1ዳዊትም ሻለቆችና መቶ አለቆች ከሆኑት የጦር ሹማምቱ ሁሉ ጋር ተማከረ።
2ከዚያም ለመላምው የእስራኤል ማኅበር እንዲህ አለ፤"እንግዲህ ነገሩ መልካም መስሎ ከታያችሁ የአምላካችን የእግዚአብሔር ፍቃድ ከሆነ፤በእስራኤል ግዛት ሁሉ ለሚኖሩ በሩቅም ሆነ በቅርብ ላሉት ለቀሩትም ሆነ በቅርብ ላሉት ለቀሩት ወንድሞቻችን እንዲሁም በየራሳቸው ከተሞና መሰማሪያዎች የሚኖሩ ካህናትና ሌዋውያን መጥተው ከእኛ ጋር እንዲሰባሰቡ እንላክላቸው።
3በሳኦል ዘምን መንግሥት ሳንፈልገው የነበረውን የአምላካችንን ታቦት መልሰን ወደ እኛ እናምጣ።
4በገሩም በሕዝቡ ሁሉ ዘንድ ተቀባይነት ስላገኘ መላው ማኅበር ይህንኑ ለማድረግ ተስማማ።
5ስለዚህ ዳዊ የእግዚአብሔር ታቦት ከቂርያትይዓሪም ለማምጣት ከግብፅ ወንዝ ከሺሖር ጀምሮ እስከ ሐማት መተላለፊያ ድረስ የሰፈሩትን እስራኤላውያን ሁሉ ሰበሰበ።
6ዳዊትና እስራኤላዊያን ሁሉ በኩሩብና በኪሩብ መካከል የተቀመጠውን፣የእግዚአብሔር በይሁዳ ወዳለችው ቂርያትይዓሪም ወደ ተባለችው ወደ በኣላ ሄዱ።
7የእግዚአብሔርም ታቦት ከአሚናዳብ ቤት በእዲስ ሠረገላ ላይ እድርገው አመጡ፤ሠረገላውን ይነዱየነበሩትም ዖዛና አሒዮ ነበሩ።
8ዳዊትና እስራኤላዊያን ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ሆነው በቅኔና በበገና፣በመሰንቆ በከበሮ፣በጽናጽልና በመለከት በሙሉ ኅይላቸው በዓሉን በደስታ ያከብሩ ነበር።
9ወደ ኪዶን ዐውድማ በደረሱ ጊዜ በሬዎቹ አደናቅፏቸው ሰለ ነበር፣ዖዛ ታቦቱን ለመደገፍ እጁን ዘረጋ።
10ታቦቱን በእጁ ሰለ ነካ፣የእግዚአብሔር ቁጣ ዖዛን ላይ ነደደ፤ስለዚህም በዚያው በእግዚአብሔር ፊት ሞተ።
11የእግዚአብሔር ቁጣ ዖዛን በድንገት ስለ ቀሠፈው ዳዊት አዘነ፤ያም ቦታ እስከ ዛሬ ድረስ የዖዛ ስብራት ተብሎ ይጠራል።
12ዳዊት በዚያን ዕለት የእግዚአብሔር ታቦት ወደ እኔ እንዴት ማምጣት እንችላለሁ?"አለ።
13-14ስለዚህ ታቦቱን ወደ ዳዊት ከተማ በመውሰድ ፈንታ የጋት ሰው ወደ ሆነው ወደ አቢዳራ ቤት ከቤተ ሰቡ ጋር ሦስት ወር ተቀመጠ፤እግዚአብሔርም ቤተ ሰቡንና ያለውንም ሁሉ ባረከ።