዘላለም እንድነግሥ ከቤተሰቤ ሁሉ እኔን አረጠ፤ መሪ እንድሆንም ይሁዳን መረጠ፤ ከአባቴ ልጆች መካከል ደግሞ በመላው እስራኤል ላይ እንድነግሥ ፈዋዱ ሆነ።
5እግዚአብሔር ብዙ ልጆች ሰጥቶኛል፤ ከወንዶቹ ልጆቼ ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት ዙፋን ላይ ተቀምጦ በእስራኤል ሁሉ ላይ እንዲነግሥ ደግሞ ልጄን ሰሎሞንን መርጦታል።
6እንዲህም አለኝ፤ ቤቴንና አደባባዮቼን የሚሠራልኝ ልጅህ ሰሎሞን ነው፤ ምክንያቱም ልጄ እንዲሆን መርጩዋለሁ፤ እኔም አባት እሆነዋለሁ።
7አሁን እንደሚያድርገው ሁሉ፤ ትህዛዛቶቼንና ሕጎቼን ምንጊዜም ሳያውላውል የሚፈጽም ከሆነ መንግሥቱም ለዘላለም አጸናታለሁ።
8እንግዲህ አሁንም ይህቺን መልካሚቱን ምድር እንድትወርሱና ለልጆቻችሁም የዘላለም ርስት አድርጋችሁ እንድታወርስይአቸው፣ የእግዚአብሔርም ትእዛዝ ሁሉ ፊት፣ በእግዚአብሔር ጉባኤና እግዚአብሔር እየሰማ አዛችኋለሁ።
9"አንተም ልጄ ሰሎሞን ሆይ! እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ስለሚመረምርና ሐሳብን ሁሉ ስለሚያውቅ፣ የአባትህን አምላክ ዕወቅ፤ በፍጹም ልብና በበጎ ፍቃድ አገግለው።
10ለመቅደስ የሚሆን ቤት እንድትሠራ እግዚአብሔር የመረጠህ መሆኑን አሁንም ዕስብ፤ በትርተህም ሥራ።
11ከዚያም ዳዊት የቤተ መቅደሱን መመላለሻ፣ የሕንጻውን፣ የዕቃ ቤቶቹን፣
12የፎቁንና የውስጥ ክፍሎቹን እንዲሁም የማስተሰሪያውን ቦታ ንድፍ ለልጁ መንፈስ ቅዱስ በልቡ ያሳደረውን የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አደባባይ፤ በዙሪያው ውያሉትን ክፍሎች ሁሉ፣ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ዕቃ ቤቶችና የንዋይ ቅድሳቱን ግምጃ ቤቶች ንድፍ ሁሉ ሰጠው፤
13እንዲሁም የካህናቱንና የሌዋውያኑን አመዳደብ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎት ሥራና ለአገልግሎቱ ስለሚጠቀምባቸው ዕቃዎች ሁሉ መመሪያ ሰጠው።
14ልዩ ልዩ አገልግሎት የሚውሉትን የወርቅ ዕቃዎች ሁሉ መጠን፤ ልዩ ልዩ አገልግሎት የሚውሉትን የብር ዕቃዎች ሁሉ መጠን አሳወቀው፤
15እንደሚቀዞችና ለቀንዲሎቻቸው የሞሆነው የእያንዳንዳቸውን የውርቅ መጠን፤ ለብሩ መቅረዞችና ለቀንዲሎቻቸው የሚያድፈልገውን የእያንዳንዳቸውን የብር መጠን፤
16ለያንዳንዱ ኅብስት ገጽ ጠረጼዛ የሚያስፈልገውን የወርቅ መጠን፣ ለእያንዳንዱ የብር መጠን፣
17ለሹካዎቹ፣ ለጎዳጓዳ ሳሕኖቹ፣ ለማንቆርቆሪያዎች የሚያስፈልገውን ንጹሕ የውርቅ መጠን፤ ለእያንዳንዱ የብር መጠን፣
18ለዕጣኑ መሠዊያ የሞሆነውን የጠራ ውርቅ መጠን እንዲሁም ክንፎቻቸውን ዘርግተው የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑን ታቦት የሚሸፍኑት ከወርቅ የተሠሩትን የኪሩቤል ጀረገላዎች ንድፍ ሰጠው።
19ዳዊትም "ይህ ሁሉ፣በእኔ ላይ ባለው በእግዚአብሔር እጅ በጽሑፍ ተገለተልኝ፤ የንድፋንም ዝርዝር እንድረዳ ማስተዋልን ስጠን"አለ።
20ደግሞም ዳዊት ልጁን ሰሎሞንን እንዲህ አለው፤ "እንግዲህ በል በርታ፤ ጠንክር፤ ሥራውንም ጀመር። አትርፍ፤ ተስፋም አትቁረጥ፤ እግዚአብሔር አምላኬ ከአንተ ጋር ነውና፤ እርሱም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎት ሥራ እስኪፈጸም ድረስ አይተውህም፤ አይጥልህም።
21ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሥራ ሁሉ የሚያስፈልጉትን ካህናትና ሌዋዋን ምድብም ዝግጁ ነው።በሁሉም የእጅ በሥራው ሁሉ ይረዱሃል። ሹማምቱና ሕዝቡ ሁሉ ትእዛዝህን ይፍፈጽማሉ።