1ከዚህ በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማዊያንን ድል መትቶ ተገዢ አደረጋቸው፤ጌትንና በዙሪያዋም የሚገኙትን መንደሮች ከፍልስጥኤማዊያን እጅ ወስደ።
2እንዲሁም ዳዊት ሞዓባዊያንድል አደረጋቸው፤እነሱም ገባሮቹ ሆኑ፤ግብርም አመጡለት።
3ከዚያም በላይ ዳዊት በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ የነበረው ግዛት ለመቁጣጠር በሄደ ጊዜ፣የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን እስከ ሐማት ድረስ ዘልቆ ወጋው።
4ዳዊትም አንድ ሺህ ሠረገላ. ሰባት ሺህ ፈረሰኛና ሃያ ሺህ እግረኛ ወታደር ማረከ፤አንድ መቶ የሠረገላ ፈረሳች ብቻ አስቀርቶ የቀሩትን ቋንጃቸውን ቁረጠ።
5ሶርያውያንም የሱባን ንጉሥ እድርአዛርን ለመርዳት ከደማስቆ በመጡ ጊዜ፣ከእነሱ ሃያ ሁለት ሺህ ሰው ገደለ።
6ከዚያም በሶርያ ግዛት ውስጥ ባለችው ወደማስቆ የጦር ሰፈር ፤አቋቋመ፤ሶርያውያን ገባሮቹ ሆኑ፤ግብርም አመጡለት።እግዚአብሔርም ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ድል አጎናፀፈው።
7ዳዊትም የአድርአዘር ጦር አለቆች ያነገቡትን የወርቅ ጋሻ ወሰደ፤ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው።
8ዳዊት ከአድርአዛር ከተሞች ከጢብሐትና ከኩን እጅግ ብዙ ናስ ወስደ፤ሰለሞን የናሱን ባሕር፤ዐምዶቹንና ልዩ ልዩ የናስ ዕቃዎቹን የሠራው በዚሁ ነበር።
9የሐማት ንጉሥ ቶዑ ዳዊት የሱባን ንጉሥ የአድርአዛርን ሰራዊት ሁሉ ድል እንደመታ ሲሰማ፣
10እጅ እንዲነሳውና ደስታውንም እንዲገልጥለት ልጁን አዳራምን ወደ ንጉሥ ዳዊት ላከው፤ቶዑ ከአድርአዛር ጋር ብዙ ጊዜ ጦርነት ገጥሞ ነበር።አዶራምም ከወርቅ፣ከብርና ከነስ የተጀሩ ልዩ ልዩ ዕቃዎች አመጣለት።
11ንጉሥ ዳዊት ከሞዓብ፣ከአሞናዊያን፣ከፍልስጥኤማውያንና ከአማሌቃውያን ከእነዚህ ሁሉ መንግሥትታት የማረከውን ወርቅና ብር ከዚህ ቀደም እንዳደረገው ሁሉ፤እነዚህንም ዕቃዎች ለእግዚአብሔር ቀደሰ።
12የጹሩያ ልጅ አቢሳ በጨው ሸለቆ ዐሥራ ስምንት ሺህ ኤዶማውያን ገደለ።
13እርሱም በኤዶም የጦር ሰፈሮች አቋቋም፤ኤዶማውያንም ሁሉ ለንጉሥ ዳዊት ገባሮች ሆኑ።እግዚአብሔር ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ድል አጎናጸፈው።
14ዳዊት በመላው እስራኤል ላይ ነገሠ፤ለሕዝቡም ሁሉ ፍትሕና ጽድቅን አሰፈናላቸው።
15የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ የሰራዊት አዛዥ ነበረ፤የአሒሉድ ልጅ ኢዮሣፍጥ ደግሞ የቤተ መዛግብቱ ኃላፊ ነበረ።
16የአኪጦብ ልጅ ሳዶቅና የአቤምሜሌክ ልጅ አብያታር ካህናት ነበሩ፤ሱሳ ደግሞ ጸሓፊ ነበረ።
17የዮሄድ ልጅ በናያስ የከሊታውያንና የፊልታውያን አዛዥ ነበረ።የዳዊት ወንዶች ልጆች ከንጉሥ ቀጥሎ የበላይ ሹማምት ነበሩ።