1እስራኤል ሁሉ በኬብሮን ወደ እነሆ፤እኛ የገዛ ሥጋህና ደምህ ነን፤
2-3በቀደመው ዘመን ሳኦል ንጉሥ ሆኖ ሳለ እስራኤልን ወደ ጦርነት የምትመራ አንተ ነበርህ፤እግዚአብሔር አምላክም፣ሕዝቤን እስራኤልን የምትጠብቅ አንተ ነህ፤ንጉሥ ዳዊት ወዳለበት ወደ ኬብሮን መጡ፤ዳዊትም በኬብሮን በእግዚአብሔር ፊት ከእነሱ ጋር ቃል ኪዳን ገባ።እግዚአብሔር በሳሙኤል አማካይነት በሰጠው ተስፋ መሠረት ዳዊትን ቀብተው በእስራኤል ላይ አነገሡት።
4ዳዊትና እስራኤላዊያን ሁሉ ኢያቡስ ወደምትባለው ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ።በዚያም የሚኖሩ ኢያቡሳዊያን፤
5ዳዊትን "ወደዚያ ፈፅሞ አትገባም"አሉት፤ዳዊትግን የጽዮንን ምሽግ ያዘ፤እርሷም የዳዊት ከተማ ናት።
6ዳዊትና "ኢያቡሳዊያንን ቀድሞ የሚወጋ ሰው የሰራዊቱ አዛዥ ይሆናል"አለ፤ስለዚህ የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ በመጀመሪያ ወጣ፤እርሱም አዛዥ ለመሆን በቃ።
7ከዚያም ዳዊት መኖሪያውን በዐባምዩቱ ውስጥ አደረገ፤ከዚያም የተነሣ የዳዊት ከተማ ተባለች።
8ዳዊትም ከሚሎ ጀምሮ የከተማይቱን ዙሪያ ቅጥር ሠራ፤ኢዮአብ ደግሞ የቀረውን የከተማይቱን ክፍል መልሶ ሠራ።
9እግዚአብሔር ጸባኦት ከእርሱ ጋር ሰለ ነበር ዳዊት በየጊዜው እየበረታ ሄደ።
10የዳዊት ኅያላን ሰዎች አለቆች እነዚህ ናቸው፤እነርሱም እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ መሠረት መንግሥቱን በምድሪቱ ሁሉ ትስፋ ዘንድ ከሌሎች እስራኤላዊያን ጋር ሆነው ለመንግሥቱ ብርቱ ድጋፍ ሰጡ።
11ዳዊት ኅያላን ሰዎች ስም ዜርዜር ይህ ነው፤ ሐክሞናዊው ያሶብዓም የጦር መኮንኖች አለቃ ነበረ፤እነርሱም ጦሩን አንጅቶ በአንድ ጊዜ ሦስት መቶ ሰው ገደለ።
12ከእርሱም ቀጥሎ ከሦስቱ ኅያላን አንዱ የሆነው የአሆሃዊው የዱዲ ልጅ አልዓዘር ነው፤
13እርሱም ፍልስጥኤማዊያን ለጦርነት በተሰበሰቡ ጊዜ በፈስደሚም ከዳዊት ጋር አብሮ ነበረ፤ገብስ በሞላበት የእርሻ ቦታ ወታደሮቹ ከፍልስትኤማውያን ፊት ሸሹ፤
14ይሁን እንጂ በእርሻው መካከል ቦታ ይዘው ስለ ነበረ ፍልስጥኤማውያንን ገደሉ፤እግዚአብሔር ታላቅ ድል ሰጣቸው።
15ከፍልስጥኤማውያን ሰራዊት ጥቂቱ በራፋይም ሸለቆ ሰፍሮ ሳለ፣ከሠላሳዎቹ አለቆች ጆስቱ ዳዊትን ለመገናኘት በዓዶላም ዋሻ አጠገብ ወደሚገኘው ወደ ዐለቱ ወረዱ።
16በዚያን ጊዜ ዳዊት በምሽጉ ውስጥ ነበረ፤የፍልስጥኤማዊያን ሰራዊት ደግሞ በቤተልሕም ነበረ።
17ዳዊትም ውሃ ፈልጎ ነበርና፣"ከቤተ ልሔም በር አቅራቢያ ከሚገኘው ጉድጓድ የምጠጣው ውሃ ማን ባመጣልኝ!" አለ።
18በዚህ ጊዜ ጆስቱ የፍልስጥኤማውያንን ሰራዊት ጥሰው በማለፍ በቤተ ልሔም በር አጠገብ ከሚገኘው ጉድጓድ ውሃ ቀድተው ለዳዊት አመጡለት፤እርሱ ግን ሊጠጣው ስላልፈለገ በእግዚአብሔር ፊት አፈሰሰው፤
19ከዚያም "ይህን ከማድረግ እግዚአብሔር የጠብቀኝ፤ይህ በሕይወታችን ቁርጠው የሄዱትን የእነዚህን ሰዎች ደም እንደ መጠጣት አይደለምን?"አለ።ይህን ለማምጣት በሕይወታቸው ቁርጠው ስለ ነበር፣ዳዊት ሊጠጣው አልፈለገም።
20የኢዮአብ ወንድም አቢሳ የጆስቱ አለቃ ነበረ። እርሱም ጦሩን አንሥቶ ሦስት መቶ ሰዎች ገደለ፤ከዚህም የተነሣ እንደ ሦስቱ ሁሉ ዝነኛ ሆነ፤
21ከጆስቱ አንዱ ሆኖ ባይቁጠርም እንኳን፣እጥፍ ክብር አገኘ፤አዛዣቸውም ሆነ።
22ከቀብስኤል የወጣውና ታላቅ ጀብዱ የሠውው የዮዳሄ ልጅ በናያስ ብርቱ ተዋጊ ነበረ።እርሱም እጅግ ያታወቁ ሁለት የሞአብ ሰዎች ገደለ።እንዲያውም አንድ ጊዜ በረዶ ምድርን በሰፈነበት ቀን ወደ አንድ ጉድጓድ ወርዶ አንበሳ ወደለ።
23ደግሞም ቁመቱ አምስት ክንድ የሆነ አንድ ግብፃዊው የሸማኔ መጥቅለያ የመሰለ ቶር በእጁ ይዞ ገጠመው፤ክችግብፃዊው ጋር እጅ ጦሩ ነጥቆ በገዛ ጦሩ ገደለው።
24የዮሄዳ ልጅ በናያስ የፈፀመው ጀብዱ ይህ ነበር፤እርሱም እንደ ሦስቱ ኅያላን ዝነኛ ሆነ።
25ከሠላሳዎቹም ይልቅ የበለጠ አንዱ አልነበረመ፤ዳዊትም የክብር ዘቡ አዛዥ አደረገው።
26ኅያላኑ ወንድም አሣሄል፤የቤተ ልሔም የዱዲ ልጅ ኤልያናን፤
27ሃሮራዊው ሳሞት፣ፊሎናዊው ሴሌዴ፣
28የቴቁሔ ሰው የሆነው የዓስካ ልጅ፣ዒራስ፣የዓናቶቱ ሰው፣አቢዔዜር፣
29ኩሳዊው ሴቤካይ፣ኦሆሃዊው ዔላይ፣
30ነቶፋዊው ማህራይ፣የነቶፋዊው የበዓና ልጅ ሔሌድ፣
31ከብንያም ወገን የጊብዓ ሰው የሆነው የሪባይ ልጅ ኤታል፣ጲርዓቶናዊው በናያስ፣
32የገዓስ ሸለቆዎች ሰው የሆነው ኡሪ፣ዓረባዊው አቢኤል፣
33ባሕሩማዊው ዓዝሞት፣ሰዓልቦዊው ኤልያሕባ፣
34የጊዞናዊው የአሳን ልጆች፣የሃራራዊው የሻጌ ልጅ ዮናታን፣
35የሃራራዊው የሳኮር ልጅ አሒአም፣የኡር ልጅ ኤሊፋል፣
36ምኬራታዊው ኦፌር፣ፍሎናዊው አኪያ፣
37ቀርሜሎሳዊው ሐጽሮ፣የኤዝባይ ልጅ ነዕራይ፤
38የናታን ወንድም ኢዮኤል፣የሃግሪ ልጅ ሚብሐር፣
39አሞናዊ ጼሌቅ፣የጽሩያ ልጅ የኢዮአብ ጋሻ ጃግሬ ቤሮ ታዊው ነሃራይ፣
40ይትራዊው ዒራስ፣ይትራዊው ጋሬብ፣
41ኬጤያዊው ኦርዮ፣የአህላይ ልጅ ዛባድ፣
42የሮቤላዊው የሺዛ ልጅ ዓዲና፣እርሱም የሮቤላዊያንና አብረውት ለነበሩት የሠላሳ ሰዎች አለቃ ነበረ።
43የማዕካ ልጅ ሐናን፣ሚትናዊው ኢዮሣፍጥ፣
44አስታሮዊው ዖዝያ፣የአሮዔራዊው የኮታም ልጆች ሻማና ይዒኤል፣
45የሺምሪ ልጅ ይዲኤል፣ወንድሙም ቴዳዊው ዮሐ፣
46መሐዋዊው ኤሊኤል፣የኤልነዓም ልጆች ይባሪይና ዮሻውያ፣ሞዓባዊው ይትማ፣
47ኤሊኤል፣ዖቤድና ምጾባዊው የዕሢኤል።