1ዳዊት በስሙ በተጠራችው ከተማ ለራሱ ብይቶችን ሠራ፤በእግዚአብሔር ታቦት ቦታ አዝጋጅቶ ድንኳን ተከለ።
2ከዚያም ዳዊት፣"የእግዚአብሔርን ታቦት እንዲሸከሙና ለዘላለም በፊቱ እንዲያገለግሉ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ከሌዋውያን በቀር፣የእግዚአብሔርን ታቦት ማንም አይሸከምም ሲል አዘዘ።
3ዳዊት የእግዚያብሔር ታቦት ወዳዘጋጀለት ስፍራ እንዲያወጡ እስራኤላዊያን ሁሉ በኢየሩሳሌም ሰበስበ።
4የአሮንን ዘሮችና ሌዋዊያውያንኑም በአንድነት ሰበሰበ፤
5ከቀዓት ዘሮች፣አለቃውን ኡርኤልንና አንድ መቶ ሃያ የሥጋ ዘመዶቹን፤
6ከሜራሪ ዘሮች፤አለቃው ዓሣያንና ሁለት መቶ ሃያ የሥጋ ዘመዶቹን፤
7ከጌድሶን ዘሮች፤ አልቃው ኤሊኤልንና አንድ መቶ ሠላሳ የሥጋ ዘመዶቹን፤
8ከኤሊጻፍን ዘሮች፤አለቃውን ሽማያንና ሁለት መቶ የሥጋ ዘመዶቹን፤
9ከኬብሮን ዘሮች፤ አለቃው ኤሊኤልንና ሰማንያ የሥጋ ዘመዶቹ፤
10ከዑዝኤል ዘሮች፤አለቃውን አሚናሳብንና አንድ መቶ ዐሥራ ሁለት የሥጋ ዘመዶቹን።
11ከዚያም ዳዊት ከህናቱን ሳዶቅንና አብያታርን፣ሌዋውያኑን ኡርኤልን፣ዓሣያን፣ኢዩኤልን፣ሽማያን፣ኤሊኤልንና አሚናዳብን ጠርቶ፣
12እንዲህ አልቸው፤"እንግዲህ እናንተ የሌዋውያን ቤተ ሰብ አለቆች ሰለ ሆናችሁ፣እናንተና ወንድሞቻችሁ ሌዋውያን ራሳችሁን ቀድሱ፤ከዚያም የእስራኤል አምላክ የእግዚአብሔርን ታቦት ወደአዘጋጀሁለት ቦታ አምጡ።
13የአምላካችን የእግዚአብሔር ቁጣ በላያችን ላይ እንዲህ የነደደው እናንተ ሌዋውያኑ ቀድሞም ስላላመጣችሁት ነው፤እኛም ብንሆን ምን ማድረግ እንዳለብን በታዘዘው መሠረት አልጠየቅነውም።
14ስለዚህ ካህናቱና ሌዋውያኑ የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔር ታቦት ለማምጣት ራሳቸውን ቀደሱ።
15ሙሴ በእግዚአብሔር ቃል እንዳዘዘው፣ሌዋውያኑ የእግዚአብሔር ታቦት በትከሻቸው ላይ በሙሎጊያዎች አድርግገው ተሸከሙ።
16ዳዊትም በዜማ መሣሪያ ማለትም በመሰንቆ፣በበገና፣በፅናፅል እየታጀቡ የደስታ ዜማዎችን እያዜሙ መዘመራንን ከወንድሞቻቸው መካከል እንዲሾሙ ሌዋውያኑ መሪዎች ነገራቸው።
17ስለዚህ ሌዋውያኑ የኢዮኤልን ልጅ ኤማንን ሾሙ፤ከወንድሞቹም የበራክያን ልጅ አሳፍን፣ከወንድሞቻቸው ከሜራራ ዘሮች የቂሳን ልጅ ኤታንን ሾሙ፤
18ከእነሱም ጋር ወንድሞቻቸውን በደረጃ ተሾሙ፤እነሱም ዘካሪያስ፣ያዝኤል፣ሰሚራ ሞት፣ይሒኤል፣ዑኒን፣ኤልያብ፣በናያስ፣መዕሤያን፣መቲትያ፣ ኤሊፍሌሁ፣ሚቅኔያ፣ደግሞም በር ጠባቂዎቹ ዖቤድ ኤዶምና ይዒኤል ነበሩ።
19መዘመራኑ ኤማን፣አሳፍ ኤታን በናስ ጸናጽል ድምፁን ከፍ እድርገው እንዲያሰሙ ተሾሙ፤
20ዘካሪያስ፣ዓዝኤል፣መዕሤያና በናያስ ደግሞ በአላሞት ቅኝት መሰንቆ ይገርፉ ነበር።
21እንዲሁም መቲትያ፣ኤሊፍሌሁ፣ሚቅኔያ፣ዖብድኤዶም፣ይዒረድኤ፣ ዓዛዝያ፣በሺሚኒት ቅኝት በገና ይደረድሩ ነበር።
22የዝማሬው ኅላፊ ሌዋዊው አለቃ ክንያን ነበረ፤ይህን ኅላፊነት የወሰደው በዝማሬ የተካነ ስለ ነበር ነው።
23በራክያና ሕልቃና ያታቦቱ በር ጠባቂዎች ነበሩ፤
24ካህናቱ ሰበኒያ፤ኢዮሣፍጥ፣ናትናኤል፣ዓማሣይ፣ዘካሪያስ፣በናያስና አልዓዛር በእግዚአብሔር ታቦት ፊት መለከት ይነፋ ነበር።ዖቤድኤዶምና ይሒያ ደግሞ ያታቦቱ በር ጠባቂዎች ነበሩ።
25ስለዚህ ዳዊት የእስራኤል ሽማግሌዎችና የሻለቃው አዛዦች የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከዖቤድኤዶም ቤት በደስታ ለማምጣት ሄዱ።
26የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙትን ሌዋውያን እግዚአብሔር ረድቶአቸው ስለ ነበር፣ሰባት ኮርማዎችና ሰባት አውራ በጎች ሠው።
27ታቦቱን የተሸከሙት ሌዋውያን ሁሉ፣መዘመራኑና የመዘመራኑ አለቃ ክናንያ የለበሱትና ዐይነት ከቀጭን በፍታ የተሠራ ልብስ ዳዊትም ለብሶ ነበር፤እንዲሁም በከፍታ የተሠራ ኤፋድ ለብሶ ነበር።
28በዚህ ሁኔታ መላው የእስራኤል ህዝብ በሆታ ቀንደ መለከትና እምቢልታ እየነፉ፣ጽናጽል እየጸነጸሉ፣መሰንቆና በገና እየደረደሩ የእግዚአብሔር የኪዳኑን ታቦት አመጡ።
29የእግዚአብሔር የኪዳኑ ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ ሲገባ የሳኦል ልጅ ሚልኮል በመስኮት ሆና ተመለከተች ፤ንጉሥ ዳዊት ደስ ብሎት ሲያሸበሽብ አይታ በልቧ ናቀችው።