መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

1ኛ ዜና 26

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

16 የቤተ መውደሱ በር ተባቂዎች አመዳደብ፤ ከቆሬያውያን ወገን፤ ከአሳፍ ወንዶች ልጆች አንዱ የሆነው የቆሬ ወንድ ልጅ ሜሱላም።
2ሜሱላም ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ የመጀመሪያው ዘካሪያስ ሁለተኛው ይዲኤል፣ ሦስተኛው ዮዛባት፣ አራተኛው የትኒኤል፣
3አምስተኛው ኤላም፣ ስድስተኛው ይሆሐናን፣ ሰባተኛው ኤሊሆዔናይ።
4ዖቤድኤዶምም እንደዚሁም ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ የመጀመሪያው ሽማያ፣ ሁለተኛው ዮዛባት፣ ሦስተኛው ኢዮአስ፣ አራተኛው ሣካር፣ አምስተኛው ናትናኤል፣
5ስድስተኛው ዓሚኤል፣ ሰባተኛው ይሳኮር፣ ስምንተኛው ፒላቲ፤ እግዚአብሔር ዖቤድኤዶምን ባርኮታልና።
6እንዲሁም ልጁ ሽማያ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነሱም በቂ ችሎታ ስለነበራቸው የአባታቸው ቤት መሪዎችች ሆኔ ነበር።
7የሽማያ ወንዶች ልጆች፤ ዖትኒ፣ ራፋቼል፣ ዖቤድ፣ ኤልዛባድ፣ ዘመዶቹ ኤሊሁና ስማክያም እንደዚሁ በቂ ችሎታ ነበራቸው።
8እነዚሁ ሁሉ የዖቤድኤዶም ዘሮች ሲሆኑ፣ እነሱም ሆኑ ወንዶች ልጆቻቸውና ቤተ ዘመዶቻቸው ሥራውን ለመጅርት በቂ ችሎታ ነበራቸው። የዖቤድኤዶም ዘሮች ባጠቃላይ ሥልሳ ሁለት ነበሩ።
9ሜሱላም በቂ ችሎታ ያላቸው ወንዶች ልጆችና ቤተ ዘመዶች ነበሩ፤ ቁጥራቸውም ባጠቃላይ ዐሥራ ሁለት ነበሩ።
10ከሜራሪ ወገን የሆነው ሖሳ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ የመጀመሪያው ሽምሪ ነበረ፤ የበኩር ልጅ ባይሆንም እንኳን አባቱ ቀዳሚ አድርጎ ነበር።
11ሁለተኛው ኬልቅያስ፣ ሦስተኛው ጥበልያ፣ አራተኛው ዘካሪያስ፤ የሖሳ ወንዶች ልጆች ቤተ ዘመዶቹ ባጠቃላይ ዐሥራ ሦስት ነበሩ።
12የቤተ መቅደሱም ጠባቂዎች በአለቆቻቸው ሥር ተመድበው ልክ እንደ በተ ዘመዶቻቸው ሁሉ እግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሥራ ለማከናውን ምድብ ተራ ነበራቸው።
13ለእያንዳንዱም በር ወጣት ሽማግሌ ሳይባል ለሁሉም እኩል ዕጣ ተጣለ።
14የምስራቁ በር ዕጣ ለሴሌምያ ወጣ።ከዚያም ምክር ዕዋቂ ለሆነው ለልጁ ለዘካሪያስ ዕጣ ጣሉ፤እርሱም የሰሜኑ በር ደረሰው።
15የደቡብ በር ዕጣ ለዖቤኤዶም ሲወጣ፤ የግምጃ ቤቱ ዕጣ ደግሞ ለልጆቹ ወጣ።
16የምዕራቡ በርና በላይኛው መንገድ ላይ የሚገኘው የሸሌኬት በር ዕጣዎችች ለሰፊንና ለሖሳ ወጣ።
17በአንዱ ዘብ ጥበቃ ትይዩ ሌላ ዘብ ትበቃ ነበረ፣ በየቀኑም በምሥራቅ በኩል ስድስት፤ በሰሜን በኩል አራት፣ በደቡብ በኩል አራት፣፣ በዕቃ ቤቱ በኩል በአንድ ሂዜ ሁለት ሌዋውያን ይጠብቁ ነበር።
18በምዕራቡ በኩል የሚገኘው አደባባዩ ደግሞ ሁለት ሆነው ይጠብቁ ነበር።
19እንዲህ የቆየና የሜራሪ ዘሮች የሆኑት በር ጠባቂዎች ድልድይ ይህ ነበር።
20ከሌዋውያን መካከል አኪያ የእግዚአብሔር ቤት ግምጃ ቤትና የተቀደሱት ዕቃዎች የሚቀመጡበት ግምጃ ቤት ኅላፊ ነበረ።
21የለአዳን ዘሮች፣ በለኣዳን በኩል ጌድሶናውያን የሆኑትና ለጌድሶዊው ለለአዳን ቤተሰቦች አለቆች የሆኑት ለለአዳን ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤ ይሒኤሊ፣
22የይሒኤሊ ወንዶች ልጆች፣ ዜቶምና ወንድሙ ኢዩኤል። እነዚህም እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ግምጃ ቤት ኅላፊዎች ነበሩ።
23ከእንበረማውያን፣ ከይስዓራውያን፣ ከኬብሮናውያን፣ ለዑዝኤላውያን፤
24የሙሴ ልጅ የግርሳም ዘር የሆነው ሱባኤል የግምጃ ቤቱ የበላይ ኅላፊ ነበረ።
25በአልዓዛር በኩል የሚዛመዱት፤ ልጁ ረዓብያ፣ ልጁ የሻያ፣ ልጁ ኢዮራም ልጁ ዝክሪ፣ ልጁ ሰሎሚት።
26ሰሎሚትና የሥጋ ዘመዶቹ ንጉሥ ዳዊት፣ የቤተሰቡ ኅላፊዎች፣ የሻለቆችና የመቶ አለቆች እንዲሁም ሌሎች የሰራዊቱ አዦች ቀድሰው ላቀረቧቸው ንዋያት ቅድሳት ኅላፊዎች ነበሩ።
27በጦርነቱ ከተገኘውም ምርኮ ከፊሉን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ማደሻ እንዲሆን ቀደሱት።
28ባለ ራእይ ሳሙኤል፣ የቂስ ልጅ ሳኦል፣ የኔር ልጅ አቤኔር፣ ቅድሳት ሰሎሚናትና ቤተ ዘመዶቹ ይጠብቁ ነበር።
29ከይስዓራውያን፤ ከናንያና ወንዶች ልጆቹ ከቤተ መቅደሱ ውጭ ባለው ሥራ በእስራኤል ላይ ሹማምትና ዳኞች ሆነው ተመደቡ።
30ከኬብሮናውያን፤ ሐሽብያ፣ ጠንካራና ጎበዝ የሆኑ ሺህ ሰባት መቶ ሰዎች ከዮርዳኖስ በሰተ ምዕራብ በሚገኘው የእስራኤል ምድር ላለው የእግዚአብሔር ሥራና ለንጉሥም አገልግሎት ኅላዎች ሆነው ተመደቡ።
31በኬብሮናውያን በኩል በቤተሰቦቻቸው የትውልድ መዝገብ መሠረት ይሪያ አለቃቸው ነበረ። በዳዊት ዘመነ መንግሥት በአርባኛው ዓመት መዛግብቱ ተመርምረው ስለ ነበር፣ በገለዓድ ውስጥ ኢያዜ በተባለ ቦታ ከኬብሮናውያን መካከል ጠንካራ ሰዎች ሊገኙ ችለዋል።
32ይሪያም ጠንካሮችና የቤተሰባቸው አለቆች የሆኑ ሁለ ሺህ ሰባት መቶ ሥጋ ዘመዶች ነበሩት። ንጉሥ ዳዊትም እነዚህን የእግዚአብሔር ለሆነውና የንጉሥም በሆነው ጎዳይ ላይ ሮቤልን፣ ጋድንና የምናሴ ነገድ እኩሌታ ኅላፊ አድርጎ ሾማቸው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።