1ነገሥታት ለጦርነት በሚሄዱበት በፈደይ ወራት፣ኢዮአብ የጦር ሰራዊቱን እየመራ ሄዶ የአሞናውያንን አገር አጠፋ፤ወደ ራባትም ሄዶ የአሞናውያንን አገር አጠፋ፤ወደ ራባትም ሄዶ ከበባት፤ዳዊት ግን ኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር።ኢዮአብም ራባትን ወግቶ አፈራረሳት፤
2ዳዊት የንጉሣቸውን ዘውድ ከራሱ ላይ ወሰደ፤ክብደቱም አንድ መክሊት ወርቅ ነበረ፤ይህንንም በዳዊት ራስ ላይ ጫኑለት፤እንዲሁም ከከተማይቱ እጅግ ብዙ ምርኮ ወሰደ።
3በዚያ የነበረውን ሕዝብ አውጥቶ መጋዝ፣ዶማና መጥረቢያ ይዘው እንዲሠሩ አደረጋቸው።ዳዊት በሌሎቹም የአሞን ከተሞች ሁሉ ይህንኑ አደረጉ።ከዚያም ዳዊትና መላው ሰራዊቱ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።
4ከዚያም በኋላ ከፍልስጥኤማዊያን ጋር በጌዝር ጦርነት ተደረገ፤በዚያ ጊዜ ኩሳታዊው ሴቦካይ የራፋይም ዘር የሆነውን ሲፋይን ገደለ፤ፍልስጥኤማውያንም ድል ተመቱ።
5ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሌላ ጦርነት ተደረገ፤የያዒር ልጅ ኤልያናን የጦሩ የቦውፍረቱ እንደ ሽማኔ መጠቅለያ የሚያህለውን የጌት ተወላጅ የሆነውን የጎልያድን ወንድም ላሕሚን ገደለ።
6ደግሞም ጌት ላይ በተደረገ ሌላ ጦርነት፣በእጆቹና በእግሮቹ ላይ ስድስት ስድስት ጣት በድምሩ ሃያ አራት ጣት የነበሩት አንድ ግዙፍ ሰው ነበረ፤ይህም እንደዚሁከራፋይም ዘር ነበረ።
7እርሱም እስራኤልን በተገዳደረ ጊዜ የዳዊት ወንድም የሳምዓ ልጅ ዮናታን ገደለው።
8በጌት የነበሩ የራፋይም ዘሮች እነዚህ ናቸው፤እነሱም በዳዊትና ሰዎቹ እጅ ወደቁ።