1ከዚያም ዳዊት፣"ከእንግዲህ የእግዚአብሔር አምላክ ቤት በዚህ ይሆናል፤እንዲሁም ስለ እስራኤል የሚቃጠል መሥዕዋት የሚቀርብበት መሠዊያ በዚሁ ይቆማል"አለ።
2ስለዚህ ዳዊት በእስራኤል የሞኖሩ መጻተኞች እንዲሰበሰቡ አዘዘ፤ከመካከላቸም እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሚሠራበትን ጥጋብ ድንጋይ እንዲያዘጋጁ ጠራቢዎች መደበ።
3ለቅጥር በሮች ምስማርና ማጠፊያ የሚሆን ብዙ ብረትና ከብዛቱ የተነሣ ሊመዘን የማይችል ናስ አዘጋጀ።
4እንዲሁም ሲዶናውያንና ጢሮሳውያን በብዛት አውጥተውለት ስለ ነበር፣ስፍር ቁጥር የሌለው የዝግባ ዕንጨት አሰናዳ።
5ዳዊትም፣"ልጅ ሰሎሞን ወጣት ነው፤ልምዱም የለውም፤ለእግዚአብሔር የሚሠራው ቤተ መቅደስ ደግሞ እጅግ የሚያምር፣በአሕዛብም ሁሉ ዘንድ አለበት፤ስለዚህ ሁሉንም እኔ አዘጋጃለሁ"እንዳለው ዳዊት ከመሞቱ በፊት በብዛት አዘጋጀ።
6ከዚያም ልጁን ሰሎሞንን ጠርቶ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚያብሔር ቤት እንዲሥራ አዘዘው።
7ዳዊትም ሰሎሞን እንዲህ አለ፤"ልጄ ሆይ ለአምላክህ እግዚአብሔር ስም ቤት ለመሥራት በልቤ አሰብ ነበር፤
8ነገር ግን ከእግዚአብሔር እንዲህ የሚል ቃል መጣልኝ፤"አንተ ብዙ ደም አፍስሰሃል፤በፊቴ በምድር ላይ ብዙ ደም ያፈሰስህ ስለሆነ አንተ ለስሜ ቤት አትሠራልኝም፤
9ነገር ግን የሰላምና የዕረፍት ሰው የሆነ ልጅ ትወልዳለህ፤ በየአቅጣጫው ካሉ ጠላቶቹ ዐሳርፈዋለሁ፤ ስሙም ሰሎሞን ይባላል። በዘመኑም ለእስራኤል ሰላምና ጸጥታን እሰጣለሁ።
10ለስሜ ቤት የሚሰራልኝ እርሱ ነው። እርሱ ልጅ ይሆነኛል 'እኔም አባት እሆነዋለሁ። ዙፋንም በእስራኤል ላይ ለዘላለም አጸናለሁ።
11አሁንም ልጅ ሆይ፤ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን፤ እንድትፈጽሙ በተናገረውም መሠረት፣ ተሳክቶልህ የአምላክን የእግዚአብሔር ቤት ለመሥራት ያብቃህ።
12በእስራኤል ላይ አለቃ ባደረገህ ጊዜ የአምላክህ እግዚአብሔርን ትእዛዝ ትፈጽም ዘንድ እግዚአብሔር ጥበብንና ማስተዋል ይስጥህ።
13ችግዚአብሔር በሙሴ አማካኝነት ለእስራኤል የሰጠውን ሕጉንና ሥርዐቱን ተጠንቅቀን ብትጠብቅ ይሳካልሃል፤ አይዞህ ጠንክር፤ በርትስ፤ ተስፋም አትቁረጥ።
14"ለእግዚአብሔር ቤት እንዲሆንም አንድ ሺህ መክሊት ወርቅ፣ አንድ ሚሊዮን መክሊት፣ ብር፣ ከብዛቱ የተነሣ ሊመዘን የማይቻል ናስና ብረት ለማዘጋጅ በተቻለኝ ሁሉ ጥሬአለሁ። ደግሞም እንጨትና ድንጋዮች አዘጋጀሁ፤ በተረፈ አንተ ጨምርበት።
15ድንጋይ ጠራቢዎች፣ግን በኞች አናጢዎች የሆኑ ልዩ ሙያ የተጠበቡ ሰዎች አሉህ፤
16አነዚህ ቁጥራቸው እጅግ የበዛ የውርቅ፣የብር፣የናስና የብረት ሠራተኞች ናቸው።በል ሥራህን ጀምር፤እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን።"
17ከዚያም ዳዊት የእስራኤል መሪዎች ሁሉ ልጁን ሰሎሞንን እንዲረዱት አዘዘ፤
18እንዲህም አለ፤"እግዚአብሔር አምላካችን እስካሁን ከእናንተ ጋር አይደለምን? በየአቅጣጫውስ ዕረፍትን ስጥቷችሁ የለምን? የምድሪቱንም ነዋሪዎች በእጄ አሳልፎ ሰጥቶኛል፤ምድሪቱም ለእግዚአብሔር ለሕዝቡ ተገዝታለች።
19አሁንም እግዚአብሔር የኪዳኑን ታቦትና ንዋያት ቅዱሳቱን ለእግዚአብሔር ስም ወደሚሠራው ቤተ መቅደስ አምጥታችሁ የአምላክ የእግዚአብሔር መቅድደስ ሥሩ።