መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

1ኛ ዜና 21

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ሰይጣን በእስራኤል ላይ ተነሥቶ ዳዊት የእስራኤልን ሕዝብ እንዲቁጥር አነሣሣው።
2ዳዊትም ኢዮአብንና የሰራዊቱን አዛዦች፤"ሄዳችሁ ከቤርሳቤህ እስከ ዳን ያሉትን እስራኤላዊያን ቁጠሩ፤ከዚያም ምን ያህል እንደ ሆኑ ዐውቅ ዘንድ ንገሩኝ አላቸው።
3ኢዮአብ ግን፣እግዚአብሔር የእስራኤል ሰራዊት አሁን ካለው በላይ በመቶ ዕጥፍ ያብዛው፤ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ሁልስ ቢሆኑ የጌታዬ ተገዢዎች አይደሉምን? ታዲያ ጌታዬ ይህን ማድረግ ለምን አስፈለገው? ለምንስ በእስራኤል ላይ በደል ያመጣል?"አለ።
4ይሁን እንጂ የንጉሥ ቃል ኢዮአብን አሸነፈው፤ስለዚህ ኢዮአብ ወጣ፤በመላው እስራኤል ከተዘዋወረ በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።
5ኢዮአብም የተዋጊዎቹን ሰዎች ቁጥር ለዳዊት አቀረበ፤እነዚህም በመላው እስራኤል አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ፣በይሁዳ ደግሞ አራት መቶ ሰባ ሺህ ሲሆኑ፣ሁሉም ሰይፍ መምዘዝ የሚችሉ ነበሩ።
6ነገር ግን የንጉሡ ትእዛዝ በእርሱ ዘንድ አስጸያፊ ነበረና፣ኢዮአብ የሌዊንና የብንያም ነገድ ጨምሮ አልቁጠረም።
7ይህ ትእዛዝ በእግዚአብሄር ዘንድ የተጠላ ነበር፤ስለዚህ እግዙአብሔርን ቀጣ።
8ከዚያም ዳዊት እግዚአብሔርን፣"ይህን በማድረጌ እጅግ በድያለሁ፤የፈጸምኩትም የስንፍና ሥራ ስለሆነ፣የባሪያህን በደል እንድታስወግድ እለምንሃለሁ"አለ።
9እግዚአብሔር የዳዊት ባለ ራእይ የሆነውን ጋድን እንዲህ አለው፤
10ሂድና ለዳዊት እንዲህ ብለህ ንገረው፤እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤እነሆ፣ሦስት ምርጫ ሰጥሃለሁ፤በአንተ ላይ እንዳደርስብህ እንዱን ምረጥ።"
11ስለዚህ ጋድ ዳዊት ሄዶ እንዲህ አለው፤"እግዚአብሔር የሚለው ይህን ነው፤አንዱን ምረጥ፤
12የሦስት ዓመት ራብ ወይስ የጠላቶችህን ሰይፍ ለሦስት ወር አይሎብህ ተሰዶ መጥፋት ወይስ ሦስት ቀን የእግዚአብሔር ስይፍ መቅሠፍት በምድሪቱ ላይ ወርዶ የእግዚአብሔር መልአክ እስራኤልን ሁሉ ያጥፋ? እንዲህ ላልከኝ ምን እንደምመልስ ቁርጡን ነገረኝ።
13ዳዊትም ጋድን፣"ችጅግ ተጨንቅይአለሁ፤ምሕረቱ ታላቅ ስለሆነ በእግዚአብሔር እጅ መውደቅ ይሻለኛል፤በሰው እጅስ አልወድቅ"አለ።
14እለዚህ እግዚአብሔር በእስራኤል ሰባ ሺህ ሰው ዐለቀ።
15እንዲሁም እግዚአብሔር እየሩሳሌምን እንዲያጠፋ መልአክ ላከ፤መልአኩም ሊያጠፋት ሲል እግዚአብሔር አይቶ ስለሚያደርሰው ጥፋት ዐዘን፤ህዝቡን የሚያጠፋውንም መልአክ፣"እጅህን መልስ"አለው።የእግዚአብሔር መልአክ በኢያቡሳዊያ በኦርና ዐውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር።
16ዳዊት ቀና ብሎ ሲመለከት፣የእግዚአብሔር መልአክ በሰማይና በምድር መካከል ቆሞ አየ፤መልአኩም በኢየሩሳሌም ላይ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ ይዞ ነበር፤ከዚያም ዳዊትና ሽማግሌዎች ማቅ እንደሚለብሱ በግንባራቸው ተደፉ።
17ዳዊት እግዚአብሔር "ተዋጊዎቹ እንዲቁጠሩ ያዘዝሁ እኔ እይደለሁም? ኅጢአት የሠራሁበትም ሆነ የበደልሁት እኔ ነኝ፤እነዚህ እኮ በጎች ናቸው፤ታዲያ እነርሱ ምን አደረጉ? እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ትሁን እንጂ፣መቅሠፍት በሕዝብህ ላይ አይውረድ"አለ።
18ከዚያም እግዚአብሔር መልአክ ዳዊት ወጥቶ በአቡሳዊያን በኦርና ዐውድማ ላይ ልችእግዚአብሔር መሠዊያ ይሠራ ዘንድ እንዲነግረው ጋድን አዘዘው።
19ዳዊትም ጋድ በእግዚአብሔር ስም በነገረው ቃል መሠረት ለመፈፀም ውጣ።
20ኦርና ስንዴ በመውቃት ላይ ሳለዘወር ሲል መለአኩን አየ፤አብረውት የነበሩት አራት ወንዶች ልጆችም ተሸሸጉ።
21ዳዊት ወደ እርሱ እየቀረበ መጣ፤ኦርናቀና ብሎ ሲመለከት፣ዳዊትን አየው፤ከዐውድማውም ወጥቶ መሬት ላይ በግንባሩ ተደፍቶ ዳዊትን እጅ ነሣ።
22ዳዊትም፣"በሕዝቡ ላይ የወረደው መቅሠፍት እንዲወገድ ለእግዚአብሔር መሠዊያ እሠራ ዘንድ ዐውድማህን ልውሰደው፤ሙሉውን ዋጋ እከፍልሃለሁ"አለው።
23ኦርናም ዳዊትም፣"እንዲሁ ወስደው፤ጌታዬ ንጉጅ ደስ ያለውን ያድርግ፤እነሆ ለሚቃጠል መሥዋዕት በሬዎቹን፣መውቂያ በትሮቹን ለማቀጣጠያ ዕንጨት፣ስንዴው ደግሞ ለእህል ቁርባን እንዲሆን እሰጣለሁ፤ሁሉንም እኔ እሰጣለሁ።አለ።
24ንጉሥ ዳዊት ግን ለኦርና "አይደረግም፤ሙሉውን ዋጋ እኔ እከፍላለሁ፤የአንተ የሆነውን ለእግዚአብሔር ለማውረብ አልፈልግም፤ዋጋ ያልከፈልኩበትም የሚቃጠል መሥዋዕት እድርጌ አላቀርብም" ሲል መለሰለት።
25ስለዚህ ዳዊት ለኦርና የቦታውን ዋጋ ስድስት መቶ ስቅል ወርቅ ከፈለ።
26ዳዊትም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠርቶ የሚቃጠል መሥዕዋትና የኅብረት መሥዋዕት አቀረበ።እግዚአብሔርም ጠራ፤እግዚአብሔርም የሚቃጠል መሥዕዋት በሚቀርብበት መሠዊያ ላይ ከሰማይ በእሳት መለሰለት።
27ከዚያም እግዚአብሔር ለመልአኩ ተናገረ፤መልአኩም ሰይፉን ወደ አፎቱ መለሰ።
28በዚያን ጊዜ ዳዊት፤እግዚያብሔር በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ ላይ እንደ መለሰለት ሲያይ፤በዚያው ቦታ መሥዕዋት ማቅረብ ጀመረ።
29ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው የእግዚአብሔር ማደሪያ ድንኳንና የሚቃጠል መሥዕዋት የሚቀርብበት መሠዊያ በዚያ ጊዜ በገባዖን ኮረብታ ላይ ነበረ።
30ዳዊት የእግዚአብሔር መልአክ ሰይፍ ሰለፈራ ወዲያ ሄዶ እግዚአብሔር ለመጠየቅ አልቻለም።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።