1በዚህ ጊዜ የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለዳዊት ቤተ መንግሥት እንዲሠሩ መልክተኞችን፣ድንጋይ ጠራቦዎችንና አናጢዎችም ከዝግባ ዕንጨት ጋር ላከ።
2ዳዊትም እግዚአብሄር በእስራኤል ላይ አንግሦ እንዳጽናውና ስለ ሕዝቡም ስለ እስራኤል ሲል መንግጅቱን ከፍ ከፍ እንዳደረገለት አስተዋለ።
3ዳዊትም በኢየሩሳሌም ብዙ ሚስቶች አገባ፤ከእነሱም ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
4በዚያ ሳለ የወለዳቸው የልጆች ስም ይህ ነው፤ሳሙስ፣ሶባብ፣ናታን፣ሰለሞን፣
5ኢያቤሐር፣ኤሊሱዔ፣ ኤሊፋላት፣
6ኖጋ፣ናፌቅ፣ያፍያ፣
7ኤሊሳማ፣ኤሊዳሄ፣ኤሊፋላት።
8ዳዊት በእስራኤል ሁሉ ላይ ተቀብቶ መንገሡን ፍልስጥኤማውያን በሰሙ ጊዜ፣እርሱን ፍለጋ በሙሉ ኅይላቸው ወቱ፤ዳዊት ይህን ሰምቶ ሰለ ነበር ሊገጥማቸውው ወጣ።
9በዚህ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን ውጥተው የራፋይምን ሸለቆ ወረሩ።
10ስለዚህ ዳዊት፣"ወጥቼ በፍልስጥኤማዊያን ላይ አደጋ ልጣልን? አንተስ በእጄ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን? ሲል እግዚአብሔር ጠየቀ።እግዚአብሔር "አዎን ውጣ! በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ"ብሎ መለሰለት።
11ስለዚህ ዳዊትና ሰዎቹ ወደ በኣልፐራሲም ወጡ፤በዚያም ድል አደረጋቸው።ዳዊትም "ውሃ ነድሎ እንደሚውጣ ሁሉ እግዚአብሄርም ጠላቶችይን በእጄ አፈርሳቸው"አለ፤ከዚህ የተነሳ ያን ቦታ "በኣልፐራሲም"ብለው ሰየሙት።
12ፍልስጥኤማውያን አማልዕክቶቻቸውን በዚያው ጥለዋቸው ስለ ነበር፣ዳዊትት በእሳት እንዲያቃጥሏቸው አዘዘ።
13ፍልስጥኤማውያን ሸለቆውን እንደ ገና ወረሩ፣
14ዳዊትም እንደገና እግዚአብሔር ጠየቀ።እግዚአብሔር እንዲህ ሲል መለሰለት "ዙሪያውን ከበህ በሾላው ዛፍ ፊት ለፊት አደጋ ጣልባቸው እንጂ በቀጥታ ወደ ላይ አትውጣ፤
15በሾላው ዐናት ላይ የሰልፍ ድምፅ ስትሰማ ወዲያኑ ለጦርነት ውጣ፤ይህም የፍልስጥኤማውያንን ስራዊት ለመምታት እግዚአብሔር በፊትህ ወጥቶአል ማለት ነውና።
16ዝዝዚህ ዳዊት እግዚአብሔር እንዳለው አደረገ፤ከገባዖን ጀምሮ እስከ ጌዝር ድረስ ፍልስጥኤማውያንን መቷቸው።
17ከዚህም የተነሳ የዳዊት ዝና በየአገሩ ሁሉ ተሰማ፤እግዚአብሔርም መንግሥታት ሁሉ እንዲፈሩት አደረገ።