1ከዚያም ንጉሥ ዳዊት ለመላው ጉባኤ እንዲህ አለ፤ "እግዚአብሔር የመረጠው ልጄ ሰሎሞን ገና ወጣትና ልምድም የሌለው ነውው። ይህ ታላቅ ሕንጻ የሚሠራውን ለሰው ሳይሆን ለእግዚአብሔ አምላክ በምሆን፣ ጅራው ከባድ ነው።
2እኔም ያለኝን ሀብት ለአምላኬ ቤተ መቅደስ ለወርቁ ሥራ ወርቁን ለብሩ ሥራ ብሩን፣ ለናስ ሥራ ናሱን፣ ለብረቱ ሥራ ብረቱን፣ ለዕንጨቱ ጅራ ዕንጨቱን እንዲሁም ለፈርጥ የሞሆነው መረግድ፣ ኬልቄዶን፣ ልዩ ልዩ ኅብር ያላቸውን ዐይነት የሚያምር ድንጋይና ዕብነበረድ፣ ይህን ሁሉ በብዛት አዘጋጅቻለሁ።
3ከዚህም በቀር ለአምላኬ ቤት ካለን ፍቅር የተነሣ ለዚህ ለተቀደሰ ቤት ከዚህ በፊት ከሰጠሁት በተጨማሪ ለዚሁ ለእግዚአብሔር ቤተ ምቅደስ የግል ሀብቴ የሆነውን ወርቅና ብር እሰጣለሁ፤
4ይህም ሦስት ሺህ መክሊት ንጹሕ ብር ለቤተ መቅደሱ የግድግዳ ግንብ ማስጌጫ
5እንዲሁም ለወርቁ ሥራ፣ ለብሩ ሥራ፣ በባለሞያዎች ለሚሠራው ሥራ ሁሉ የሚሆን ነው። ታዲያ ዛሬ ራሱን ለእግዚአብሔር ለመቀደስ ፍቃደኛ የሚሆን ማን ነው?።
6ከዚያም የቤተሰቡ አሪዎች፣ የነገዱ የእስራኤል ሹማምት፣ የሻለቆችና የመቶ አለቆች እንዲሁም በንጉሥ ሥራ ላይ የተመደቡ ሹማምት፣ በፍቃዳቸው ሰጡ፤
7ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሥራ የሰጡትም አምስት ሺህ መክሊት ወርቅ፣ ዐሥር ሺህ ዳሪክ ወርቅ፣ ዐሥር ሺህ መክሊት ናስ አንድ መቶ ሺህ መክሊት ብረት ነው።
8የከበሩ ድንጋዮች ያለውም ሁሉ፣ በጌድሶናዊው በይሒኤል አማካኝነት ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ግምጃ ቤት አስገባ።
9ስጦታው በገዛ ፈቃደና በፍጹም ልብ የቀረበ በመሆኑ፣ አለቆች ስላደረጉት የብበጎ ፈቃድ ስጦታ ሕዝቡ ደስ አለው፤ ንጉሥ ዳዊትም እንደዚሁ እጅግ ደስ አለው።
10ዳዊትም በመላው ጉባኤ ፊት እግዚአብሔር እንዲህ ሲል አመሰገነ፤ "የአባታችን የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ከዘላለም እስከ ዘላለም ለአንተ ምስጋና ትሁን።
11እግዚአብሔር ሆይ፤ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ ለአንተ ነውና፤ ታላቅነት፣ ኅይል ክብርና ግርማ የአንተ ነው። እግዚአብሄር ሆይ፤ መንግሥትህም የአንተ ነው፤ አንተም እንደ ራስ ከሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያልህ ነህ።
12ባለጠግነት ክብር የሚገኘው ከአንተ ነው፤ አንተም የሁሉ ገዢ ነህ፤ ከፍ ከፍ ለማድረግ፣ ለሁሉም በርታትን ለመስጠት፣ ብርታትና ኅይል በእጅህ ነው።
13አምላካችሁ ሆይ፤ አሁንም እናመሰግንሃለን፤ ለከበረው ስምህም ውዳሴ እናቀርባለን።
14"ሁሉ የተገኘው ከአንተ ነው፤ ለአንተም የሰጠንህ ከእጅህ የተቀበልነው ብቻ ነው። ታዲያ እንዲህ ያለ ቸርነት እናድርግ ዘንድ እኔ ማነኝ? ሕዝቤስ ማንኝ?
15እኛም እንደ ቀድሞ አባቶቻችን በፊትህ መጻተኞችና እንግዶች ነን፤ ዘመናችንም በምድር ላይ እንደ ጥላ ነው፤ ተስፋ ሲስም ነው።
16እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤ ለተቀደሰው ስምህ ቤተ መቅደስ እንሠራለን ዘንድ ይህ በብዛት ያዘጋጀውን ሁሉ፤ ከእጅህ የተገኘውና ሁሉም ለአንተ ነው።
17አምልኬ ሆይ፤ ልብን እንደምትመረምርና ቅንነትን እንደምትወድ ዐውቃለሁ፤ እኔም ይህን ሁሉ የሰጠሁት በበጎ ፈቃደና በቀና መንፈስ ነው። አሁንም በዚህ ያለው ሕዝብህ በበጎ ፈቃዱ እንዴት እንደ ሰጠ አይቻለሁ።
18የአባታቸው የአብርሃም፣ የይስሐቅ፣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህን ዐሳብ ለዘላለም በሕዝብህ ልብ ጠብቀው፤ ልባቸውንም ለአንተ ታማኝ አድርገው።
19ትእዛዞችህን፣ እኔ ባዘጋጀሁለት ነገሮች ታላቅ ህንጻ ለመጅራት እንዲችል፣ ለልጄ ለሰሎሞ ፍጹም ፈቃደኛነት ሰጠው።
20ከዚያም ዳዊት ለመላው ጉባኤ፣ "አምላካችሁን እግዚአብሔር ወሰዱት" አላቸው። ስለዚህ የአባታቻችን አምላክ እግዚአብሔር ወደሱ፤ በእግዚአብሔር በንጉሡም ፊት ተደፍተው ሰገዱ።
21በማግስቱም ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ሠው፤ የሚቃጠል መስሥዕዋትም አቀረቡ፤ ይህም አንንድ ሺህ ወይፈን፣ አንድ ሺህ አውራ በግ፣ አንድ ሺህ የበግ ጠቦት ሲሆን፤ ከመጠጥ ቁርባኖቻቸውና ከሌሎች መሥዕዋቶች ጋር ስለ እስራኤል ሁሉ በብዛት አቀረቡ።
22በዚህችም ዕለት በእግዚአብሔር ፊት በታላቅ ደስታ በሉ፤ ጠጡም። ከዚያም የዳዊት ልጅ ሰሎሞን ንጉሥ መሆኑን ሁለተኛ ጊዜ በይፋ ዐወቁ፤ ገዥ እንዲሆንም በእግዚአብሔር ፊት ቀቡት፤
23ሰለሞንም ነግሦ በአባቱ በዳዊት ምትክ በእግዚአብሔር ዙፋን ላይ ተቀመጠ፤ ተከናወነለት፤ እስራኤልም ሁሉ ታዘዙለት።
24የጦር አለቆችና ኅያላኑ ሁሉ እንዲሁም የንጉሥ የዳዊት ወንዶች ልጆች በሙሉ ታማኝነታቸውን ለንጉሥ ሰሎሞን አረጋ ገጡለት።
25እግዚአብሔር ሰሎሞንን በእስራኤል ሕዝብ ዘንድ ሁሉ እጅግ ከፍ ከፍ አደረገው፤ ከእነሱ በፊት ለነበሩት የእስራኤል ነገሥታት ያላጎናጸፋቸውን ንጉሣዊ ክብር ሁሉ ሰጠው።
26የእሴይ ልጅ ዳዊት በእስራኤል ሁሉ ላይ ነግሦ ነበር።
27እርሱም በኬብሮን ሰባት ዓመት፤ በእየሩሳሌም ሠላሳ ሦስት ዓመት፣ በአጠቃላይ አርባ ዓመት ነገሠ።
28ብዙ ዘመን ባለጠግነትና ክብር ሳይጎድልበት ዕድሜ ጠግቦ ሞተ፤ ጅጁ ልምሞን በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።
29በንጉሥ ዳዊት ዘመነ መንግሥት ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻ የተከናወነው ድርጊት በባለ ራእዩ በሳሙኤል የታሪክ መጽሐፍ፣ በነብዩ በናታን የታሪክ መጽሐፍ ተጽፎአል።
30የተጻፈውም በሥልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ ከፈጸማቸው ዝርዝር ጉዳዮችና በዙሪያው ከከበቡት፤ ከእስራኤልና ከሌሎች አገር መንግሥታት ታሪክ ጋር ነው።