1ከዚያም የእግዚአብሔር ታቦት አምጥተው ዳዊት በተከለለት ድንኳን ውስጥ አኖሩት፤የሚዋጠል መሥዕዋትና የኅብረት መሥዕዋትም በእግዚአብሔር ፊት አቀረቡ።
2ዳዊት የሚቃጠለውን መሥዕዋትና የኅብረቱ መሥዕዋት ከሠዋ በኋላ፣ህዝቡን በእግዚአብሔር ስም ባረከ።
3ከዚያም ለእስራኤል ሁሉ ለወንዱም ልችሴቱም አንዳንድ ሙልሙል ዳቦ፣አንዳንድ ጥፍጥፍ ዘቢብ ሰጠ።
4በእግዚአብሔር ታቦት ፊት እንዲያገለግሉና ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ልመና፣ምስጋናና ውዳሴ እንዲቀርቡ ከሌዋውያን ሰዎች ሾሙ፤
5አለቃው አሳፍ ነበረ፤ከእርሱ ቀጥሎ ዘካሪያስ ሁለተኛ ሆኖ ተሾመ፤ከዚያም ይዒኤል፣ሰሚራሞት፣ይሒኤል፣መቲትያ፣ኤልያብ፣በናያስ፣ ዖቤድኤዶም፣ይዒኤል ተሾሙ፤እነሱም በመሰንቆና በበገና ይዘምሩ ነበር፤አሳፍ ደግሞ ጽናጽል የሚጸነጽል ሆኖ ተመደበ።
6እንዲሁም ካህናቱ በናያስና የሕዚኤል ዘውትር በእግዚአብሔር የኪዳኑ ታቦቱ ፊት መለከት እንዲነፉ ተመደቡ።
7በዚያም ቀን ዳዊት በመጀመሪያ ለአሳፍና ለሥራ ጓደኞቹ ይህን የእግዚአብሔር ምስጋና መዝሙር ሰጠ፤
8ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርቡ፤ስሙንም ጥሩ፤ለአሕዛብ ያደረገውን ሁሉ ንገሩ፤
9ዘምሩለት፤ውዳሴም አቅርቡለት፤ድንቅ ሥራውን ሁሉ ንገሩ፤
10በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤እግዚአብሔር የሚፈልግ ሁሉ፤ልባቸው ሐሤት ያድርግ፤
11ወደ እግዚአብሔር ወደ ኅይሉ ተምልከቱ፤ዘውትር ፊቱን ፈልጉ፤
12ይደረጋቸውን ድንቅ ሥራዎች፣ታምራቱንና የሰጠውንም ፍርድ አስታውሱ፤
13እናንተ የባሪያው የእስራኤል ዘሮች፣እናንተ የተመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች።
14እርሱ እግዚአብሔር አምልካችን ነው፤ፍርዱም በምድር ሁሉ ላዬ ነው፤
15ኪዳኑን እስከ ዘላለም፣ይያዘዘውንም ቃል እስከ ሺህ ትውልድ ያስባል፤
16ከአብርሃም ጋር የገባውን ቃል ኪዳን፣ለይስሐቅ የማለውን መሐላ።
17ይህንንም ለያዕቆብ ሥርዐት አድርጎ አጸና፤ለእስራኤልም የዘላለም ኪዳን አደረገ፤
18እንዲህ ሱል "የምትወርሰው ርስት እንዲሆን፣የከነዓንን ምድር ለአንተ እሰታለሁ።"
19ቁጥራቸው ገና ጥቂት ሳለ፤በርግጥ ጥቂትና መጻተኞች ሳሉ፤
20ከአንዱ ሕዝብ ወደ ሌላው ሕዝብ ከአንዱም መንግሥት ወደ ሌላው መንግሥት ተንከራተቱ።
21ማንም እንዲጨቁናቸው አልፈቅድም፤ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ፤
22እንዲህ ሲል፤"የቀባኋቸውን አትንኩ፤በነብያቴ ላይ ክፉ አታድርጉ።"
23ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ማዳኑንም ዕለት ዕለት ዐውጁ።
24ክብሩን ለአሕዛብ ተናገሩ፤ድንቅ ሥራዎቹን ለሕዝቦች ሁሉ ንገሩ።
25እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤ምስጋናውም ብዙ ነው፤ከአማልዕክትም ሁሉ በላይ ሊፈራ የሚገባው ነው።
26የአሕዛብ ሁሉ አማልክት ጣዖታት ናቸው፤እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ።
27በፊቱ ክብርና ሞገስ አለ፤ ብርታትና ደስታም በማድሪያው ስፍራ።
28የአሕዛብ ወገኖች ለእግዚአብሔር ስጡ፤ክብርና ኅይልን ለእግዚአብሔር አምጡ።
29ለስሙ የሚገባውን ክብር ለእግዚአብሔር ሰጡ፤መባ ይዛችሁ በፊቱ ቅረቡ፤በቅድስናውም ክብር ለእግዚአብሔር ሰገዱ።
30ምድር ሁሉ በፊቱ ትንቀጥቀጥ፤ዓለም በጽኑ ተመሥርታለች፤አትናወጥምም።
31ሰማያት ደስ ይባላቸው፤ምድር ሐሤት ታድርግ፤በአሕዛብ መካከል፣"እግዚአብሔር ነገሠ!"ይበሉ።
32ባሕርና በውስጧ ያለው ሁሉ ይናውጥ፤ሜዳዎችና በእርሷ ላይ ያሉ ሁሉ ሐሤት ያድርጉ።
33ያን ጊዜ የዱር ዛፎች በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበላቸው፤በደስታ ይዘምራሉ፤በምድር ላይ ሊፈርዱ ይመጣልና።
34ቸር ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ፍቅሩንም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።
35«አዳኛችን እግዚአብሔር ሆይ፤ታደገን፤ለቅዱስ ስምህ ምስጋና እንድናቀርብ፣በምስጋናም እንድንከብር ስብሰበን"ብላችሁ ጩኹ።
36ከዘላለም እስከ ዘላለም፣ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ፣"አሜን፤እግዚአብሔር ይመስገን"አለ።
37ዳዊትም ለእያንዳንዱ ቀን በተመደበው መሠረት ዘውትር እንዲያገለግሉ አሳፍና የሥራ ባልደረቦቹን በዚያው በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ተዋቸው።
38እንዲሁም ዖቡድኤዶምና ሥልሳ ስምንቱ የሥራ ባልደረቦቹ አብረዋቸው እንዲያገለግሉ በዚያው ተዋቸው።የኤዶታም ልጅ ዖቤድኤዶምና ሖላ የቅጥሩ በር ጠባቂዎች ሆኑ።
39ዳዊት ካህኑን ሳዶቅንና የሥራ ባልደረቦቹን ካህናት በገባዖን ከፍተኛ ቦታ ላይ በሚገኘው በእግዚአብሔር ድንኳን ፊት ተዋቸው፤
40የተዋቸውም ለእስራኤል በተሰጠው ትእዛዝ መሠረት በእግዚአብሔር ሕግ እንደ ተጻፈው ሁሉ በመሠዊያው ላይ የሚቀርበውን የሚቃጠል መሥዕዋት ላይ የሚቀርበውን የሚቃጠል መሥዋዕት ጧትና ማታ በየጊዜው እንዲያቀርቡ ነው።
41ደግሞም፤"ፍቅሩ ለዘላለም ነውና"እያሉ ምስጋና እንዲያቀርቡ ኤማንና ኤዶታም እንዲሁም ተመርጠውና ስማቸው ተመዝግቦ የተመደቡ ሌሎችም አብረዋቸው ነበሩ።
42ድምፅ መለከቱንና ጽናጽሉን ለማሰማት፤ደግሞም መንፈሳዊ መዝሙር ሲዘመር ሊጠቀሙባቸው ሌሎች መሣሪያዎች ኅላፊዎች ኤማንና ኤዶታም ነበሩ፤የኤዶታምም ልጆች በሩን እንዲጠብቁ ተመድበው ነበር።
43ከዚያም ህዝቡ ተነሣ፤እያንዳንዱም ወደየቤቱ ሄደ።ዳዊትም ቤተ ሰቡን ለመባረክ ወደ ቤቱ ተመለሰ።