1ዳዊት ከሰራዊቱ አለቆች ጋር ሆኖ በመሰንቆ፣ በበገና በጽናጽል ድምፅ እየታጀቡ ትንቢት የሚናገሩትን ከአሳፍ፣ ከኤማንና ከኤዶም ቤተሰብ መካከል መርጦ መደብ፤ ይህን አገልግሎት የሚያከናውኑትም ሰዎች ዝርዝር እንደ ሚከተለው ነው፤
2ከአሳፍ ወንዶ ልጆች፤ ዘኩር፣ ዮሴፍ፣ ነታንያ፣ አሼርኤላ። እአሳፍ ልጆች በአሳፍ አመራር ሥር ነበሩ፤ አሳፍም በንጉሥ አመራር ሥር ነበረ።
3ከኤዶምወንዶች ልጆች፤ ዶልያስ፣ ጽሪ፣ የሻያ፣ ሰሜኢ፣ ሐሸብያ፣ መቲትያ። እነዚህ ስድስቱ በመሰንቆ እግዚአብሔርን እያመሰገነና እየወደሰ ትንቢት በተናገረው አባታቸው በኤዶታም አመራር ሥር ነበሩ።
4ከኤማን ወንዶች ልጆች፤ ቡቅያ፣ መንታያ፣ ዓዛርዔል፣ ሱባኤል፣ ኢያሪሙት፣ ሐናንያ፣ ናኒ፣ ኤልያታ፣ ጊዶልቲ፣ ሮማንቲዔዘር፣ ዮሽብቃሻ፣ መሎቲ፣ ሆቲር፣ መሐዝዮት።
5እነዚህም ሁሉ የንጉሡ ባለራእይ የኤማን ልጆች ነበሩ። እርሱን ከፍ ከፍ እንዲያደርጉትም እግዚአብሔር በገባለት ቃል መሠረት ተሰጡት፤ እግዚአብሔር ለኤማን ዐሥራ አራት ወንድሞችና ሦስት ሴቶች ልጆች ሰጠው።
6እነዚህ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በጽናጽል፣ በመሰንቆ በበገና አገልግሎት በአባቶቻቸው አመራር ሥር ነበሩ። አሳፍ፣ ኤዶታምና ኤማን ደግሞ በንጉሥ የበላይ አመራር ሥር ነበሩ።
7እነዚህም ከቤተዘመዶቻቸው ጋር በመሆን ሁሉም ወደ እግዚአብሔር በሚቀርበው ዜማ የሠለጠኑ የተካኑ ነበሩ፤ ቁጥራቸውም ሁለት መቶ ሰማንያ ስምንት ነበረ።
8የሥራ ድርሻቸውንም ለመወሰን ወጣት፣ ሽማግሌ፣ መምህርም ሆነ ደቀ መዝሙር ሳይባል እኩል ዕጣ ተጣጣሉ።
9የመጀመሪያው ዕጣ ከአሳፍ ወገን ለሆነው ዮሴፍ ወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸው12 ሁለተኛው ለጎዶልያስ ወጣ፤ እነሱን ጨምሮ ለቤተ ዘመዶቹና ለወንዶች ልጆቹ፤ ቁጥራቸውም12
10ሦስተኛው ለዛኩር፣ ወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም12
11አራተኛው ላይጽሪ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
12አምስተኛው ለነታንያ ለወንዶቹ ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ ቁጥራቸውም 12
13ስድስተኛው ለቡቃያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
14ሰባተኛው ለይሽርኤል፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
15ስምንተኛው ለየሻያ፤ ለወንዶች ልጆቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
16ዘጠነኛው ለመታንያ፣ ወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ቁጥራቸውም 12
17ዐሥረኛው ለሰሜኢ፣ ወጣ ወንዶች ልጆችና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ ቁጥራቸውም 12
18ዐሥራ አንደኛው ለዓዛርኤል፣ ወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
19ዐሥራ ሁለተኛው ለሐሻብያ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
20ዐሥራ ሦስተኛው ለሱባኤል፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ ቁጥራቸውም 12
21ዐሥራ አራተኛው ለመቲትያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
22ዐሥራ አምስተኛው ለኢያሪሙት፣ ለወንዶች ልጆቹና ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
23ዐሥራ ስድስተኛው ለሐናንያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
24ዐሥራ ሰባተኛ ለዮሽብቃሻ፣ ለወንዶች ልጆቹና ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
25ዐሥራ ስምንተኛው ለሐናኒ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
26ዐሥራ ዘጠነኛ ለመሎቲ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጧ፤ ቁትራቸውም 12
27ሃያኛው ለኤልያታ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
28ሃያ አንድኛው ለሆቲር፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸው 12
29ሃያ ሁለተኛው ለጊዶልቲ፣ ወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
30ሃያ ሦስተኛው ለመሐዝዮት፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
31ሃያ አራተኛውም ለሮማንቲዔዘር፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12