መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

1ኛ ዜና 23

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ዳዊት በሽመገለና ዕድሜው በገፋ ጊዜ፤ልጁን ሰሎሞንን በእራኤል ላይ አነገጀው።
2እንዲሁም መላውን የእስራኤል መሪዎች፣ካህናቱ ሌዋውያኑን ሁሉ በአንድነት ሰበሰበ።
3ዕድሜውቸው ሥላሳና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ተቁጠሩ፤ቁጥራቸውም በጠቅላላው ሠላሳ ስምንት ሺህ ነበረ
4ዳዊትም እንዲህ አለ፤ "ከእነዚህ መካከል ሃያ አራቱ ሺህ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሥራ ይቁጣጠሩ፤ ስድስቱ ሺህ ደግሞ ሹሞችና ዳኞች ይሁኑ፤
5አራቱ ሺህ የቅጥሩ በር ጠባቂዎች ይሁኑ፤ አራት ሺህ ደግሞ ለዚሁ ብዬ ባዘጋጀሁት የዜማ መሣሪያ እግዚአብሔር ያመስግኑ"።
6ዳዊትም ሌዋውያኑን በሌዊ ልጆች በጌድሶን፣ በቀነዓና በሜራሪ በየጎሣቸው መደባቸው።
7ከጌድሳናውያን ወገን፤ ለአዳን፣ሰሜኢ።
8የለእአዳን ወንዶች ልጆች፤ የመጀመሪያው ይሒኤል፣ ዜቶም፣ ኢዮኤል፣ባጠቃላይ ሦስት ናቸው።
9የስማኢ ወንዶች ልጆች፤ ሰሎሚት፣ ሀዝዝኤል፣ ሐራን፣ ባጠቃላይ ሦስት ናቸው። እነዚህ የለአዳን ቤተሰብ አለቆች ናቸው።
10የስማኢ ወንዶች ልጆች፤ ኢኢት፣ ዚዛ፣ የዑስ፣ በሪዓ፣ እነዚህ አራቱ የስሚኤ ልጆች ናቸው።
11የመጀመሪያው ኢኢት፣ ሁለተኛው ደግሞ ዚዛ፣ ነበረ የዑስና በሪዓ ግን ብዙ ወንዶች ልጆች አልነበሯቸውም፤ ስለዚህ የተቁጥዐሩት በሥራ መደብ እንደ ቤተሰብ ሆነው ነው።
12የቀነዓት ወንዶች ልጆች፤ እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮን፣ ዑዝኤል፣ ባጠቃላይ አራት ናቸው።
13የእንበረት ወንዶች ልጆች፤ አሮን፣ ሙሴ። አሮን የተቀደሰ እንዲሆን ተለየ፤ እርሱና ዘሮቹ ለዘላለም ቅዱስ የሆኑትን ነገሮች እንዲቀደሱ፣ እግዚአብሔር ፊት መሥዕዋት እንዲያቀርቡ፤ በፊቱ እንዲያገለግሉና በስሙም ለዘላለም እንዲባረኩ ተለዩ።
14እግዚአብሔር ሰው የሙሴ ወንዶች ልጆችም እንደ ሌዊ ነገድ ሆነው ተቁጠሩ።
15የሙሴ ወንዶች ልጆች፤ ጌርሳም፣ አልዓዛር።
16የጌሳም ዘሮች፤ ሱባኤል።
17የአልዓዛር ዘሮች፤ የመጀመሪያው ረዓብያ ነበረ።አልዓዛር ሌሎች ወንዶች ልጆች ግን እጅግ ብዙ ነበሩ።
18የይስዓር ዶዶችች ልጆች፤ የመጀመሪያው ሰሎሚት።
19የኬብሮን ወንዶች ልጆች፤ የመጀመሪያው ዬሪያ፣ ሁለተኛው አማርያ፣ ሦስተኛው የሕዚኤል፣ አራተኛ ይቅምዓም ነበሩ።
20የዑዝኤል ወንዶች ልጆች፤ የመጀመሪያው ሚካ፣ ሁለተኛው ይሺያ ነበሩ።
21የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤ ሚሖሊ፣ ሙሲ፣ የሞሐሊ ወንዶች ልጆች አልዓዛር ቂስ ነበሩ።
22አልዓዛር ወንድ ልጅ ሳይወልድ ሞተ፤ ልጆቹ ሴቶች ብቻ ነበሩ፤ እርሱንም የአጎታቸው የቂስ ልጆች አገቡአቸው።
23የሙሲ ወንዶች ልጆች፤ ሞሖሊ፣ ዔደር፣ ኢያሪሙት ባጠቃላይ ሦስት ናቸው።
24እንግዲህ እነዚህ የቤተሰብ አለቆች ሆነው እያንዳንዳቸው በየስማቸው ተመዝግበው የተቁጠሩት የሌዊ ዘሮች ናቸው፤ ዕድሜአቸው ሃያና ከዚያ በላይ የሆናቸው በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስት የሚያገለግሉ ነበሩ።
25ዳዊት እንዲህ ብሎ ነበርና፣ "የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ዕረፍት ሰጥቷል፤ በእየሩሳሌምም ለዘላለም ለመኖር መጥቷል፤
26ሌዋውያን ከእንግዲህ ወዲህ ድንኳኑን ወይም የመገልገያ ዕቃውን ሁሉ መሸከም የለባቸውም።"
27ዳዊት በሰጠው የመጨረሻ መመሪያ መሠረት የተቁጠሩት ሌዋውያን ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያ በላይ ነበረ።
28የሌዋውያኑ ተግባር በእግዚአብሔር ቤተ መቅደሱን ቅጥር ግቢና ክፍሎች መንከባከብ፣ የተቀደሱ ዕቃዎች ሁሉ ማጻትና በእግዚአብሔር ቤት ያሉትን ሌሎች ተግባሮች ማከናውን ነበር።
29እንዲሁም መባ ሆኖ የሚቀረውን ኅብስት ገፅ፣ የእህል ቁርባኑን ዱቄት፣ ያለ እርሾ የሚጋገረውን ቂጣ የሚጋግሩ፣ የሚያቦኩና የሚሰፍረውንም ሆነ የሚለካውን ሁሉ በኅላፊነት የሚቁጣጠሩ እኔሩ ነበር።
30በየለዕቱ እግዚአብሔርን ለማመስገንና ለመወደስ ጠዋት ጠዋት ይቆኑ ነበር፤ይህንንም ማታ ማታ፣
31እንዲሁም በየሰንበቱ፣ በወር መባቻ በዓልና በተደነገጉት በዓላት ሁሉ፣ የሚቃጠል መሥዕዋት ለእግዚአብሔር በሚቀርብበት ጊዜ ሁሉ ይፈፅሙ ነበር። በተወሰነላቸው ቁጥርና በተሰጠው መመሪያ መሠረት ዘውትር በእግዚአብሔር ፊት ያገለግሉ ነበር።
32ስለዚህ ሌዋውያኑ ለመገናኘት ድንኳንና ለመቅደሱ እንዲሁም በወንድሞቻቸው በአሮን ዘሮች ሥር ሆነው ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ያለባቸውን ኅላፊነት ያከናውኑ ነበር።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።