1ዳዊት ከቂስ ልጅ ከሳኦል ፊት ሸሽቶ በጺቅላግ ሳለ ወደ እርሱ የመጡት ሰዎች እነዚህ ናቸው፤እነርሱም በጦርነቱ ላይ ከረዱት ተዋጊዎች መካከል ነበሩ።
2ሰዎቹ ቀስተኞች ሲሆኑ፣በቀኝም ሆነ በግራ እጃቸው ፍላጻ መወርወርና ድንጋይ መወንጨፍ የሚችሉ ነበሩ፤እነርሱም ከብንያም ነገድ የሆነው የሳኦል ሥጋ ዘመዶች ነበሩ፤
3አለቃቸው አሐዔዝር ነበረ፥ከእርሱም በኋላ ኢዮአስ ነበረ፤ሁለቱም የጊብዓዊው የሸማዓ ልጆች ነበሩ፤የዓዝሞት ልጆች ይዝኤልና ፋሌጥ፣በራኪያ፣ዓናቶታዊው ኢዩ፣
4ገባናዊው ሰማያስ ከሠላሳዎቹም መሪ ነበረ፤ርርሚያስ፣የሕዚኤል ዮሐንስ፣ገድሮታዊው ዮዛባት፣
5ኤሊዛይ፣ኢያሪሙት፣በዓልያ፣ሰማራያ፤ሐሩፋዊው ሰፋትያስ፣
6ቆሬያውያኑ ሕልቃና፣ይሺያ፣ዓዘኤል፣ዮዛር፣ያሻብዓም፣
7የጌዶር ሰው ከሆነው ደግሞ የይሮሐም ልጆች ዮዔላና ዝባድያ።
8ዳዊት በምድረ በዳ በሚገኘው ምሽጉ ውስጥ ሳለ፣ከጋድ ነገድ የሆኑ ሰዎች መጥተውው የእርሱን ሰራዊት ተቀላቀሉ፤ከእነሱም ለውጊያ የተዘጋጁ ጋሻና ጦር ለመያዝ የሚችሉ ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ፤ፊታቸው እንደ አንበሳ እንደሚይዝ ሚዳቋ ፈጣኖች ነበሩ ።
9የእነዚህም አለቃ ዔፌር ነበረ፤ሁለተኛ አዛዥ አብድዩ፣ሦስተኛው ኤልያብ፣
10አራተኛ መስመና፣አምስተኛው ኤርሚያስ፤
11ስድስተኛው ዓታይ፣ሰባተኛው ኢሊኤል፣
12ስምንተኛው ዮሐናን፣ዘጠነኛው ኤልዛባድ፣
13ዐሥረኛው ኤርሚያስ፣ዐሥራ አንድኛው መክበናይ።
14እነዚህ ጋዳውያን የጦር አዛዦች ነበሩ፣ከእነሱም ታናሽ የሆነው እንደ መቶ፣ታላቅ የሆነው ደግሞ እንደ ሺህ አለቃ ይቁጠር ነበር።
15በመጀመሪያው ወር የዮርዳኖስ ወንዝ ከአፍ እስከ ሞልቶ ሳለ፣ወንዙን ተሻግረው በስተ ምሥራቅና በስተ ምዕራብ ሸለቆዎች ይኖሩ የነበሩትን ሁሉ ከዚያ ያባረሩት እነዚህ ሰዎች ነበሩ።
16ሌሎች ከብንያምና ከይሁዳም ወገን የሆኑ ሰዎች ዳዊት ወደሚገኝበት ምሽግ መጡ።
17ዳዊትም እነዚህን ሰዎች ሊቀበል ወጥቶ እንዲህ አላቸው፤የመጣችሁት ልትረዱኝና በሰላም ከሆነ፤ከእኔ ጋር እንድትሰለፉ ልቀበላችሁ ዝግጁ ነኝ፤ነገር ግን እጄ ከበደል ንጹሕ ሆኖ ሳለ፤ለጠላቶቼ አሳልፋችሁ ልትሰጡኝ ከሆነ፤የአባቶቻችን አምላክ ይመልከተው፤ይፍረድውም።
18ከዚያም እግዚአብሔር መንፈስ በሠላሳዎቹ አለቃ በዓማሣይ ላይ ወረደ፤እርሱም እንዲህ አለ፤"ዳዊት፤እኛ ክችአንተ ጋር ነን፤ሰላም ፍፁም ሰላም ለአንተ ይሁን፤አንተን ለሚረዱም ሁሉ ሰላም ይሁን፤አምላክህ ይረዳሃል"።ስለዚህ ዳዊት ተቀበላቸው፤የሰራዊቱም አለቃ አደረረጋቸው።
19ዳዊት ከፍልስጥኤማዊያን ጋር ተባብሮ ሳኦልን ለመውጋት በሄደ ጊዜ፤ከምናሴ ነገድ የሆኑ ጥቂት ሰዎች ከድተው ከዳዊት ሰራዊት ጋር ተቀላቀሉ።እርሱ ግን ርዳታ አላደረገላቸውም፤ምክንዩም የፍልስትኤማዊያን ገዦች ምክር ካደረጉ በኋላ እንዲህ ሲሉ ልከውት ነበር፤"ከድቶ ወደ ጌታው ውደ ሳኦል ቢሄድ እኛን ያስጨርሰናል።
20ዳዊት ወደ ጺውላግ በሄደ ጊዝዜ ከድተው ወደ እርሱ የተቀላቀሉ የምናሴ ነገድ ሰዎች እነዚህ ነበሩ፤ዓድና፣ዮዛባት፣ይዲኤል፣ሚካኤል፣ዮዛባት፣ኤሊሁ፣ ጺልታይ፤እነዚህ በምናሴ ግዛት ሳሉ የሸለቆች ነበሩ።
21ሁሉ ብርቱ ተዋጊዎችና በዳዊትም ሰራዊት ውስጥ አዛዦች ሰለ ነበሩ፣አደጋ ጣዮችን በመውጋት ረዱት።
22ሰራዊቱም እንደ እግዚአብሔር ሰራዊት እስኪሆን ድረስ፤፣ዳዊትን ለመርዳት በየዕለቱ ብዙ ሰዎች ይጎርፉ ነበር።
23እግዚአብሔር ለዳዊት በገባለት ቃል ኪዳን መሠረት የሳኦል መንግሥት አንሥተው ለእርሱ ለመስጠት ዳዊት ወደ ሚገኝበት ወደ ኬቤሮን የመጡት ሰዎች ቁጥር ይህ ነው፤
24ጋሻና ጦር አንግበው ለጦርነት የተዘጋጁት የይሁዳ ሰዎች ስድስት ሺህ ስምንት መቶ።
25ከስምዖን ነገድ ለጦርነት ዝግጁ የሆኑ ሰባት ሺህ አንድ መቶ።
26ከሌዊ ነገድ አራት ሺህ ስድስት መቶ፤
27የአሮን ቤተ ሰብ መሪ የሆነውን ዮዳሄን ጨምሮ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ሰዎች፤
28ወጣቱ ብርቱ ተዋጊ ጻዶቅና ከቤተ ሰቡ ሃያ ሁለት የጦር አለቆች፤
29የሳኦል ሥጋ ዘመድ የሆኑ የብንያም ሰዎች ሦስት ሺህ፤ከነዚህም አብዛኞቹ እስከዛያች ጊዜ ድረስ ለሳኦል ቤት ታማኝ ነበሩ፤
30ከኤፍሬም ሰዎች በጎሣዎቻቸው ዘንድ ታዋቂ የሆኑ ብርቱ ተዋጊዎች ሃያ ሺህ ስምንት መቶ፤
31ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ዐሥራ ስምንት ሺህ ሰዎች፤እነርሱም ዳዊትን ለማንገሥ በየስማቸው ተጽፈው የመጡ ነበሩ።
32ዘመኑን የተረዱና እስራኤላዊያንም ምን ማድረግ እንደሚገባቸው የተገነዘቡ የይሳኮር ሰዎች ሁለት መቶ አለቆች፤በእነሱም ሥር ሆነው የሚታዘዙ ዘመዶቻቸው።
33ልምድ ያላቸው፤በሁለቱም ዐይነት መሣሪያ ለመዋጋት የተዘጋጁትና ዳዊትን ለመርዳት የመጡት መንታ ልብ የሌላቸው የዛቢሎን ሰዎች ሃምሳ ሺህ፤
34ከንፍታሌም ሰዎች አንድ ሺህ የጦር አለቆች፤ከእነርሱም ጋር ጋሻና ጦር የያዙ ሠላሳ ሰባት ሺህ ሰዎች፤
35ከዳን ሰዎች ለጦርነት የተዘጋጁ ሀያ ስምንት ሺህ ስድስት መቶ፤
36ከአሴር ሰዎች ልምድ ያላቸውና ከጦርነት የተዘጋጁ ወታደሮች አርባ ሺህ፤
37ከምስራቅ ዮርዳኖስ ከሮቤል፣ከጋድና ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ልዩ ልዩ ዐይነት መሣሪያ የታጠቁ አንድ መቶ ሃያ ሺህ ሰዎች።
38እነዚህ ሁሉ በሰራዊቱ ውስጥ ለማገልገል ፈቃደኞች የሆኑ ተዋጊዎች ናቸው፤ወደ ኬብሮን የመጡትንም ዳዊትም በእስራኤል ሁሉ ላይ ለማንገሥ ወስነው ስለ ነበር ነው።የቀሩትም እስራኤላዊያን ሁሉ ዳዊትን ለማንገሥ በአንድ ሐሳብ ጸኑ።
39የሚያስፈልጋቸውን ቤተ ሰቦቻቸው አዘጋጅተውላቸው ሰለ ነበር፣ሰዎቹ እየበሉና እየጠቱ ከዳዊት ጋር ሦስት ቀን ቁዩ።
40እንዲሁም ሩቅ ከሆነው ከይሳኮር፣ከዛቢሎንና ከንፍታሌም አገር ሳይቀር ጎረቤቶቻቸው በአህያ፣በግመል፣በበቅሎና በበሬ ጭነው ምግብ አመጡላቸው፤በእስራኤል ታላቅ ደስታ ሰለ ሆነ ዱቄት፣የበለስና የዘቢብ ጥፍጥፍ፣የወይን ጠጅ፣የወይራ ዘይት፣የቀንድ ከብትና በጎች በገፍ ቀርበው ነበር።