1ዳዊት በቤተ መንግሥቱ ተደላድሎ በተቀመጠበት ጊዜ፤ነቢዩ ናታንን"እነሆ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤት ውስጥ እኖራለሁ፤የእግዚአብሔር የኮዳኑ ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ይኖራል"አለው።
2ናታንም ለዳዊት፣"እግግዚአብሔር ከአንተ ጋር ስለሆነ፣ያሰብከውን ሁሉ እድርግ"ሲል መለሰለት።
3በዚያም ሌሊት የእግዚአብሔር ቃል ወደ ናታን መጥቶ እንዲህ አለው፤
4"ሂድና ለባርያዬ ለዳዊት እንዲህ ብለህ ንገረው፤እግዚአብሔር የሚለውን ይህን ነው፤እኔ የምኖርበትን ቤት የምትሠራልኝ አንንተ አይደለህም።
5እስራኤልን ከግብፅ ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ፤ከአንዱ ድንኳን ወደ ሌላው ማደሪያ እሄድ ነበር እንጂ፣በቤት ውስጥ አልኖርሁም።
6ከእስራኤላዊያን ጋር በሄድኩባቸው ቦታዎች ሁሉ፣ሕዝቤን እንዲጠብቁ ላዘዝኋቸው መሮዎቻቸው ከቶ፣"ለምን ከዝግባ ዕንጨት ቤት አልሰራችሁልኝምያልሁበት ጊዜ አለን?፤
7"ከእንግዲህ አሁንም ለባሪያዬ ለዳዊት እንዲህ ብለህ ንገረው፤የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሚለው ይህን ነው፤የሕዝቤ ይእስራኤል ገዥ እንድትሆን በጎችን ከመጠበቅና ከመከትተል አንሥቶ ወሰድሁህ።
8በሄድህበት ሁሉ ከአንተ አልተለየሁህም፤ጠላቶችህም ስምህን እንደ ምድር ታላላቅ ሰዎች ስም ገናና አደርገዋለሁ።
9ለሕዝቤ ለእስራኤል መኖሪያ ስፍራ እሰጥተዋለሁ፤የራሳቸውም መኖሪያ ስፍራ እንዲኖራቸው ከእንግዲህም በኋላ እንዳይናወጡ አደርጋቸዋለሁ።ክፉ ሰዎች በመጀመሪያ እንዳደረጉት ሁሉ፤ከእንግዲህ አይጨቁናቸውም፤
10ከዚህ ቀደም በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪዎች በሾምሁ ጊዜ ጨቋኞቹ ያደረጉትን ዛሬ አያደርጉትም፤ጠላቶቻችሁም ሁሉ አዋርዳቸዋለሁ።"እግዚአብሄር ቤት እንደሚሠራልህ በግልፅ እነግርሃለሁ፤
11ዘመንህን ጨርሰህ ወደ አባቶችህ በምትሄድበት ጊዜ፤ከአብራክህ ከተከፈሉት ልጆችህ አንዱ በእግርህ እንዲተካ አደረጋለሁ፤መንግሥቱንም አፅናለሁ፤
12ቤት የሚሠራልኝ እርሱ ነው፤እኔም ዙፋኑን ለዘላለም አፀናለሁ።
13አባት እሆነዋለሁ፤እርሱም ልጅ ይሆነኛል፤ፅኑ ፍቅሬን ከአንተ በፊት ከነበረው ላይ እንደወሰድሁ፣ከእርሱ ላይ ከቶ አልወስድም።
14በቤቴና በመንግሥቴ ላይ ለዘላለም እኖረዋለሁ፤ዙፋኑም ለዘላለም ይፀናል።"
15ናታንም የዚህን ሁሉ ራእይ ቃል ለዳዊት ነገረው።
16ከዚያም ንጉሥ ዳዊት ገባ፤በእግዚአብሔር ፊት ተቀምጦ እንዲህ አለ፤ "እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤ለመሆኑ እስከዚህ ያደረሰኸኝ እኔ ማን ነኝ? ቤተ ሰብይስ ምንድን ነው?
17አምላክ ሆይ፤ይህ በፊትህ በቂ እንዳልሆነ ቁጥረህ ስለ ወደፊቱ የባሪያህ ቤት ተናገረ።እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤እኔንም ከሰዎች ሁሉ እጅግ የከበርረ ሰው አድርገህ ተመለከትኸኝ።
18ባሪያህን ስላከበትኸው፣ዳዊት ከዚህ በላይ ምን ማለት ይችላል? ባሪያህ እኮ ታውቀቃለህ፤
19እግዚአብሔር ሆይ፤ስለ ባሪያህ ብለህና እንደ ፈቃድህም መሠረት ይህን ታላቅ ነገር አድርግሃል፤እነዚህም ታላላቅ ተስፋዎች ሁሉ እንዲታወቁ አደረግህ።
20አቤቱ፤እንደ አንተ ያለ የለም፤በጆሮአቸን አንደ ሰማነው ሁሉ ከአንተ በቀር አምላክ የለም
21ከግብፅ ተቤዠተህ እንዳወጣኸው እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ ማን አለ? እነርሱ እግዚአብሔር ለራሱ ሊቤዣቸው ናቸው፤በሕዝብህም ፊት ታላቅና አስፈሪ ነገሮችን በማድረግ መንግሥታትን በፊታቸው አሳደድህ።
22ሕዝብህንም እስራኤልን ለዘላለም የራስህ ሕዝብ አደረግኸው፤እግዚአብሔር ሆይ፤አንተም አምላክ ሆንህለት።
23እግዚአብሔር ሆይ፤አሁንም ስለባሪያህ ስለ ቤቱ የሰጠኸው ተስፋ ለዘላለም የጸና ይሁን፤የሰጠኸውንም ትተስፋ ፈፅም፤
24ይህም ስምህ ጸንቶ እንዲኖርና ለዘላለም ታላቅ እንዲሆን ነው።ከዚያም ሰዎች "የእስራኤል አምላክ ጌታ እግዚአብሔር በእውነት የእስራኤል አምላክ ነው!"ይላሉ፤የባሪያህ የዳዊትም ቤት በፊትህ የጸና ይሆናል።
25አምላክ ሆይ፤ቤት እንደምትሠራለት ለባሪያህ ገልጸህለታል፤ስለዚህ ባሪያህ ወደ አንተ ለመጸለይ ድፍረት አገኘ።
26እግዚአብሄር ሆይ፤በእውነት አንተ አምላክ ነህ፤ይህንንም መልካም ተስፋ ለባሪያህ ስጥተሃል።
27በፊትህ ለዘላለም እንዲኖር አሁንም የባሪያህን ቤት ልትባርክ ወደሃል፤እግዚአብሔር ሆዩ፤የባረክኸውን አንተ ስለ ሆንህ፣ለዘላለም የተባረከ ይሆናል።