1የአሮን ልጆች አመዳደብ እንደ ሚከተለው ነበረ፤ የኦ ልጆች ናዳብ፣ አብድዩ፣ አልዓዛር፣ ኢታምር፣ ነበሩ።
2ናዳብና አብድዩ ግን ዘር ሳይተኩ ከአባታቸው በፊት ሞቱ፤ ስለዚህ አልዓዛርና ኢታምር ካህናት ሆነው ያገለግሉ ነበር።
3ዳዊትም የአላዓዛር ዘር የሆነው ሳዶቅና የኢታምር ዘር ሆነው አቢሜሌክ እየረዱ እንደየአገልግሎታቸው ሥርዓት እየለየ መደባቸው።
4ከኢታምር ይልቅ በአልዓዛር ዘሮች መካከል ብዙ መሪዎች ተገኙ፤ አከፋፈላቸውም እንደሚከተለው ነበር፤ ከአልዓዛር ዘሮች ዐሥራ ስድስት የቤተሰብ አለቆች።
5ከአልዓዛርና ከኢታምር ዘሮች መካከል የመቅደሱ ሹማምትና የእግዚአብሔር ሹማምት ስለ ነበሩ፣ ያለ አድልዎ በዕጣ ለዩአቸው።
6የሌዋውያ የናትናኤል ልጅ ጻሓፊው ሸማያ በንጉሥና በሹማምቱ፣ በካህኑ በሳዶቅ፣ በአብያታር ልጅ በአሜሌክ እንዲሁም በካህናቱና በሌዋውያኑ ቤተሰብ አለቆች ፊት ስማቸውን ጻፊ፤ የጻፈውም አንዱን ቤተሰብ ከአልዓዛር ሌላውን ደግሞ ከኢታምር በመወሰድ ነው፤
7የመጀመሪያው ዕጣ ለዮአሩብ፣ ሁለተኛውም ዕጣ ለዮዳሄ ወጣ።
8ሦስተኛው ለካሪም፣ አራተኛው ለሥዖሪም፣
9አምስተኛው ለመልክያ፣ ስድስተኛው፤
10ሰባተኛው ለአቆስ፣ ስምንተኛው ለአብያ፣
11ዘጠናኝው ለኢያሱ፣ ዐሥረኛ ለሴኬንያ፣
12ዐሥራ አንደኛው ልች ኤሊያሴብምም ዐሥራ ሁለተኛው ለያቂም፣
13ዐሥራ ሦስተኛው ለኦፓ፣ዐሣር አራተኛው ለየሼብአብ፣
14ዐሥራ ሰባተኛው ለቢልጋ፣ ዐሥራ ስድስተኛው ለኢሜር፤
15ዐሥራ ሰባተኛው ለኤዚር፣ ዐሥራ ስምንተኛው ለሃፊጼጽ፣
16ዐሥራ ዘጠነኛው ለፈታያ፣ ሃያኛው ለኤዜቄል፣
17ሃያ አንደኛው ለያኪያ፣ ሃያ ሁለተኛው ለጋሙል፣
18ሃያ ሦስተኛው ለድላያ፣ ሃያ አራተኛ ለመዓዝያ ውጣ።
19የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ባዘዘውና ከቀድሞ አባታቸው ከአሮን በተሰጣቸው መመሪያ መጠረት ወደ እግዞአብሔር ቤተ መቅደስ በሚገቡበት ጊዜ፣ የተወሰነላቸው ሥርዐት ይህ ነበር።
20የቀሩት የሌዊ ዘሮች አግሚ፦ከእንበረም ወንዶች ልጆች፤ ሱባኤል፤ ከሱባኤል ወንዶች ልጆች፤ ዬሕድያ።
21ከረዓብያ ወንዶች ልጆች፤ አለቃው ይሺው።
22ከይስዓራውያን ወገን፤ ሰሎሚት ከሰሎሚት ወንዶች ልጆች፤ ያሐት።
23የኬብሮን ወንዶች ልጆች፤ የመጀመሪያው ይሪያ፣ ሁለተኛው አማርያ፣ ሦስተኛው የሕዚኤል፣ አራተኛው ይቀምዓም።
24የዑዝኤል ልጅ፤ ሚካ። የሚካ ወንዶች ልጆች ሻሚር።
25የሚካ ወንድም ይሺያ፤ ከይሺያ ወንዶች ልጆች ዘካርያስ።
26የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤ሞሖሊምም ሙሲ።የያዝያ ወንድ ልጅ በኖ፤
27የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤ ከያዝያ በኖ፣ ሾሃም፣ ዘኩር፣ ዔብሪ።
28ከሞሒሊ፤ አልዓዛር፤ ይህ ሰው ወንዶች ልጆች አልነበሩትም።
29ከቂስ፣ የቂስ ወንድ ልጅ፤ ይረሕምኤል።
30የሙሲ ወንዶች ልጆች፤ ሞሖሊ፣ ዔዳር፣ ኢያሪሙት። እነዚህ እንግዲህ እንደቤተሰባቸው የተቁጠሩ ሌዋውያን ነበሩ።
31ወንድሞቻቸው የአሮን እንዳደረጉት ሁሉ፣ እነዚህም በንጉሥ ዳዊት፣ በሳዶቅ፣ በአቢሜሌክ እንዲሁም የካህናቱ የሌዋውያኑ ቤተሰብ አለቆች ባሉበት ዕጣ ተጣጣሉ፤ የበኩሩም ቤተሰቦች እንደ ትንሹ ወንድም ቤተሰብ እኩል ዕጣ ተጣለላቸው።