መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

1ኛ ዜና 19

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከዚህ በኋላ የአሞናውያን ንጉሥ ናዖስ ሞተ. ልጁም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።
2ዳዊትም "አባቱ ለእኔ በጎ ነገር እንዳደረገልኝ እስቲ እኔም ለናዖስ ልጅ ለሐኖን በጎ ነገር ላድርግለት"ብሎ አስብ።ስለዚህ ዳዊት ስለ አባቱ ሞት ሐዘኑን ለመግለጽ ወደ ሐኖን መልክተኞችን ላከ።የዳዊት ሰዎች ሐናቸውን ለመግለጽ ሐኖን ወደሞኖርበት ወደ አሞናውያን ምድር በመጡ ጊዜ፣
3የአሞናውያን መኳንንት ለሐኖን "ዳዊት ሀዘኑን ለመግለጽ ሰዎችን ወደ አንተ የላከው አባትህን አክብሮ ይመስልሃን? ሰዎች ወደ አንተ የመቱት አገሩቱን ለመመርመር፣ለመሰለልና ለመያዝ አይደለምን? አሉት።
4ስለዚህ ሐኖን የዳዊትን ሰዎች ይዞ ላጫቸውል ልብሳቸውንም እስከ መቀመጫቸው ድረስ መኻል ለመኻል ቀዶ ሰደዳቸው።
5በሰዎቹ ላይ የደረሰባቸውን ዳዊት በሰማ ጊዜ እጅግ ዐፍረው ስለ ነበር፣ወደ እነርሱ መልክተኞችን ላከ፤ንጉሥም፣"ጢማችሁ እስኪያድግ ድረስ በኢያኮር ቁዩና ከዚያ በኋላ ትመጣላችሁ"አለ።
6አሞናውያን በዳዊት ዘንድ እንደ ተጠሉባወቁ ጊዜ፣ሐኖንና አሞናውያን ከመሰጴጦምያ፣ከአራምመዓካና ከሱባ ሠረገሎችንና ፈረሶችን ለመከራየት አንድ ሺህ መክሊት ብር ላኩ፤
7ከዚያም ሠላሳ ሁለት ሺህ ሠረገሎችንና ፈረሶኞችን እንዲሁም የመካዓን ንጉሥና ወታደሮች በገንዘብ ቀጠሩ፤እነርሱም መጥተው በሜድባ አጠገብ ሲሰፍሩ፣አሞናውያን ደግሞ ከየከተሞቻቸው ተሰብስበው ለጦርነት ወጡ።
8ዳዊት ይህን ሲሰማ ኢዮአብንና መላውን ተዋጊ ሰራዊት ላከ።
9አሞናውያንም መጥተው ወደ ከተማቸው በሚያስገባው በር ላይ ለጦርነት ተሰለፉ፤የመጡት ነገሥታት ደግሞ ብቻቸውን በሜዳው ላይ ነበሩ።
10ኢዮአብም ከፊቱና ከኋላው ጦር መኖሩንና አየ፤ስለዚህ በእስራኤል የታወቁትን ጀግኖች መርጦ ሶርያውያንን እንዲገጥሙ አሰለፋቸው።
11የቀሩትም ሰዎች በወንድሙ በአቢሳ ሥጋ ሆነው አሞናውያንን እንዲገጥሙ አስለፋቸው።
12ኢዮአብም እንዲህ አለ፤"ሶርያውያን ከበረቱብኝ አንተ ትረዳኛለህ"አሞናውያን ከበረቱብህ ደግሞ እኔ እረዳሃለሁ።
13እንግዲህ በርቱ፤ስለ ሕዝባችንና ስለ አምላካችን ከተሞች ብለን በጀግንነት እንዋጋ፤እግዚአብሔር ደስ ያሰኘውን ያድርግ።"
14ከዚያም ኢዮአብና አብረውት ያሉት ወታደሮች ሶርያውያን ለመዋጋት ወደ ፊት ገሠገሠ፤ሶርያውያንም ከፊታቸው ሸሹ።
15አሞናውያንም ሶርያውያን መሸሻቸውን ሲያዩ፣እርሱም ከውንድሙ ከአቢሳ ፊት ሸሽተው ወደ ከተማይቱ ገቡ፤ስለዚህ ኢዮአብ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።
16ሶርያውያን በእስራኤል መሸነፋቸውን ሲያዩ፣መልክተኞችን ልከው ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ያሉትን ሶርያዊያን አስመጡ፤እነዚህንም የሚመራቸው የአድርአዛር ስራዊት አዛዥ ሾፋክ ነበረ።
17ዳዊት ይህን ሲሰማ፣እስራኤልን ሁሉ ሰብስቦ ዮርዳኖስን ተሻገረ፤ወደፊት በመገሥገሥም ከፊት ለፊታቸው የውጊያ መሥመሩን ያዘ።ዳዊትም ሶርያውያንን ጦርነት ለመግጠም ወታደሮቹን አሰለፈ፤እነርሱም ተዋጉት።
18ይሁን እንጂ ከእስራኤል ፊት ሸሹ።ዳዊትም ሰባት ሺህ ሠረገለኞችና አርባ ሺህ እግረኛ ወታደሮች ገደለ።የሠራዊታቸው አዛዥ ሾፋክም በጦርነት ላይ ሞተ።
19የአድርአዛርም ሹማምት በእስራኤል መሸነፋቸውን ሲያዩ፣ከዳዊት ጋር ታረቁ፤ገባሮቹም ሆኑ።ስለዚህ ሶርያውያን ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አሞናውያንን ለመርዳት ፍቃደኞች አልሆኑም።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።