መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

1ኛ ዜና 27

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የእስራኤል የቤተሰብ አለቆች፣ የሻልለቆች፣ መቶ አለቆች እንዲሁም ዓመቱን ሙሉ በየወሩ አለቆች እንዲሁም ዓመቱን ሙሉ በየወሩ የሚመደቡትና ዋና ዋና ክፍሎች በተመለከተ ንጉሡን ያገለገሉ አለቆቻቸው ዜርዜር ይህ ነው። እያንዳንዱ ዋና ክፍል ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረው።
2በመጀመሪያው ወር የመጀመሪያው ዋና ክፍል የበላይ የዘብድኤል ልጅ ያሾብዓም ሲሆን፣ በሥሩ የሚታዘዙ ሃያ አራት ሺህ ሰዎች ነበሩ።
3እርሱም የፋሬስ ዘር ሲሆን፣ በመጀመሪያው ወር የሰራዊቱ ሹማምት ሁሉ የበላይ ነበር።
4በሁለተኛው ወር የክፍለ ጦሩ የበላይ አዛዥ ኢሆሃዊው ዱዲ ሲሆን፣ የዚሁ ክፍል መሪ ደግሞ ሚቅሎት ነው፤ በጅሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።
5በሦስተኛውም ወር የሦስተኛው ክፍለ ጦር የበላይ አዛዥ የካህኑ የዮዳሄ ልጅ በናያስ ነበረ፤ ዋናው እርሱ ሲሆን፤ በሥሩ ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።
6ይህም ከሠላሳዎቹ ይልቅ ኅያል ሲሆን፤ የሠላሳዎቹ የበላይ ነበረ፤ ልጁ ዒሚዛባድም የክፍሉ ሰራዊ አዛዥ ነበረ።
7በአራተኛው ወር አራተኛው የበላይ አዛዥ የኢዮአብ ወንድም አሣሣል ሲሆን፤ በእግሩ የተተካውም ልጁ ዝባድያ ነው፤ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።
8በእብምስተኛው ወር አምስተኛው የበላይ አዛዥ ይዝራዊው ሸምሁት ሲሆን፤ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።
9በስድስተኛው ወር ስድስተኛው የበላይ አዛዥ የቴቁሐዊው የዒስካ ልጅ ዒራስ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።
10በሰባተኛው ወር ሰባተኛው የበላይ አዛ የኤፍሬም ወገን የሆነው ፍሎናዊው ሴሌስ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።
11በስምንተኛው ወር ስምንተኛው የበላይ አዛዥ ከካዛራውያን ወገን የሆነው ኩሳታዊ ሲቦካይ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።
12በዘጠነኛው ወር ዘጠነኛው የበላይ አዛዥ ከብንያም ወገን የሆነው ዓናቶታዊው አቢዔዘር ሲሆን፣በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።
13በዐሥረኛው ወር ዐሥረኛው የበላይ አዛዥ ከከዛራውያን ወገን የሆነው ነጦፋዊው ኖኤሬ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።
14በዐሥራ አንደኛው ወር እስራ አንደኛው የበላይ አዛዥ ከኤፌሬም ነገድ የሆነው ጲርዓቶናዊው በናያስ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።
15በዐሥራ ሁለተኛው ወር ዐሥራ ሁለተኛ የበላይ አዛዥ ከጎቶንያል ቤተሰብ የሆነው ነጦፋዊው ሔልዳይ ነበረ፤ በጅሩም ሃያ አራት ሰው ነበረ።
16የየነገዱ የእስራኤል የጦር ሹማምት፤ በሮቤል ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዝክሪ ልጅ አልዓዛር፤ በስምዖን ነገድ ላይ የተሶመው፣ የመዓካ ልጅ ሰፍጢያስ።
17በሌዊ የተሾመው የቀሙኤል ልክ ሐሸቡያ፤ በእሮን ነገድ ላይ የተሾመው፣ ሳዶቅ።
18በይሁዳ ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዳዊት ወንድም ኤሊሁ፤ በይሳኮር ነገድ ላይ የተሾመው፣ የሚካኤል ልጅ ዖምሪ።
19በዛቢሎን ነገድ ላይ የተሾመው፣ የአብዱዩ ልጅ ይሽማያ፤ በንፍታሌም ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዓዝሪኤል ልጅ ኢያሪሙት።
20በኤፍሬም ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዓዝያ ልጅ ሆሴዕ፤ በምናሴ ነገድ እኩሌታ ላይ የተሾው፣ የፈዳያ ልጅ ኢዩኤል።
21በገለዓድ ባለው የምናሴ ነገድ እኩሌታ ላይ የተሾመው፣ የዛካርያስ ልጅ አዶ፣ በብንያም ነገድ ላይ የተሾመው፣ የአቤኔር ልጅ የዕሢኤል።
22በዳን ነገር ላይ የተሶመው፣ የይህሮም ልጅ ዓዛርኤል፤ እንግዲህ የእዝራኤል ነገድ እነዚሁ ነበሩ።
23እግዚአብሔር እስራኤልን እንደ ሰማይ ክዋክብት እንደሚያዛቸው ሃያና ከዚያ በታች ይየሆነው አልቁጠረም ነበር።
24የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ መቁጠር ጀመረ፤ ሆኖም አልፈፀመውም፤ መቁጠራቸው በእስራኤል ላይ ቁጣ ስላመጣ፣ የተቁጠረውም በንጉሥ ዳዊት መዝገብ አልገባም።
25የዓዲኤል ልጅ ዓዝሞት የቤተ መንግሥቱ ዕቃ ኅላፊ ነበረ፤
26የክሉብ ልጅ ዔዝሪ ምድሪቱም ለሚያርሱት ገበሬዎች ኅላፊ ነበረ።
27ራማታዊው ስሜኢ የውይን ተክል ቦታዎች ኅላፊ ነበረ፤ ሽፋማዊው ዘብዲ የወይን ጠጅ ዕቃ ኅላፊ ነበረ።
28ጌድራዊው በአሐናን በምራባዊው ኩረብታዎች ግርጌ ለሚገኙት የወይንና የወርካ ዛፎች ጥበቃ ኅላፊ ነበረ፤ ኢዮአስ የዘይት ቤቱ ኅላፊ ነበረ።
29ሳሮናዊው ሰጥራይ በሳሮን ለሚሰሩት የከብት መንጋዎች ኅላፊ ነበረ። የዓድላይ ልጅ ሻፋጥ በሸለቆው ውስጥ ላሉት የከብት መንጋዎች ኅላፊ ነበረ።
30እስማኤላዊው ኡቢያስ የግመሎች ኅላፊ ነበረ። ሜሮታዊው ዬሕድያ የአህዮች ኅላፊ ነበረ።
31አረጋዊው ያዚዝ የበግና የፍየል መንጋዎች ኅላፊ ነበረ።
32አስተዋይ የሆነው አጎት ዮናታን አማካሪና ጸሐፊ ነበረ፤ የሐክሞኒም ልጅ ይሒኤል ደግሞ የንጉሥ ልጆች ሞግዚት ነበረ።
33አኪጦፌል የንጉሥ አማካሪ ሲሆን፣ አርካዊው ኩሲ ደግሞ የንጉሥ ልጆች ሞግዚት ነበረ። አኪጦፌል የንጉሥ አማካሪ ሲሆን፣ አርካዊው ኩሲ ደግሞ የንጉሥ ወዳጅ ነበረ።
34የበናያስ ልጅ ዮዳሄና አብያታር በአኪጦፌል እእግር ተተኩ። ኢዮአብም የንጉሥ የክብር ዘብ አዛዥ ሆነ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።